Site icon ETHIO12.COM

ከመቀለ 50 ኪሎ ሜትር ውጊያ ተጀምሯል፤ የጥምር ጦሩ ወደ ሰቆጣ አምርቷል

” የትግራይ አማጺያን ባለ ምጡቅ አዕምሮ” በሚል ስያሜ ሲቆላመጡና ሲወደሱ የነበሩት ጻድቃን ለጊዜው ድምጻቸው አልተሰማም። ጦርነቱ በሳምንታት ወይም በቀናት ያበቃል እነደሚያበቃ፣ ጦራቸው ወደ አዲስ አበባ እየገፋ እንደሆነና ” ድርድር ከማን ጋር” ሲሉ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመጡት ጻድቃን ስለ አዲሱ ” ማፈግፈግ” እስካሁን ማብራሪያ አልሰጡም። ” የጦር ሜዳ ሊቀ ሊቃውንት” ብሎ ቢቢሲ ወደ ሰማይ ያጎናቸው ሌተናል ጂነራል ጻድቃን የተሞካሹበት የጦርነት ስልት ” የድጋይ ዘመን የጦርነት ዘዴ፣ የሰው ማዕበል ማዝነብ” ነው በሚል “አይ ሊቀ ሊቃውንት” ሲሉ የሳቁም ነበሩ።

ምንም ተባለ ምን ሸዋ ደርሶ የነበረው የትህነግ የሰው ማእበል ወደ አዲስ አበባ ስያሆን ወደ ትግራይ መመለስም ቀላል እንዳልሆነለት እየተነገረ ነው። በገሃድ ጦር ሜዳ ገብተው ውጊያ እንደሚመሩ የተነገረላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ይህ ሃይል ከመቀለ በራቀ ቁጥር የሽንፈት ቀለበት ውስጥ እየገባ ይሄዳል” በሚልመናገራቸው ይታወሳል:

ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ” በቅርቡ መቀለ” በሚል ከተናገሩት ውጭ የመንግስት የሁለተኛው ዘመቻ ኢላማ ምን እንደሆነ በግልጽ የተባለ ነገር የለም። የሆነ ሆኖ ግን ከአፋር በኩል እየሰረሰረ የገባው ሃይል፣ ከወሎ ግንባር እየገፋ የመጣውና ጋሸናን እያጸዳ ያለው ሃይል ተዳምሮ በዘረጋው የማጥቃትና የከበባ ስትራቴጂ ” የገባው እንዳይወጣ” የሚባለውን ስልት ጥምር ሃይሉ እየተገበረው መሆኑ ተሰምቷል። ሃላፊዎችና መንግስትም ይህንኑ እያረጋገጡ ነው።

የጣምራው ጦር ከኢትዮጵያ አይር ሃይል ጋር በመሆን ሰፊ ቁሳዊና ሰብአዊ ኪሳራ አድርሶ የሳንቃን፣ የሲሪንቃን፣ የሰሜን ወሎ ዋና ከተማ የሆነችውን ወልድያ ከተማን፣ ሐራን፣ ጎብየን፣ ሮቢትን እና ቆቦን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን መንግስት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው የትህነግ ወራሪ ሃይል በአፋር አባላ ከተማ ላይ አዲስ ጥቃት መሰንዘሩ የተሰማው።

ከመቀለ 50 ኪሎ ሜትር በምትገኝ አባላ Abala (Abqaala) በምትባል የአፋር ትንሽ ከተማ ላይ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ሃይል ዛሬ ጥቃት መጀመሩን ዶክተር ኮንቴና ሌሎች የአፋር አክቲቪስቶች የአካባቢውን አስተዳደር ጠቅሰው ይፋ አድርገዋል።

Afar Watch@AfarWatch·21m የሚባለውና ስለ አፋር ክልል ታማኝ መረጃዎችን ቀድሞ የሚያወጣው ገጽ የአፋር ሃይሎች አጻፋ መመለሳቸውንና ” በአማኤሪካ የሚደገፈው አሸባሪ” የሚሉትን ሃይል ዳግመኛ ስጋት ሊሆን በማይችልበት መልኩ በማጥቃት እንደሚያሸመደምዱት ገልጿል። ራሳቸውን የመከላከል ብቻ ሳይሆን አልፎ የመሄድ እርምጃም እንደሚወስዱ አስታውቋል።

ዶክተር ኮንቴ ሙሳ በቲውተር ገጻቸው ትህነግ ጭፍጨፋ መፈጸሙ ብቻ ሳይሆን የትግራይ ተወላጆችም እርዳታ እንዳይገባላቸው እንቅፋት መሆኑን አስታውቀዋል። ለሰብአዊ እርዳታ መስተጓጎል ኢትዮጵያን አትውቀሱ ብለዋል። ስለ ጥቃቱ ብዙ ዶክተር ኮንቴ ብዙ መረጃ ባይጽፉም፣ ሌሎች እንዳሉት ከሆነ ግን የአጻፋ እርምጃው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የጥምር ሃይሉ ወልደያንና ከላይ የተዘረዘሩትን አካባቢዎች መቆጣጠሩን ተከትሎ አቶ ጌታቸው አላማጣ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙንና ሲቪል ሰዎች መጎዳታቸውን አስታውቀዋል። አሁን ላይ እንደሚሰማው ከሆነ የጥምር ሃይሉ ወደ አላማጣ መተጋቱ ነው።

ዘመቻው አላማጣ ከደረሰና ከመቀለ 50 ኪሎሜትር ላይ የተጀመረው ውጊያ የፋር ባለስልታናት እንዳሉት ማጥቃታቸውን የሚያተናክሩ ከሆነ ነገሩ ሌላ ተልዕኮ ሊኖረው እንደሚችል እየተገመተ ነው።

ላለፉት አራት ወራት ወረዋት ከነበረችው ወልደያ በሽንፈት ተደምሠውና ተመተው እንደወጡ መገለጹ ሃሰት መሆኑን ገልጸው አቶ ጌታቸው አሁንም ” ወደንና ፈቀደን ነው የወጣነው” ሲሉ አስታውቀዋል። እስከየትና እምን ድረስ አውቀው እንደሚለቁ ግን ፍንጭ አልሰጡም።

የውጊያ ስልት አርቃቂውና ባረቀቁት ስልት እጅግ ተወድሰው ” ሊቀ ለቃውንት” የተባሉት ጻድቃን ይህ እስከታተመ ድረስ ያሉ ነገር የለም።

የዲያስፖራው የትህንገ ደጋፊ ክንፍ ግን ስጋት እንደገባው የሚገልጽ መረጃ እያሰራጩ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። አቶ ጌታቸውን ” አትዋሽ” የሚል ምላሽ መሰንዘር የጀመሩም አሉ።

አቶ ጌታቸው ” መጣንላችሁ እናንተ ወጠጤዎች” ካሉዋቸው መካከል አንዱ የአብን ምክትል ሊቀመንበር አቶ የሱፍ ” የት ነህ ወዳጄ ቀሪ ሃሳብ አለህ..?” ሲሉ አቶ ጌታቸው ላይ ተዛብተውባቸዋል። አቶ የሱፍ ” እመኑኝ ደሴን የምናይበትን ቀናት በጣታቸን እየቆጠርን ነው” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። እሳቸው ይህን ባሉ በሰባተኛው ቀን ደሴ እናት አገሯን እቅፍ ውስጥ ሆናለች።


Exit mobile version