ETHIO12.COM

ትህነግ አሜሪካን በተመድ በኩል “ቃልሽን ፈጽሚ” ሲል ደብዳቤ ጻፈ፣ አየር ክልሌን ጠብቁልኝ አለ፣ ጥምር ጦር አላማጣን ያዘ

“አራተኛው ቃል ትህነግ ካልተሳከላተና የሚጨነፍ ከሆነ የኢትዮጵያ ሃይሎች ወድ ትግራይ እንዳይገቡ እናደርጋለን የሚል ቃል ስለተገባላቸው ለተውጊዎቻቸው ይህን ቃል ገብተው ነው” የሚል እንደነበር ዶክተር ዳኛቸው ከወር በፊት ገልጸው ነበር። “አሁን ዶክተር ደብረጽዮን የጻፉት ደብዳቤ የአራተኛውን ውል ቃላችሁን ፈጽሙ እንደማለት ነው። ይህ ካልሆነና የኢትዮጵያ ጥምር ሃይል መቀለ ከገባ ግጭቱ ከሸወዱት የትግራይ ሕዝብ ጋር ይሆናል። አቶ ጌታቸውን አሜሪካ አዲስ አበባ ግቡ ባላን ነው ማለታቸውን መዘንጋት አያስፈልግም። በዚህ ስሌት መከላከያ መቀለን ከተቆጣጠረ አዲሱ ጨዋታ በህዝብና በሸዋጁ ትህነግ መካከል ይሆናል። ቁሉፍ የጩኸቱ መነሻ፣ የድብዳቤው ሚስጢር ይህ ነው” ሲሉ አስተየት የሰጡ አስታውቀዋል


ከአንድ ቀን በፊት እንደ ማርቲን ፓላውት ” የሰላም ድርድር ይሸተናል” ሲሉ ምንም የሰሙት ጉዳይ እንደሌለ አመልክተው በቲውተር ገጻቸው ማሰራጨትና መቀባበል ጀመሩ። ይህንኑ ሃሳብ ነገሩ የገባቸው በተኑት። ሃያ አራት ሰዓት ሳይሞላ እሁድ ደብረጽዮን ትግራይ ከበረራ ክልል ነጻ እንደትሆን የሚጠይቅ ” የድርሱልን” ጥያቄ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት መላካቸውን እንዚሁ ክፍሎች አስታወቁ። ይህ ሁሉ ሲሆን የጥምር ሃይሉ ጥቃቱን አተናክሮ አላማጣን ተቆጣጥሮ ወደፊት እየሄደ መሆኑ እየተገለጸ ነው።

Habesha News - ጀግናው የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመቐለ ያሉ የተመረጡ ወታደራዊ... | Facebook
የኢትዮጵያ አየር ሃይል

የትህነግ ወራሪ ሃይል መሪ የሆኑት ዶክተር ደብረጽዮን በደብዳቤያቸው ለሲቪል አገልግሎትና ለእርዳታ አቅርቦት ከሚደረጉ በረራዎች ውጪ ትግራይ ከበረራ ነጻ ክልል እንዲደረግና በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲጣል ለተባበሩት መንግስታት ጥሪ አቅርበዋል። ራሳቸውን እንደ አገር ቆጥረው የተባበሩት መንግስታትን በር እንዳሻቸው የሚከፍቱላቸውና የሚዘጉላቸው ወገኖች ተጠቅመው ላቀረቡት ጥያቄ፣ ጥያቄው የቀረበላቸው ወገኖች በይፋ ያሉት ነገር ባይኖርም የሱዳን ኮሪዶር እንዲከፈት ግን ከመወትወት ቦዝነው አያውቁም።

” የሽንክርቱ የመጨረሻ ልጣጭ” የተባለው ” የሰላም ድርድር” ተግባራዊ እንዲሆን የትግራይ ሃይሎች ታዘው ያለ ውጊያ የአማራና የአፋር ክልልን እንደለቀቁ ደብረጽዮን ” አዝዤ” ሲሉ በድብዳቤያቸው መግለጻቸው ጠቅሰው “ወዳጅ” ሚዲያዎች ጽፈዋል። እነዚህ ሚዲያዎች መንግስትና የአማራና የአፋር ክልሎች ላይ የደረሰውን ግፍና ውድመት በነጻነት ገብተው እንዲዘግቡ ጥሪ ቢደረግላቸውም እሳክሁን በይፋ ጥሪውን ተቀብለው ዝርዝር ሪፖርት ለማቅረብ ሃይል ስለማሰማራታቸው ምንም አልተሰማም። በመንግስት ሚዲያዎች በፊልም ተድግፈው የሚቀርቡ ዘግናኝ ሪፖርቶችን ጆሮ ዳባ ብለዋቸዋል።

ክስጋት በመነጨ “ትግራይ የአየር ክልሏ ላይ ማንኛውም በረራ እንዳይደረግ፣ ከበረራ የታገደ ክልል አድርጉልን” ሲሉ ዛሬ በይፋ የትህነጉ መሪ ቢማጸኑም።፣ቀደም ባሉት ጊዚያት አቶ ጌታቸው ድሮንን “አሻንጉሊት” በማለት የትግራይን ክልል ዘልቆ የሚገባ አንዳችም የአየር ላይ መሳሪያ እንደማይኖር በተደጋጋሚ ሲያስታወቁ ነበር። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አዛዥ ጄነራል ይልማ መርዳሳ ” ደጋግማችሁ አስቡ። ከቀጣን ሁለተኛ እንዳይለመድ አድርገን ነው” የሚል ማሳሰቢያ ይሰጡ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ” የክላሽ ጦርነትን አታስቡ። ኋላ ቀር ጦርነት አትገምቱ” ብለው መክረው እንደነበር መናገራቸው ይታወሳል።

በትግራይ ከመቀለ ብዙም በማይርቅ ስፍራ፣ መሶበ ሲሚንቶ አካባቢ ጉዳብ ላይ የአየር መቃወሚያ ለመትከል ሙከራ እየተደረገ ሳለ ገና ከጅምሩ አየር ሃይሉ ወደ ዓመድነት ቢለውጠውም፣ ከአየር ሃይሉ ቁመና አንጻር ጥቃቱ ኢመንት በመሆኑ ዝም እንደትባለ በሌላ አጋጣሚ ላይ ተጠቁሞ ነበር። የአየር ሃይል፣ መከላከያ፣ የአፋርና አማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻ፣ ሕዝብና ፋኖ ተጣምረው በሁሉም አቅጣጫ ከበው የትህነግን ወራሪ ሃይል ክፉኛ እንደጎዱት እጃቸውን የሰጡ ” በተአምር ተርፈናል” ሲሉ መመስከራቸው ይታወሳል። በርካታ የምስል መረጃዎችም እየወጡ ነው። ወልደያና በርካታ ከተሞች በሃይል ነጻ መውጣታቸው ከተገለጸ በሁዋላ “ለሰላም ሲባል ወታደሮቻችንን ከአፋርና ከአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ አስወጥተን ጨርሰናል” ሲሉ አቶ ጌታቸው ለሮይተርስ ተናግረዋል። ሮይተርስም የሚፈትን ጥያቄ ሳያቀርብ አልፏል። ድብድቤውም የተጻፈው መንግስት የመጀመሪያ ዘመቻውን አጠናቆ ሙሉ የሰሜን ወሎን ማጽዳቱን ካስታወቀ በሁዋላ ነው።

ትህነግ የሰላም ድርድር ሲጠይቅ እንደዚህ ያሉትን በደሎች እንዴት ፍትህ እንደሚያገኙ አላመለከተም

አየር ሃይል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን በተዘዋሪ መንገድ ያመነው የትግራይ ወራሪ ሃይል አመራር ” ትግራይ ከበረራ ቀጣና ውጪ ትሁንልን” ሲሉ ላቀረበው ጥያቄ እስካሁን በይፋ የተሰጠ መልስ የለም። ይሁን እንጂ ትህነግ ሙሉ በሙሉ መክሰማያው ሲደርስ ይህ ጥሪ መቅረቡ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል። “ቃል እንደገባሽው ቃልሽን ጠብቂ” የሚመስለው ደብዳቤ ዝም ብሎ የተጻፈ እንዳልሆነ ብዙ ምልክቶችም አሉ። የሰላም ንግግር ተስፋ ስላለ አሜሪካ የጂኖሳይድ ክስ እንደምታነሳ ካስታወቀች በሁዋላ ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ኢትዮጵያ ሃይሎች ማመዘኑን ተንተርሶ የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ገለልተኛ ምርመራ እንዲያደርግ አስቀድሞ መወሰኑ አሁን ትህነግ እየጮኸበት ያለውን የሰላም ድርድር ጥያቄ መንግስት እንዲቀበል ማስገደጃ እንዲሆን ታስቦ መሆኑ እየተገለጸ ነው።

የጦር ሜዳ ሽንፈቱ ግልጽ እየሆነ ሲመጣ የአውሮፓ ህብረት አርቅቆ ያቀረበው ህግ ገና ከጅምሩ የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ በመሆኑ እንደማትቀበለው ኢትዮጵያ ማስታወቋ፤ ሙሉ የአፍሪካ አገሮች አንድ ረቂቁን መቃወማቸው ልዩ ትርጉም እያሰጠው ባለበት ወቅት ትህነግ ሃይሉን በወረራ ከያዝቸው ቦታዎች ማስወጣቱ እንደ ከሽብፈቱ በላይ ገኖ መነገሩ ሌላ መነጋገሪያ ሆኗል።

የአሜሪካንን ሚዲያዎ፣ መረቦች፣ ተላላኪዎችና ባለስልታናትን፣ የአውሮፓ ውስን አገሮችን ሴራ ከትህነግ ጋር አንድ ላይ የመከተው የኢትዮጵያ መንግስት፣ ባገኘው ድል ሃፍረት ውስጥ የገቡት ዲፕሎማቶችና አሜባሲዎች ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሱ ነው። የተባበሩት መንግስታትም በይፋ አገሪቱ ሰላም መሆኗን አምኖ እገዳ የታለባቸው ሰራተኞቹ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ማዘዙን አስታውቋል። ትህነግ እንደሚሸነፍ፣ ኢትዮጵያን ሊቋቋም እንደማይችል፣ ይህንንም ተከትሎ የአቋም ለውጥ እንደሚከሰት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ገልጸው ነበር። “ትህነግ አዲስ አበባን ከቧል” እየተባለ በሚዘገብበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” ለምነው እንግባ ይላሉ” ሲሉ አስታውቀው ወደ ዘመቻ በማማራት በሁለት ሳምንት ውስጥ ነገሮች ተቀይረዋል። ገና ለዘመቻ ሲወጡ የተቿቸው የትህነግ ሰዎች አሁን ” ለሰላም ሲባል ለቀን ወጣን” ከማለት ውጭ ሌላ ያሉት የለም።

ደብረጽዮን ሃይላቸው ከነ ሙሉ አቅሙ ወደ ትግራይ መመለሱን ሲያስታውቁ አቶ ጌታቸው በሽንፈት ዳርዳርታ ወቅት ” ስንፈልግ ዳግም እንይዛለን” ሲሉ እንደነበረው በዶክተር ደብረጽዮን ደብዳቤ አልተገለጸም። የትህነግ መሪ የሰላም ድርድሩ “ወዲያው ተግባራዊ” እንደሚሆን ተስፋቸውን ጠቁመው በአስቸኳይ ግጭቶች ቆመው ድርድር ሊጀመር እንደሚገባ አመልክተዋል።

መንግስትም ሆነ ደብዳቤው የተጻፈለት የተባበሩት መንግስታት እስካሁን የመለሱት ምላሽ የለም። ትህነግ የሰላም ጥያቄ እያቀረበ በአፋር በኩል ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሮ እንደነበርና እንደተመከተ አፋር ሃይሎችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

አቶ ጌታቸው በቲውተር መልዕክታቸው ኤርትራንም እንደሚፈሩ አስታውቀዋል። የኤርትራን ስም ደጋግመው በመጥራት እየወተወቱ ያሉት አቶ ጌታቸው በቀጥታም ባይሆን ጣልቃ ገብነትን እየለመኑ ነው። በውጭ ሃሎች ላይ ጥገኛ እንደሆነ የሚነገርለት ትህነግ በቀናት ውስጥ ምን ሊገጥመው እንደሚችል ባይታወቅም በአካባቢው የሚሆነውን ቅርብ ሆነው የሚከታተሉ እንዳሉት የኢትዮጵያ ጦር ትግራይን ዘልቆ እየገባ ነው። “አሁን በጥድፊያ የሰላም ድርድሩ ጥያቄና “የድረሱልን” ለቅሶ የዚሁ ውጤት ሊሆን እንደሚችል እናምናለን፤ ለሁሉም ግን የጥምር ሃይሉ አላማታን ተቆጣጥሮ ወደፊት እየሄደ ነው” ሲሉም አስተያየት ሰጥተዋል።

ትህነግ ገና ከጅምሩ እርቅ እንዲቀበል የአገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች ተንበርክከው፣ ታዋቂ ሰዎችና ወዳጅ የተባሉ አገሮች ሲጠይቁት ያከማቸውን መሳሪያና ያደራጀውን ሃይል በመተማን እንደማይቀበል ሲያስታውቅ መቆየቱ ይታውሳል።


Exit mobile version