ETHIO12.COM

የተመድ የሰብአዊ መብቶች ውሳኔ ” ለይቶ ማልቀስ”

“ውሳኔ ሰጥቶ ሸንጎ መቀመጥ” ሲል ነው መንግስት ዛሬ በኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኩል ያስታወቀ። የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በሚጥስ መልኩ የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ኢትዮጵያ ላይ የውሰነውን ውሳኔም ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበለው በይፋም አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ልዩ ስብሰባ አካሂዶ አፍሪካውያን ሙሉ በሙሉ ጀርባቸውን በሰጡት ስብሰባ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን የሚያጣራ ዓለም አቀፍ መርማሪ አካል ለማቋቋም የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ያጸደቀው የመንግስታቱ ድርጅት፣ ከአፍሪካ አንድም ድጋፍ ያላገኘ ሲሆን ሃያ አንድ አገሮች ደግፈውት፣አስራ አምስት አገራት ተቃውመውት፣ አስራ አንድ አገራት ድምጸ ተአቅቦ አድርገውበት የተወሰነ ሲሆን፣ ከውሳኔው በላይ ዜና የሆነው የአፍሪካ አገራት ዝምታ የበርሊኑንን ዝግ የቅርምት ስብሰባ ማስታወሱ ነው። አፍሪቃ ላይ በሩን ከርችሞ ስለቅርመት የመከረውን የቅኝገዢዎች ሴራ “ገለልተኛነት የጎደለው ገለልተኛው ተቋም” የሚለውን ማስፈንተሪያ ተጭነው ያንብቡ


ገለልተኝነት የራቀው “ገለልተኛው ተቋም”

ምዕራባዊያኑ አፍሪካን በቅኝ ግዛት ለመቀራመት በርሊን ላይ ሲመክሩና የበርሊኑን ስምምነት ሲያጸድቁ የመምከሪያ አዳራሹ በር ለአፍሪካ እና አፍሪካዊያን ዝግ ነበር፡፡ አፍሪካ ላይ በር ከርችመው በጣጥሰው ሲቀራመቷት…..


በአውሮፓ ሕብረት ተዘጋጅቶ የቀረበውና የጸደቀው ረቂቅ ከዚህ በፊት የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር በጣምራ ያካሄዱትንና በተመድ ሙሉ እውቅና የተሰጠውን ሪፖርት ትቶ ከዜሮ እንደ አዲስ ምርመራ እንዲጀመር የሚያደርግ ነው። ሪፖርቱን መንግስት በመርህ ደረጃ እንደሚቀበለው አመልክቶ በጥፋተኞች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ብዙ ርቀት ሄዶ እየሰራ መሆኑንን መንግስት አስታውቆ ይህን ውሳኔ እንደምያቀበል፣ የቀደመውን መላክም ትብብሩን ጥላሸት የሚቀባ፣ የአገር ሉአላዊነትን የሚንድ፣ የፖለቲካ መጠቀሚያ ሰበብ ሆኖ የቀረበና ፍትህ የተጓደለበት ማብራሪያ አቅርቧል።

መንግስት አብሮ ለመስራት ሲያስታውቅና ሲጎተጉት መኖሩን የኮሙኒከሽን አገልግሎት ዛሬ ማለዳ በሰጠው መግለጫ ይፋ ያድረገ ሲሆን፣በአማራና አፋር ሕዝብ ላይ ለመናገር በሚዘገንን መልኩ የተፈጸመውንና እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ገብተው እንዲታዘቡና እንዲያጋልጡ መንግስት በአደባባይ ጥሪ ሲያቀርብ እነዚህ ወገኖች ምላሽ እንዳልሰጡ በማብራሪያው ተመልክቷል። ” መርጦ አልቃሽ” ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ድርጅቱ ክብሩን እያታ መሆኑንን አስታውቋል።

“በውስጣዊ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት በመሆኑ ውሳኔውን በምንም መልኩ አልቀበልም” ሲል የመንግስትን አቋም ይፋ ያደረጉት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዳኤታ ሰላማዊት ካሣ፣ ውሳኔውንና የተኬደበትን አግባብ “ቀደም ሲል የነበሩ ግንኙነቶችንና ትብብሮችን የገፋ” ብለውታል። “ማን በፈተናችን ጊዜ ለኢትዮጵያ ከጎኗ ቆመላት? ማን ሲያሴርባት ነበር፣ የሚለውን ለይተንበታል” ሲሉም ሁሉም ለታሪክ እንደሚቀመጥ ጠቁመዋል።

“ታሪክ የሚዘግባቸው ወዳጅ አገራትን አይተናል፤ ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት እነዚህን ወዳጆች ከፍ አድርገው ያመሰግናሉ” ሲሉ ሚኒስትሯ አስታውቀዋል። አያይዘውም ” በችግር ጊዜ ያደረጉት ድጋፍ ዋጋቸው ውድ ያደርገዋል” በማለት ከኢትዮጵያ ጎን ለቆሙ አገራት ክብርን ሰጥተዋል።

ውሳኔውን የደገፉት አገራት 21 አገራት አርጀንቲና፣ አርሜኒያ፣ ኦስትሪያ፣ ባሃማስ፣ ብራዚል፣ ቡልጋሪያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ዴንማርክ፣ ፊጂ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ የማርሻል ደሴቶች፣ ሜክሲኮ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖላንድ፣ ኮሪያ ሪፐብሊክ፣ ዩክሬን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ኡራጓይ ናቸው።

የአፍሪካ አገራት ራሱ “ልዩ” የተባለውን ስብሰባ፣ እንዲሁም የውሳኔ ሐሳቡብ በጥቅሉ ተቃውመዋል። አካሄዱና መንፈሱ የንኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ክብረና የግዛት አንደነት ለአደጋን የሚጋብዝ መሆኑን ጠቃሰው በጥብቅ እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል። ተቃውሞ ያሰሙት አስራ አምስቱ አገራት ቦሊቪያ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ካሜሩን፣ ቻይና፣ ኮትዲቯር፣ ኩባ፣ ኤርትራ፣ ጋቦን፣ ሕንድ፣ ሊቢያ፣ ናሚቢያ፣ ፓኪስታን፣ ፊሊፒንስ፣ ሩሲያ፣ ሶማሊያ እና ቬንዙዌላ መሆናቸው ታውቋል። ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉት 10 አገራት ደግሞ ባህሬን፣ ባንግላዲሽ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ማላዊ፣ ሚሪታኒያ፣ ኔፓል፣ ሴኔጋል፣ ሱዳን፣ ቶጎ እና ኡዝቤክስታን ናቸው።

ከስብሰባው ቀደም ብሎ ዓለም ዓቀፍ የታማኝነት ክብር የተሰጠው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ይህ አካሄድ እንደሚያሰጋውና አደገኛም ሊሆን እንደሚችል ” ወደ ተግባር እንግባ” በሚል ድጋፍ ጠይቆ በላከው ደብዳቤ ተመድን ጠይቆ ነበር።

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብ አዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ምርመራና ግኝት ሪፖርት መሰረት በትግራይ ጂኖሳይድ ስለመፈጸሙ የታየ ምልክት አለመኖሩን፣ ረሃብን ለጦርነት የመጠቀም ጉዳይ አለመታየቱን ገልጾ ያቀረበው ሪፖርት ተቀባይነት ካገኘ በሁዋላ የአውሮፓ ህብረት ወደዚህ ህግ ማርቀቅ የገባበት ምክንያት አስገራሚ እንደሆነ ተመልክቷል።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ አፈ ቀላጤ አቶ ጌታቸው ረዳ ” አሜሪካ አዲስ አበባ ግቡ ብላናለች” በሚል ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይህ ወታደራዊ ሩጫ ሸዋ ሲዘልቅ አውሮፓም ሆነ አሜሪካ ዝምታን መርጠው በሌለኦች ተቋሞቻቸውና ሚዲያዎች አማካይነት መንግስት ሊወድቅ እንደሆነ ያስተጋቡ ነበር። ዲፕሎማቶችና የውጭ አገር ዜጎች ከነተቋማቸው አዲስ አበባን ለቀው እንዲወጡ ሲጎተጉቱ ነበር። የትህነግ ታጣቂዎች አዲስ አበባ ዙሪያ አርባ ኪሎሜርት እንደሚገኙ፣ አዲስ አበባ ያሉ የኤፒ ጋዜጠኞችም መቶ የሚሆኑ የኦነግ ሸኔን ሃይሎችን ስልጠና ሲያደርጉ የሚያሳይ ቪዲዮ ከቃለ ምልልስ ጋር አድርገው አሰራጭተው እንደነበር ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ውጪ እንዲኮበልሉ እግረመንገዳቸውን ጫና ሲፈጥሩ የነበሩት አሜሪካኖች ያሰቡት እንዳልተሳካ ሲያረጋግጡ አዲስ ዘመቻ መጀመራቸው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ነው ይህ ረቂቅ ከአውሮፓ የቀረበው። የሕዝብ አንድ መሆን ወረራውን ከመመከት አልፎ ቀዳዳ የዘጋ በመሆኑ በዚህ መልኩ ለመምጣት መሞከሩን ባለሙያዎች እያወገዙት ይገኛሉ።

በትግራይም ሆነ በመላው አገሪቱ የሚፈጸሙና የተፈጸሙ ወንጀሎች በእኩል ደረጃ ፍትህ እንደሚያሻቸው በርካቶች ያምናሉ። የሚታየው ግን ያንን አያሳይም። መንግስት እንዳለው ” መርጦ ማልቀስ” ነው።

መንግስት ዛሬ እንዳስታወቀው በተቋምም ሆነ በግል የተፈጸሙትን ወንጀሎች ለማጣራት ለሚመጡ ተባባሪ ነው። ይህ በንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ በክልሉ ህጻናት እንዳይከተቡ፣ ተመላላሽ የስኳርና የደም ግፊት በሽተኞች መደበኛ ክትትል እንዳይደረግላቸው፣ ህጻናት እንዳይከተቡና ለወረሽኝ እንዲሁም ለተላላፊ ህመም እንዲዳረጉ መደረጉ በአማራ ላይ ከጦርነቱ ጋር የተያያዘ ስልታዊ ጂኖሳይድ መሆኑንን ጠቅሰው በአሃዝ የተደገፈ መረጃ አቅርበዋል።


Exit mobile version