ETHIO12.COM

በኢትዮጵያ የጉዞ ሰነድ “ኤርትራዊ ናቸው” ተብለው ከአገር የወጡትን በሙሉ መንግስት እንደሚያውቃቸው ገለጸ፤

የኤርትራ ስምና ዜግነት ይዘው በኢትዮጵያ የጉዞ ሰነድ ወደ ውጭ የወጡ የትግራይ ዴያስፖራዎችን መንግስት ሙሉ በሙሉ ለይቶ አንደሚያውቅና በበቂ ደረጃ የተደራጀ መረጃ እንዳለው አስታወቀ። የሚገቡትንም ሆነ የሚወጡትን የሚከታተለበት ስራአት ማዘጋጀቱንም ይፋ አደረገ። አንድ ሻንጣ ለአገር በሚለው መርህ መሰረት ወደ አገር ቤት የሚገቡ ወገኖች ይዘው የመጡትን የሚያስረክቡበት ጣቢያ በግልጽ በአውሮፕላን ማረፊያ መዘጋጀቱም ተመለከተ።

ዛሬ በአምባሳደር ዘነበ ዘለቀ አማካይነት በተዘጋጀ የዙም ስብሰባ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ከበደ፣ የኢሚግሬሽንና ደህነት ሃላፊው አቶ ታምራትና የዲያስፖራ ኤጀንሲ መሪ ዶክተር መሐመድ እና ዶከተር ማርታ ንግግር አድርገው ነበር። ጥያቄ ቀርቦላቸው ምላሽም ሰጥተዋል።

ከሄልሲንኪ እንደሆነች የገለጸች ጠያቂ “በርካታ የትግራይ ተወላጆች ኤርትራዊያን ስደተኞች ( የተባበሩት መግስታት ስደተኞች ድርጅት) በሚሰጠው መታወቂያ “ኤርትራዊ ናቸው” ተብሎ፣ በወቅቱ የነበረውን አሰራርና ሃላፊዎች በመጠቀም ወደውጭ አገር የሄዱ፣ ውጭ አገር ሆነው በኤርትራዊነት የፖለቲካ ጥገኝነት ያገኙ፣ በዲያስፖራ ስም ሲገቡ የሽብር ሃይሎችን ዳግትም በገንዘብና በአንዳንድ ቁሳቁስ የማደራጀት ተግባር እንዳይፈጸም ምን ጥንቃቄ ተደርጓል” ስትል የስደት ካምፖቹን ስም በመጥራት ጠይቃ ነበር።

አቶ ታምራት ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳይገቡ “በኢትዮጵያ የጉዞ ሰነድ ከአገር ቤት የወጡትን በሙሉ እናውቃቸዋለን። የተደራጀ መረጃና አሰራር ስለተዘረጋ ስጋት አይግባችሁ” ብለዋል። መንግስት ባደረገው ጥሪ መሰረት ለገና ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የዲያስፖራ እንግዶችን በሚገባው ከማስተናገድ በተጨማሪ የድህንነት ስጋት ከቶውንም እንደማይታሰ አቶ ታምራት አመልክተዋል። ከዜናው መረዳት እንደተቻለው መንግስት የሚያውቀው መረጃ ቢኖርም፣ በወቅቱ ሆን ተብሎ ይህ መፈጸሙ ቢታመንም። ለዝግጅት ሲባል መረጃው በአንድ ቋት ሆኖ ሊሸሸግ በማይችል መልኩ እንዲቀመጥ ከማድረግ በዘለለ ሌላ ተንኮል የታሰበ እንዳልሆነ ከሃላፊው ስሜት መረዳት ይቻላል።

በትውልድ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ የዲያስፖራ አባላት አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኮቴ ግብር እንደማይከፍሉ አቶ ታምራት ይፋ አድርገዋል። ይህም ለአንድ ወር እንደሚቆይ አመልክተዋል። ዲያስፖራው በሰፊ ቁጥር ወደ ኢትዮጵያ እየገባ በመሆኑ ለብቻው እንዲስተናገድ የተለየ ካውነተር መዘጋጀቱም ተመክቷል።

“ትኬት አልቋል” በሚል አውቀው ጉዞ ለማስተጓጎል ወሬ የሚያናፍሱ ስለመኖራቸው ተጠይቆ፣ ከአሜሪካ ሰፊ ቁጥር ያለው ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ እየጎረፈ መሆኑ፣ ከአውሮፓም አሁን ላይ ቁጥሩ እየጨመረ ቢሆንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁሉንም ለማስተናገድ ተግቶ እንደሚሰራ፣ የሚወራው ወሬ ሃሰት እንደሆነ ድ/ር መሓመድ አመልክተዋል።

ዶክተር ሊያ ከበደ በበኩላቸው በአማራና አፋር ክልል ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮችና የጤና ተቋማት መውደማቸውን አመልክተው አንድ ሻንጣ ለአገር በሚለው መርሃ መሰረትም ሆነ በልዩ አግባብ ወገኖቻቸውን ለመርዳት ዝግጅት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ለርዳታ የሚመጡ ቁሶችን ወዲያውኑ የሚረከበ ከተርሚናሉ በፊት ኬላ ወይም የመረከቢያ ነጥብ መዘጋጀቱን ደግሞ ዶክተር ማርታ አስረድተዋል።

በዙም በተደረገ ስብሰባ የጉዞ ዶክመንት የሌላቸው ወይም ወደ አገራቸው ለመግባት ሰነድ ያላሟሉ ከጊዚያዊ የመጓጓዣ ሰነድ ጀምሮ አስፈላጊው ወገናዊ እርዳታ እንደሚደረግ ተመልክቷል። ተጨማሪ መረጃ በኢምግሬሽን መስሪያ ቤት ድረ ገጽ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል።


Exit mobile version