Site icon ETHIO12.COM

ሴናተር ጂም ኢንሆፍና እንደራሴ ካረን ባስ የባይደን አስተዳደር ውሳኔውን እንዲቀይር ጠየቁ ” የጀኖሳይድ ውንጀላ ክስ ረቂቅ መከነ”

ኢትዮጵያን በጅኖሳይድ ለመጠየቅ በአሜሪካ ሴኔት ቢሮ የታሰበው #HR_4350 ውስጥ አንቀፅ 6464 ከረቂቅነት መሰረዙ ተገለጸ

“በተለያዩ ምንክንያቶች ኢትዮጵያ ከልቤ ውስጥ ናት” በማለት የባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያ ላይ ሊጥል ቀን የቆረጠበትን የአግዋ ውሳኔ እንዲያነሳ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አመለከቱ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንደራሴ ካረን ባስም አገራቸው ውሳኔውን እንድታጤንና እንድትቀይር ጥረት ላይ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል። ቻይና ለአፍሪካ የግብርና ምርቶች ነፃ ገበያን ለመፍቀድ መወሰኗና የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ መሄድ ተነስቷል።

“የባይደን አስተዳደር በዴሞክራሲ የተመረጠውን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት መደገፍ ይገባዋል” ሲሉ የተደመጡት ሴናተሩ ” በኢትዮጵያ ፖለቲካ እየሆነ ያለው አይገባኝም። አንድ ነገር ግን ግልጽ ነው በርካቶች ይሞታሉ ….” ሲሉ የየዕለቱ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው አመልክተዋል። ቻይና 300 ቢልዮን ዶላር በሶስት ዓመት ውስጥ አፍሪቃ ውስጥ በኢንቨስትመንት ለማዋል ማቀዷን፣ ሩሲያና ቻይናን በተደጋጋሚ በማንሳት የባይደን አስተዳደር ስህተት መስራቱን ያመለተቱት ሴናተሩ በአዲስ ዓመትና በክሪስማስ ዋዜና መልካም ዜና እንዲሆን አሳሰበዋል።

The Biden administration should take real steps to undo the sanctions against the democratically elected government of Ethiopia and roll back the termination of AGOA benefits. Watch my full remarks:

የምክር ቤት አባሏ ካረን ባስ በበኩላቸው የአፍሪካ ሃገራት በአሜሪካ ገበያ እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያዘውን የአጎዋ ስምምነት የባይደን አስተዳደር እኤአ ከጥር 1 ቀን 2022 ጀምሮ እንዲቋረጥ ያስተላለፈው ውሳኔ ጥድፊያ የተሞላበት ስለሆነ እንዲራዘም የሚፈልጉ መሆኑን ባወጡት መግለጫ አመልክተዋል።

ካረን ባስ፤ እኤአ ህዳር ሁለት የተላለፈው የአጎዋ እገዳ ውሳኔ የኢትዮጵያን ህዝብና መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሱ አካላትን የሚጎዳ በመሆኑ እገዳው እንዲነሳ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ካረን ባስ “እኤአ ከጥር 1/2022 ጅምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በድንገት የተላለፈው ውሳኔ ዜጎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ከማምጣት በቀር ለሰላሙ ምንም አማራጭ አይሰጥም፤ፍይዳ ቢስ ነው” ሲሉ አሳስበዋል፡፡ አያያዘውም ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ለችግር ተጋላጭ የሆኑትን የህብረተሰ ክፍሎች ችግሮች ያባብሳል በማለት አክለዋል፡፡

እንደራሴ ካረን ባስ

በፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያን ከአገጎዋ በማስወጣት ፍላጎታቸውን ለመጫን የተሸረበው ሴራ ከባድ ስህተት መሆኑን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ወዳጆችና ስለ ሴራው የሚያውቁ ምሁራኖች በሰፊ መሰረታዊ አመክንዮ ተቅቅውሟቸውን ሲገልፁ መቆየታቸው የሚታወስ ነው። አሁንም እየገለጹ ሲሆን የቻይና ድንገተኛ ውሳኔ የአሜሪካን አቋም ሊያስቀይር እንደሚችል ያመላከቱም ነበሩ።

ቻይና ለአፍሪካ የግብርና ምርቶች ነፃ ገበያን ለመፍቀድ የወሰነችው ውሳኔው የተሰማው የቻይና-አፍሪካ 8ኛው የሚኒስትሮች ጉባኤ በሴኔጋል ዳካር በተካሄደበት ወቅት ፕሬዝዳንት ሺን ጂንፒንግ ባሰሙት ንግግር ነው። ለአፍሪካ የግብርና ምርቶች ከታሪፍ ነፃ የገበያ ዕድልን ለመፍጠር የተወሰነው ውሳኔ ይፋ ከመሆኑ በፊት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የገበያ ትሥሥራቸውን ወደ ኢሲያና መካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም አፍሪካ ላይ እንደሚተክሉ ደጋግመው አስታውቀው ነበር።

በርካታ አስገራሚ ውሳኔዎችና የምስራች ይዞ የመጣው የቻይና-አፍሪካ 8ኛው የሚኒስትሮች ጉባኤ በመጪው ሶስት ዓመታት በአፍሪካ 300 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት እቅድንም ይፋ አድርጓል። አፍሪካ ወደ አምራች አገርነት እንድትቀየር የሚያንደረድራት ይህ ዕቅድ አሜሪካን ማስደንገጡም ተሰምቷል።

ቻይና ከአፍሪካ ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን የበለጠ ለማጠናከርና የልማት አጋርነቷን ለማሳየት ለአዳጊ አገራት በምትሰጠው ነፃ የገበያ ዕድል በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ከአፍሪካ ወደ ቻይና የሚገቡት ምርቶች ዋጋ 300 ቢሊዮን ዶላር እንዲደርስ ያለመ ነው፡፡በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ ዳይሬክተር ጄኔራሉ ው ፔንግ ነበሩ ለአፍሪካዊያን የታቀደውን የፕሬዝዳንት ሺን ጂንፒንግ ውሳኔን ይፋ ያደረጉት፡፡ በዚህ መነሻ ነው ” የቻይና ዕቅድ አሜሪካ ውሳኔዋን እንድትመረምር ተጽዕኖ ይፈጥራል” ሲሉ ቀደም ብለው አስተያየት የሰጡ አሉ።

በሌላ ታላቅ ዜና ኢትዮጵያን በጅኖሳይድ ለመጠየቅ በአሜሪካ ሴኔት ቢሮ የታሰበው #HR_4350 ውስጥ አንቀፅ 6464 ከረቂቅነት መሰረዙ ተረጋግጧል። የኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል ትላንት ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ለካውንስሉ በላኩት መረጃ አንቀጹ መሰረዙን አመክተዋል።

ኢትዮጵያን በጅኖሳይድ ለመጠየቅ በሴኔት ቢሮ የታሰበው #HR_4350 ውስጥ አንቀፅ 6464 ከረቂቅ Determination of potential Genocide or crimes Against Humanity የሚለው ሙሉ በሙሉ ህጉ መሰረዙን ነው ካውንስሉ ይፋ ያደረገው።ይህንን ለማሰረዝ ትላንት ከፍተኛ ስብሰባ በሴኔተር ጂም እና በሲቪክ ካውንስሉ መካከል አጅንዳ ሆኖ ክርክር ተደርጎበት እንደነበ ካውንስሉ አስታውቋል።

ኢትዮጵያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ፕሬዝዳንትም ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ለሴኔተር ጀምስ ኢንሆፍ “የክፉ ቀን የቁርጥ ወዳጃችን ነዎት እና በመላው የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን እንዲሁም በመላው የዲያስፖራ ደጋፊዎቻችን ስም እጅግ እናመሰግናለን ሲሉ” መልስ መስጠታቸው ታውቋል። ድርጅቱን ጠቅሶ የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።


Exit mobile version