Site icon ETHIO12.COM

ጻድቃን ዋናውን ጉዳይ አፈነዱ፤ የአሜሪካ ማስተባበያ ይጠበቃል

መንግስት በአሸባሪነትና በጦር ወንጀለኛነት ” እፈልጋቸዋለሁ” ከሚላቸው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ጻድቃን ገብረትንሳይ ሃይላቸው አዲስ አበባ መድረስ ያልቻለበት ዋና ምክንያት ምን እንደሆነ ይፋ አደረጉ። ሰራዊቱ አሁንም ከትግራይ ክልል ውጪ የያዛቸው በኦታዎች እንዳሉ በመናገር መንግስት በየቀኑ በሃይል እያስለቀቀ ለመሆኑ ማረጋገጫ ሆኑ። እንደተለመደው አሜሪካ ማስተባበያ ትሰጥበታለች ተብሎ ይገመታል።

በቢቢሲ የኒውስ አወር ክፍለ ጊዜ ላይ የቀረቡት የቀድሞ ኤታማዦር ሹምና የአሁኑ “ወራሪ የሃይል” የሚባለው የትግራይ ታጣቂ መሪ ” ወደ አዲስ አበባ በምንገሰግስበት ጊዜ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሂደቶች ከወታደራዊ አካሄዳችን ጋር ሊጣጣሙ አልቻሉም። የዲፕሎማቲክ ሁኔታዎች በሚፈለገው መልኩ እየሄዱ አልነበሩም። ይህም አንድ ምክንያት ነበር። ሲሉ ተሸንፈውና የድሮን ጥቃት መቋቋም ተስኗቸው ማፈግፈጋቸውን አስመልክቶ ለተጠየቁት መልስ ሰጥተዋል።

” ወደ አዲስ አበባ በምንገሰግስበት ጊዜ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሂደቶች ከወታደራዊ አካሄዳችን ጋር ሊጣጣሙ አልቻሉም። የዲፕሎማቲክ ሁኔታዎች በሚፈለገው መልኩ እየሄዱ አልነበሩም። ይህም አንድ ምክንያት ነበር” ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው ቢያልፈውም፣ ቃለ ምልልሳቸውን የተከታተሉ ወዲያውኑ ሃሳቡ ግልጽና የማያሻማ መሆኑንን አመልክተዋል። ሲያብራሩም ” የዲፖሎማቲክ ሁኔታዎች በሚፈለጉት አልሄደልንም” ሲሉ ትህነግ አዲስ አበባ ዙሪያ አርባ ኪሎ ሜትር ላይ መድረሱን በጨበጣ ሲያስታውቁና የዲፕሎማቲክ ሰራተኞች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ሰራተኞችና አምባሳደሮች ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ፣ከዚህ ዘመቻ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አገር ለቀው እንዲወጡ አሜሪካ ስታደርግ የነበረው ጫና ዳር አለመድረሱን ለሃሳባቸው መጨናገፍ ዋና ምክንያት መሆኑንን መግለጻቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

የትህነግ መሪዎች ” ነገሩ አልቋል። የምታድኑት ከተማም ሆነ አገር የለም። እጃችሁን ስጡ” እያሉ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ፣ ጻድቃን ” ከማን ጋር ነው ድርድሩ” በማለት መንግስት እንደወደቀ ሲናገሩና አቶ ጌታቸው ” ስለ አዲስ መንግስት ምስረታና ስለብልጽግና አመራኦች ፍርድ ሲትቱ፣ የትህነግ ደጋፊዎች ከበሮ ጸሃይ ላይ አስጥተው ለጭፈራ ሲዘጋጁ እንደነበር በሚገልጽበት ቅጽበት የታየው አስገራሚ የነገሮች መለዋወጥ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ይዞ እየመጣ ለመሆኑ የጻድቃን ቃለ ምልልስ አመላካች ነው። አቶ ጌታቸው ረዳ ቀደም ሲል ” አሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ግቡይ ብላናለች” ከማለታቸው ጋር ጻድቃን ከወታደራዊ ሩጫው ጋር የዲፖላቲክ አካሄዱ አለመጣጣሙን ሲያክሉበት ጎልታ የምትወጣዋ አሜሪካ እንደሆነች አስተያየት የሚሰጡት አመልክተዋል።

በአሜሪካ መንግስት ዕውቅና የተሰጣቸው ትህነግ የሰበሰባቸው ዘጠኝ ምናቸውም የማይታወቅ ድርጅቶች መግለጫና ቅንብረና የኢትዮጵያን መሪዎች ቪዛ አመቻችቶ አገር ለቀው እንዲወጡ ሲደረግ የነበረው ጫና በተወሰኑ አቅመ ቢሶች ተቀባይነት አግኝቶ እንደነበር የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ታዬ ደንደአ ማመልከታቸው ይታወሳል። ሆኖም ግን ኈትና ሶስት ናቸው የተባሉትን ባለስልጣኖች በስም አላነሱም።

ደጋግማ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ስትጠይቅና የኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጠውን መንግስት ስለመናድ በግልጽ ስትሰራ የነበረቸው አሜሪካ የትህነግ ሃይል ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ መግፋቷን ለዚሁ ተግባር በተቋቋመው የቪኦኤ አማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ክፍለ ጊዜ ማስተባበሏ የሚታወስ ነው። አሁንም ጻድቃን ስም ሳይጠቅሱ የዲፖላማቲክ ስራው ከሰራዊታቸው አካሄድ ጋር አለመጣጣሙን ሲያስታውቁ መግልጽ አሜሪካ አስገድዳ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይን ከአዲስ አበባ አለመፈንቀሏን ለማመላከት መሆኑ ተመልክቷል።

በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጦር ሜዳ ገብተው ከጦር መኮንኖቻቸው ጋር በመሆን አመራር በመስጠት በሁለት ሳምንት ውስጥ በወረራ ሸዋ ደርሶ የነበረው ሃይል ከሞት፣ ከጥይትና ከምርኮ የተረፈው ወደ መዳረሻውን ትግራይ እንዲያድርግ ሆኗል። ይህንኑ ተከትሎ ሽንፈት ሳይሆን ” ለሰላም እድል ለመስጠት ሲባል” በሚል የትግራይ ሃይሎች ወደ ትግራይ እንዲገቡ መደረጉ በትህነግ በኩል ተገልጿል። ይህንኑ ተከትሎ አስቸኳይ የተኩስ አቁምና የሰላም ንግግር እንዲጀመረ ትህነግ ጠይቋል።

ጻድቃን በቃለ ምልልሳቸው ለደህንነት ሲባል ሃይላቸው ከትግራይ ውጪ እንዳለ ” የተወሰኑ አሁንም ወደ ትግራይ እየተመለሱ ያሉ ተዋጊዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ለደኅንነት ሲባልም እዚህም እዚያም እንዲቆዩ የተደረጉ አሉ” ሲሉ አመልክተዋል። ይህ ገለጻቸው የጥምር ሃይሉ በየጊዜው በሃይል እየደቆሰ በወረራ የተያዙ ቦታዎችን ነጻ እያወጣ መሆኑንና አሁንም በቀጣይ ማጥቃቱን እንደቀጠል ለሚሰጠው መረጃ ምስክር የመሆን ያህል እንደሆነ ተገልጿል። ” የትግራይ ሃይል ሙሉ ለሙሉ ትግራይ ገብቷል” በተባለ በሁለተኛው ቀን ” የተወሰኑ አሁንም ወደ ትግራይ እየተመለሱ ያሉ ተዋጊዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ለደኅንነት ሲባልም እዚህም እዚያም እንዲቆዩ የተደረጉ አሉ” ሲሉ ጻድቃን መናገራቸው እርስ በርሱ የሚጣረስ እንደሆነም ተገልጿል።

ከወር ተኩል በፊት ” ባለ ምጡቅ አዕምሮ” ሲል ቢቢሲ ያነገሳቸው ጻድቃን “ግዙፍ ሠራዊታችንን በስንቅና ትጥቅ ሙሉ ለማድረግ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ረዥም ርቀት በሚጓዙበት ጊዜ ለድሮን ጥቃት ተጋልጠው ቆይተዋል። በዚህም ድሮኖቹ በግብአት አቅርቦታችን ላይ ተጽእኖ ፈጥረዋል” ሲሉ በተደጋጋሚ ድጋፍ ሰጪ ሃሎች ከትግራይ ሲነሱ በድሮን መደምሰሳቸውን ሲገልጽ ለነበረው የመንግስት ሃይል እምኝ ሆነዋል። በዚያው መጠን ልጆቻቸው ወደ ወረራ ለዘመቱባቸው ቤተሰቦች መርዶ ነግረዋል።

ቢቢሲ ያነሳው የወቅቱ መነጋገሪያ ጉዳይ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መጠላት ጉዳይን ነው። ” ህወሓት በ30 ዓመት የሥልጣን ቆይታው የተነሳ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ በጎ ስም የሌለው፣ወንጀለኛና የሚያስፈራ፣ መሸነፍ ያለበት ድርጅት ነው” ሲል በጥያቄ አንስቷል። ጻድቃን ጦርነቱ የትግራይ ህዝብ የምቢ ባይነት ጦነት መሆኑንን ጠቁመው በተቋቋመው ገለልተኛ መርማሪ የሚጣራ ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል። አክለውም ኤርትራን ከሰዋል። ለአንድ ቀጣይ ሚሽን የተዘጋጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

አሜሪካ ለምስራቅ አፍሪቃ የመደበቻቸው በላሟሏ ፌልስት ማን ” ሰዎቹ 1991 ላይ ናቸው። አዲስ አበባ መግባት አትችሉም ብለናቸዋል” ሲሉ ነገሩ ከከሸፈ በሁዋላ መናገራቸው ይታወሳል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርም ” ትህነግን ደጋፌ አላውቅም” ማለቷ አይዘነጋም። ለስር ቃለ ምልልሱን እንዳለ ቢቢሲ ተርጉሞ ያቀርበውን አትመነዋል።

ቢቢሲ ኒውስ አወር በአሁኑ ጊዜ በጦርነቱ ዙሪያ የታየውን ለውጥ እንዴት ይገልጹታል?

ጄነራል ጻድቃን፡ በአሁኑ ጊዜ አብዛኛው ሠራዊታችን በሕገ መንግሥቱ በተረጋገጠው የትግራይ ግዛት ውስጥ ነው ያለው። የተወሰኑ አሁንም ወደ ትግራይ እየተመለሱ ያሉ ተዋጊዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ለደኅንነት ሲባልም እዚህም እዚያም እንዲቆዩ የተደረጉ አሉ። ዞሮ ዞሮ አብዛኛው ሠራዊታቸን ትግራይ ውስጥ ነው። ልብ ሊባል የሚገባው ይህንን ፖለቲካዊ ውሳኔ የወሰንነው መላው ምዕራብ ትግራይ በኤርትራና በኢትዮጵያ ሠራዊትና በአጋሮቹ ኃይሎች ተይዞ ሳለ ነው።  የተወሰኑ የኢሳያስ ወታደሮችም በተወሰኑ የሰሜን ትግራይ አካባቢዎች እንዳሉ ናቸው። የኤርትራ ኮማንደሮች አንዳች አይነት ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እያቀዱ ነው። የኤርትራ መኮንኖች የኢትዮጵያን መካናይዝድ ኃይል እየመሩ ነው ያሉት። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ኃይሎቻችንን ለማስወጣት ወስነን አብዛኞቹን አስወጥተን ወደ ትግራይ የመለስነው ለሰላም ዕድል ለመስጠት ነው።

ቢቢሲ ኒውስ አወር፡ ጄኔራል ጻድቃን ይህ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው ብለዋል። ብዙ ሪፖርቶች የሚያሳዩት ግን ተሸንፋችሁ ማፈግፈጋችሁን ነው። በተለይም የድሮን ጥቃት መቋቋም አለመቻላችሁ ነው ወደ ትግራይ እንድትመለሱ ያደረጋችሁ። አይደለም እንዴ?

ጄነራል ጻድቃን ፡- ያ አንድ ምክንያት አይደለም አልልህም። ነገር ግን ብቸኛው ምክንያት አይደለም። ወደ አዲስ አበባ በምንገሰግስበት ጊዜ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሂደቶች ከወታደራዊ አካሄዳችን ጋር ሊጣጣሙ አልቻሉም። የዲፕሎማቲክ ሁኔታዎች በሚፈለገው መልኩ እየሄዱ አልነበሩም። ይህም አንድ ምክንያት ነበር።

በተለይ ግዙፍ ሠራዊታችንን በስንቅና ትጥቅ ሙሉ ለማድረግ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ረዥም ርቀት በሚጓዙበት ጊዜ ለድሮን ጥቃት ተጋልጠው ቆይተዋል። በዚህም ድሮኖቹ በግብአት አቅርቦታችን ላይ ተጽእኖ ፈጥረዋል።

ቢቢሲ ኒውስ አወር፡ የፌዴራል ኃይሎች ጥምረት በምዕራብ ትግራይ፣ የኤርትራ ሠራዊት በሰሜን ትግራይ አለ ብለውኛል። እንደዚያ ከሆነ ለምን እዚያ ላይ አላተኮራችሁም? አዲስ አበባ ለመገስገስ ምናልባት ጓጉታችሁ ይሆን?

ጄነራል ጻድቃን፡ አይደለም። ከመነሻው ግልጽ መሆን ያለበት ነገር አለ። አዲስ አበባን የመቆጣጠር ፍላጎት አልነበረንም። እርግጥ ነው ጦርነቱን በተቻለ ፍጥነት የማጠናቀቅ ጉጉት ነበረን። 

በእኛ አስተሳሰብ ወደ ደቡብ ዘመቻ በማድረግ፣ በዚያውም የፖለቲካ ጥምረቱን በተቻለ ፍጥነት በማቀናጀት መንግሥት ሁሉን አቀፍ ለሆነ ንግግር እንዲቀመጥ እናስገድደዋለን ብለን ነበር።

በዚህ መልኩ ጫና መፍጠር አቋራጭ ሆኖ ነበር የታየን። ይህን ብናደርግ ያለንበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያቃልልልናል ብለን ነበር የገመትነው።

ቢቢሲ ኒውስ አወር፡ ብዙ ጊዜ ስለ ሁሉን አቀፍ ንግግር ያነሳሉ። ህወሓት በ30 ዓመት የሥልጣን ቆይታው የተነሳ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ በጎ ስም የሌለውና የሚፈራ መሆኑ ላይ ምን ያህል ይስማማሉ? በቅርቡ ደግሞ በአፋርና በአማራ ክልል ውስጥ ወታደሮቻችሁ በፈጸሙት የጅምላ ግድያዎች፣ ሴቶችን መድፈርና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ምናልባትም የጦር ወንጀሎች የተነሳ ስማችሁ መልካም አይደለም። በዚህ የተነሳ አብዛኛው ኢትዮጵያ ህወሓት አስፈሪ ኃይል ስለሆነ መሸነፍ አለበት ብሎ በማመኑ ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ?

ጄነራል ጻድቃን፡ የትግራይ ጦርነት ለትግራይ ራስን የመከላከልና ጭቆናን እምቢኝ የማለት ሕዝባዊ ጦርነት ነው። በጄኔቫ የመርማሪ ቡድን ለማቋቋም ተወስኗል። ቡድኑ በመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም በእኛ ኃይሎች ተፈጽሟል ስለሚባለው ሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዙርያ ምርመራ እንዲያደርግ ነው የተቋቋመው። ያንን በጸጋ ተቀብለናል።  በአማራና በአፋር የእኛ ኃይሎች ስለፈጸሙት ጭፍጨፋዎች ጠይቀኸኛል። እንደተባለው ጥሰት ተፈጽሞ እንኳ ቢሆን በትግራይ ላይ የተፈጸመው ሰብአዊ ጥሰት እጅግ የከፋ ነው።  በኤርትራና በኢትዯጵያ ኃይሎች የተፈጸመው ሰብአዊ ጥሰት እጅግ ግዙፍና ዘግናኝ ነው። አሁን ማለት የምችለው በጄኔቫ የተወሰነው ውሳኔ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ነው። መጥተው ይመርምሩና ያን ጊዜ እንፍረድ


Exit mobile version