Site icon ETHIO12.COM

ጦርነቱ ካልቀጠለ ትህነግ በሁለት ምክንያቶች እንደሚከስም መገምገሙ ተሰማ

“በሱዳን በኩል የተቆለፈውን በር ማስከፈት ካልተቻለ፣ የውጭ ወዳጅና አጋዦች ጣልቃ የሚገቡበት ሁኔታ ካልተመቻቸ፣ ጦርነቱን መሸከምና መቀጠል ይከብዳል። በመካከሉ መንግስት ከአሜሪካ ጋር የሚግባቡበት ደረጃ ከተደረሱ የትህነግም ሆነ የትግራይ ጉዳይ የአሜሪካ አጀንዳ አይሆንም። አሜሪካ ከተወችን ሁሉም ይተውናል … “

ራሱን ለግማሽ ምዕተ ዓመት በተገንጣይ ስም የሚጠራው ትህነግ ጦርነቱ ካልቀጠለ በሁለት ምክንያቶች ሊከስምና ሊሞት እንደሚችል መገምገሙና ስለ ሰላም በመስበክ ጦርነቱን ለማስቀጠል መወሰኑ ተሰማ። በአንዳን አካባቢዎችና የድርጅት አመራሮች የተጀመረው አሽሙርና ንትርክ በርካታ የአማራ ተወላጆችን እንዳሳዘነ ተሰማ።

የአሜሪካ ተባባሪያችን የትህነግ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ መቀለ ያለውና በውጭ ያለው የድርጅቱ አመራር ጦርነቱ ካልቀጥለ የሞት እጣ ፈንታቸው የማይቀር ነው። እንደ ምክንያት ያቀረቡት ሁለት ጉዳዮችን ሲሆን አንዱ ከውጭ ያለውን ድጋፍ ሊከስም እንደሚችል ያመለከቱበት ሲሆን ሁለተኛው የውስጥ ጉዳይ ላይ ያለው እውነታ ነው።

በከፍተኛ ደረጃ በሰው ሃይል መመናመናቸውን ሳይሸሽጉ የተነጋገሩት የትህነግ አመራሮች ጦርነቱ የሚያቆም ከሆነ በትግራይ ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚጠብቃቸው ምልክት እንዳለ አመልክተዋል። መንግስትም ይህንን የተቃውሞ ዳርዳርታ እንደሚደግፍ ግልጽ በማድረጉ ችግሩ ሊገነፍል የሚችልበት አጋጣሚም ሊኖር እንደሚችል አውስተዋል። በውጭ ድጋፍ ሰጪ የነበረውም ሃይል ከማጉረምረም ባለፈ ጥያቄ እያነሳ ስለሆነ፣ ጻድቃን ” ለደህንነት ሲባል የትግራይ ሰራዊት በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰፍሯል” ሲሉ እንዳስታወቁት አሁንም “ምዕራብ ትግራይ” በሚባለው አቅጣጫ ትግራይ መወረሯን በማጉላት፣ የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ጥቃት ሊሰነዘርበት እንደሆነ በማሳመን እየተነሳ ያለውን ጥያቄ በፍርሃት ራስን ወደ መከላከል እሳቤ ብቻ እንዲቀይር ማድረግ የተመረጠው መንገድ መሆኑን ተባባሪያችን አመልክቷል።

የደጋፊዎቻቸውን ሞራል ለመጠበቅ ” የተሸነፍነው የድሮን ጥቃት መቋቋም ባለመቻላችን ነው” የሚለውን ዜና በእንግሊዝና አሜሪካ ሚዲያዎችና አጋሮቻቸው በተደጋጋሚ እንዲነሳና እስከ ተባበሩት መንግስታት ድረስ እንዲደርስ መደረጉ በታሰበው መጠን ድጋፍ ሊያስገኝ እንዳልቻለ በንግግራቸው መነሳቱ፣ አንዳንዴም እርስ በርስ የሚጋጩ መረጃዎች ከሃላፊዎች መውጣቱ ደጋፊዎችን እንዳደናበረና ለጠላት ፕሮፓጋንዳ እንዳጋለጣቸው በግምገማቸው አንስተዋል። ተባባሪያችን ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው አቶ ጌታቸው እየተቻኮሉ የሚያሰራጩትን መረጃ በቡድን በሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ተመስርተው እንዲያሰራጩም ተነግሯቸዋል።

ከውስጥ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል ከሚለው ቀጥሎ በስፋት ትኩረት የተሰጠው ” እኛ በግንባር እየዛልን ከሄድን መንግስት ከአሜሪካ ጋር የመስማማትና አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ልትገለበጥ የምትችልበት አጋጣሚ ሊመጣ ይችላል” የሚለው ጉዳይ ነው።

ከትህነግ ጋር ልዩ ፍቅር ስለያዛት ሳይሆን በአካባቢው የጂኦፖለቲካ የኤርትራ፣ ኢትዮጵያና ሶማሌ ህብረትና የቀይ ባህር ቀጣይ ፖለቲካ ያሳሰባት አሜሪካ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚመሩትን መንግስት ለመጣል ስትል ለትህነግ አይን ያወጣ ድጋፍ እንደምታደርግ በተደጋጋሚ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።

በዚሁ መነሻ ህዝብ ያባረረው ትህነግ፣ በሁለት ሳምንት ጥቃት የተደመሰሰው ትህነግ ዳግም የማንሰራራት እድል አግኝቶ አፋርና አማራ ክልልን ወሮ ወደ አዲስ አበባ እንዲያቀና አሜሪካ ፈቅዳና መመሪያ ሰጥታ እንደ ነበር አቶ ጌታቸው መናገራቸው ይታወሳል። ይህ ንግግር አሜሪካንን ያስቆታ እንዲመስል ተደርጎ ” ትህነግን አግዘን አናውቅም” የሚል ምላሽ እንዲሰጥበት መደረጉም የሚታወስ ነው።

ጻድቃን ከቢቢሲ አፍሪካ ክፍለ ጊዜ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ ” ሕዝብ አይወዳችሁም” ከመባላቸው በተጨማሪ አዲስ አበባ የመግባት ነገር እንዴት እንደከሸፈባቸው ሲጠየቁ ” የዲፕሎማሲው ስራ ከእኛ ሩጫ እኩል አልሄደም” ሲሉ አሜሪካ ዶክተር አብይን ነቅላ ወደ ባህሬን አለመላኳ የቤት ስራዋን እንዳልሰራች አድርገው የማቅረብ መሆኑ ተመልክቷል።

የትህነግ የውስጥና የውጭ አመራሮች እንዳሉት በምዕራብ በኩል ” ተወረናል” በሚል ተጋድሎ ካላደረጉና ውጤት ሳያዝመዘግቡ ጊዜ ከፈጁና መንግስት ልዩነቱን በንግግር ከአሜሪካ ጋር ሊፈታ የሚችልበት አግጣሚ ከተፈጠረ እስከነ አካቴው ከጨዋታ ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገምገማቸውን በሁኔታው ከተበሳጩ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ተባባሪያችን አመልክቷል።

መንግስት ወደ ትግራይ ላለመግባት የውሰነው ውሳኔ አሉታዊ ውጤትም እንዳለው በግምገማው ተመልክቷል። በጣልቃ ገብነት ሊያግዟቸው እያኮበኮቡ ያሉትን ሃይሎች ( አሜሪካና አሜሪካ የምትነዳቸው አገራትና ተቋም ) ምክንያት እንዲያጡ ሊያደርግ እንደሚችል ስጋታቸውን አንስተው ተነጋግረዋል።

በተደጋጋሚ ትህነግ ህዝብን ለማስነሳትና ዓለም ዓቀፍ ድጋፍ ለማግኘት የተቀነባበረ አደጋ በራሳቸው ሕዝብ ላይ በመፈጸም መልሰው ለፕሮፓጋንዳ የመጠቀም ልምድ ያካበቱ እንደሆነ በተደጋጋሚ በራሳቸው ነባር አመራሮች ሳይቀር የሚገልጽ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል።

አሁን ላይ ከአንዳንድ በሳል ፖለቲከኞችና ምሁራን እንደሚደመጠው ኢትዮጵያ ከማሬካ ጋር ያላትን ልዩነት የሚይረግብ ልዩ ልዑክ በማቋቋም ንግግር መጀመር እንዳለባት እየጠቆሙ ነው። ምን አልባትም ትህነግ ይህ ስጋት ሆኖበት በጉዳዩ ላይ በስጋት ደረጃ ጊዜ ውስዶ ስለመነጋገሩ የተባለ ነገር የለም።


Exit mobile version