የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግን በተደጋጋሚ ” አሸባሪ ቡድን” እያሉ የጠሩት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አስራ አራት ደቂቃ በፈጀው ንግግራቸውን ሲቋጩ የኢትዮጵያን ታሪክ በመረዳትና በማክበር ” ኢትዮጵያዊያን ወዳጆቼ ” አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በስም ጠርተው ” አብረንዎት ነን” የሚል ማረጋገጫ ሰጡ። የተዘጋጀው የቪዛ ማእቀብ የሚፈይደው አንዳችም በጎ ነገር እንደሌለ አመልክተው ይልቁንም መርዳት እንደሚሻል፣ አብይ አህመድም ሰላሟ የተተበቀ አንድ አገር እየገነቡ እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ አመለከቱ።
” የማይገባ፣ እጅግ ስህተት የሆነ፣” ሲሉ የገለጹትን የአሜሪካ አቋም ” በፍጹም ተቀባይነት የሌለው” በማለት አራክሰው እንደማይቀበሉት ይፋ ካደረጉ በሁዋላ ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከጎንዎት ነን” ሲሉ በአደባባይ መናገራቸው ይህን ኢትዮጵያን ለሚወዱ ሁሉ ብስራት ሆኗል።
በንግግራቸው ከኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም ጀመሮ የነበረውን አስተዳደር የቃኙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ” የተማሩና ብልህ መሪ” ሲሉ አድነቀዋቸዋል። አያይዘውም ” በአፍሪካ እንደ እሳቸው ያለ መሪ አላየሁም” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።
ከለውጡ ማግስት ጀምሮ “የሽብር ቡድን” ሲሉ የጠሩት ትህነግ በርካታ ክፉ ተግባራትን ሲያከናውንና መንግስትን ሲያውክ መኖሩን አውስተው፣ በመቸረሻም ራሱን አግልሎ በኮቪድ ምክንያት ምርጫ ሲራዘም በማፈንገጥ የራሱን ምርጫ ያከናወነና ማዕከላዊ መንግስትን የማይታዘዝ ቡድን እንደነበር ጠቁመዋል።
ሴናተሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የበለጸገች፣ አንድነቷን የጠበቀች፣ ሰላማዊ አገር ለመገንባት እየሰሩ መሆኑንን አመልክተው፣ ወደ ስልጣን ሲመጡ ቃል የገቡትን በመፈጸማቸው ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል። እስረኞች ፈተዋል። ጋዜተኞችን ለቀዋል። የፖለቲካ ምህዳሩን አስፍተዋል ሲሉ በሽግግር ጊዜ ውስጥ ተሰሩ ያሉዋቸውን ዘርዝረዋል።
“አሸባሪው ህወሓት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደስተኛ አልነበረም፤ ከመንግስትም ጋር አብሮ ለመስራት እንቢተኛ ሆነ፤ ተቃውሞውንም አገሪቷን በማወክ መግለጽ ጀምሮ ነበር፤ በዚህ የህወሓት ሽብር የተሞላበት አካሄድ የተነሳ የኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፤ ይህንን አሸባሪ ድርጅት የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት እኩል ማየት መጀመሩ ስህተት ነው፣ ተቀባይነት የለውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ጥረት እያደረጉ ነው” ሲሉ የተደመጡት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አብይ አህመድ አምላካቸውን የሚፈሩ መሆናቸውንም አክለዋል።
ትሀንግ ካፈነገጠ በሁዋላ ሚሊሻ አደረአጅቶ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ማጥቃቱንና መሳሪያ መዝረፉን ያስታወሱት ታዋቂው የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል እና የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማእቀብ ከቶውንም ፍትሃዊ ሊባል እንደማይችል አስምረውበታል። ሲቀጥሉም ኢትዮጵያ የብሄራዊ መከላከያ ሃይሏ ከተጠቃ በሁዋላ ምላሽ መስጠቷን ” እውነታው ይህ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?More stories “ትህነግ የኤርትራና ኢትዮጵያ የጋራ ጠላት ነው”ያሉት የአትላንቲክ ካውንስል ተመራማሪ ዛሬም “አሸባሪ” ሲሉ ተጠያቂ አደረጉትAugust 3, 2021… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት