ETHIO12.COM

ጌታቸው ረዳ ከሸኔ ጋር ሲላላ “…የአማራ ሕዝቦች ወንድምነት ይለምልም” አሉ

ኦነግ ሸኔና የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ /ትህነግ የመለያታቸው ዜና እየተነከረ በሄደበት፣ ሂውማን ራይትስዎች የትህነግ ታጣቂ ወራሪዎች የፈጸሙት እጅግ አስደንጋጭ ግፋና ወንጀል ቆንጥሮ በውስን ስፍራ ብቻ የተፈጸሙትን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ አቶ ጊታቸው ረዳ “የትግራይና የአማራ ህዝቦች ወንድማማችነት ይለምልም” ሲሉ ተዛበቱ።

የሁለቱን ሕዝብ በፈጠራ ድርሰት አላኩሶ፣ አማራውን የትግራይ ሕዝብ ልዩ ጠላት አድርጎ የቆየው ትህነግ፣ ያለፈው ቢቀረ አሁን ላይ ክልሉን ወሮ የፈጸመ ወንጀል ገና ሳያገገን አቶ ጌታቸው ” … ብዙም ስላላነሰነው ደግና ሩህሩህ ያማራ ህዝብ አለመናገር ትልቅ ስህተት ይሆናል” ብለዋል። አክለውም “ሃላፊነት የጎደለው ተስፋፋፊ” ሲሉ ልሂቃኑንን በመስደብ ” አማራ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን” ላሉት ማጣፊያ ሰጥተዋል። ይህ አዲስ አካሄድ ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለው ግንኙነት በከሚሴና በተጀመረው ግጭትና የትህነግ ሃይል ሲሸሽ የሸኔን ሃይል ” አትከተሉን” በሚል በክህደት ማስመታቱን ተከትሎ ወደ መለያየት እየመራ በመሆን የተነሳ ሊሆን እንደሚችል አስተያየት የሰጡ አሉ።

“ደጉና ሩህሩሁ” ያሉት የአማራ አርሶ አደርና የአማራን ሕዝብ ዛሬ ማመስገን የፈለጉበት ምክንያት ምን እንደሆነ ሳያስታውቁ፣”… የሸዋ ወሎ ጎንደር ህዝብ እስካሁን ሰራዊታችን በደረሰበት ሁሉ የሰራውን ትልቅ ስራ መቸም አንዘነጋም። ታጋዮቻችን ያሉትን ነው የደገምኩት” ሲሉ ያስታወቁት አቶ ጌታቸው ” ምንድን ነው ዛሬ የጠጣኸው” ከሚለው ጀምሮ ሰፊ ስድብ ወርዶባቸዋል።

ይህ ወራሪ መንጋ በአማራ አርሶ አደሮች ቤት ሊጥ እየጠጣ፣ አሻሮና እንኩሮ ሳይቀር እየበላ፣ ዶሮና እንቁላል እየሰረቀ፣ የክልሉን ሃብት እያወደም፣ ንጹሃንን እየፈጀ፣ እናት፣ መነክሴና ሕጻን ሳይል በደቦ እየደፈረ እንደቆየ ማስረጃ የቀረበበትን፣ የጦር ወንጀል መፈጸሙ የተረጋገጠበትን ሃይል ” እነሱ የነገሩኝን ነው የምደግመው” በሚል ከዚህ ሁሉ ወንጀል ማጥ ውስጥ ተነክሮ አቶ ጌታቸው ለዚህ ሕዝብ “እናመሰግናለን” ማለታቸው የቀኑ አስገራሚ ዜና ሆኗል።

” የህዝብ ለህዝብ ጥላቻ ነጋዴዎች” ሲሉ አቶ ጌታቸው ገጽ ላይ አስተያየት የሰጡ ” ለዚህ ነዋ” ሲሉ ሰፊ ህሊናን የሚፈትን ጥያቄ አንስተዋል።

ለዚህ ነዋ


Exit mobile version