Site icon ETHIO12.COM

ልዩ ዜና-“ለትህነግ ክፉ ተግባራቱን ሁሉ የሚዘክሩለት የመታሰቢያ ሃውልቶች ሊቆሙለት ነው” የሊጥ ሃውልት አንዱ ነው

ሃያ ሰባት ዓመት በሃይል አስገድዶና ምርጫ እያታለለ ስልጣን ላይ የኖረው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ( ትህነግ ) በሕዝብ ትግልና ከውስጡ በተነሱ የለውጥ አራማጆች ህብረት ከመንበሩ መወገዱን ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎ በመላው አገሪቱ ሲቀሰቀሱ ለነበሩ ረብሻዎች፣ መፈናቀልና ግድያ ተጠያቂ ተደርጎ ” አሸባሪ” መባሉም አይዘነጋም።

ከዚህ ሁሉ ሂደት በሁዋላ የራሱ አመራሮች በይፋ እንዳስታወቁት ሃያ ሁለት ዓመት በትግራይ የኖረውንና ድንበር ሲጠብቅ እድሜውን በጨረሰው የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመክፈት ክህደት የፈጸመው ትህነግ፣ አመራሩ ወደ በረሃ ከሸሸ ስምንት ወር በሁዋላ ወደ መቀለ ተመልሷል። መንግስት የተኩስ አቁም አውጆ ከትግራይ ክልል መልቀቁን ሲያስታውቅ፣ ትህነግ በድል አድራጊነት ወደ መቀለ መመለሱን ሲያውጅ አዲስ አበባ ሳይቀር ያሉ ደጋፊዎቹ በከፍተኛ ደረጃ ደስታቸውን ገልጸዋል። በውጭ አገር የእርቃን ፓርቲ ሁሉ ተደርጓል።

ሰፊ ሰራዊት ግንብቶና ቀድሞ ዝግጅት አድርጎ እንደነበር ሲያስታውቅ የቆየው ትህነግ የአማራና አፋር ክልሎችን በስፋት መውረሩና ወረራው በፍጥነት እየተስፋፋ በተጋገነነው ደረጃ ባይሆንም ሸዋ ሮቢትን ዘልቆ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአገር እንደሚወጡ እየተናገረና በየቀኑ ” አልቆላችኋል እጅ ስጡ” የሚል ጥሪ ሲያቀርብ የነበረው የትህነግ አመራር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ግንባር በሄዱ በሁለት ሳምንት ውስጥ “ታክቲካ በሆነ ጉዳይ አፈግፍጊያለሁ” ማለቱ ደጋፊዎቹን ሳይቀር ያስደነገጠና ለመቀበል ያስቸገረ ዜና ነበር።

መንግስትና እማኞች ትህነግ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ እንደደረሰበት ሲናገሩ፣ ጭፍራ ሆኖ የዘገበው አልጀዚራ ወኪል ” ጦርነቱ መተዛዘን የሚባል ነገር መቅረቱን የሚያሳይ፣ ሜዳው ሁሉ አስከሬን በአስከሬን ሆኗል” የሚል ትዝብቱን አቅርቦ ነበር። ምርኮኞችም በተዓምር መትረፋቸው ሲገልጹ ተሰምተዋል።
ከትግራይ የተነሳው ወራሪ ሃይል በሃይል የለቀቃቸውና የመንግስት ሃይል ነጻ ካወጣቸው አካባቢዎች የሚወጡት ዜናዎች እጅግ ለማመን የሚከብዱና የሚዘገንኑ በመሆናቸው ትህነግ የሚባል ድርጅት እስከወዲያኛው መጥፋት እንዳለበት ሕዝብ አቋም ያዘ። መዝረፍ፣ ማጋዝ፣ ካልተቻለ ማውደም፣ ሕዝቡን ማንገላታት፣ መግደል፣ ሴቶችን እድሜ ሳይመርጡ መድፈር፣ ሌማት ላይ፣ የዕምነት ስፍራዎች፣ በየመስሪያ ቤቶች፣ በየመነገዱ፣ በፋብሪካዎችና የአገልግሎት ተቋማት ውስጥ መጸዳዳት … የመሳሰሉ ዜናዎች በምስልና በተጎጂ አንደበት ይፋ መሆናቸውን ተከትሎ ሶስት ለጊዜው ማንነታቸው ያልተገለጸ ፕሮፌሰሮች ለዚህ ሁሉ የትህነግ ወንጀል መታሰቢያ እንዲቆምለት የመነሻ ሃሳብ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የትህነግን ታሪኩን፣ የተከላቸውን መታሰቢያዎቹንና አመለካከቱን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት እንደሚሰራ በይፋ መናገራቸው ምን አልባትም ከዚህ ጉዳይ ጋር ስለመያያዙ መረጃውን የሰጡ አላስታወቁም። አቶ ለደቱም 360 ላይ ቀርበው ከኤርሚያስ ለገሰ ጋር ትህነግ ህያ ሰባት ዓመት ሆን ብሎ የሰራው ጥፋት እንደሌለ ሲሟገቱ የነበረው ይህን ሃሳብ ለመከላከል አስበው ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር ነገር የለም።

ሃሳቡን ያቀረቡት ክፍሎች እንዳሉት ግን በየክልሉ ከተማዎችና በተመረጡ ህዝብ የሚሰበስባቸው አካባቢዎች ላይ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ሁሉ የፈጸማቸውን ተግባራት የሚያሳዩ መታሰቢያ እንዲቆም መነሻ ፕሮፖዛል አቅርበዋል። ሃሳቡን ያቀረቡት ምሁራን ድፍን የትግራይ ህዝብን በማይወክል ደረጃ በጥንቃቄ የትህነግን የሞራል ውድቀት፣ የክፋት ጥግ፣ የክህደት ደረጃ፣ ዝርፊያ፣ ግድያ፣ አውዳሚነትና የጅምላ ደፋሪነቱን የሚያሳዩ መታሰቢያዎች እንዲቆምለት የቀረበርው ፕሮፕዛል ምን ምላሽ እንደተሰጠው ባለቤቶች ለጊዜው አላስታወቁም።

” ከትንሿ የሊጥ፣ አሻሮና እንኩሮ ዘርፊያ ጀመሮ ሁሉንም አይነት ተግባሩን ትውልድ ባለፈ ባገደመ ቁጥር እንዲማርበት፣ ሲደግፉት የነበሩትም ሃፍረቱን እያዩ ለውደፊቱ እንዳይመለሱበት፣ የሚያደረግ መታሰቢያ በቅርቡ ይቆማል” ያሉት የሃሳቡ ባለቤቶች፣ አስቸኳይ ምላሽ እንደሚሰጣቸው እምነታቸው መሆኑንን አክለው ገልጸዋል።

በፕሮፖዛሉ በብሄራዊ ደረጃ አንድ ቀን ተሰይሞ መታሰቢያዎች ዙሪያ የትህነግን ክፉ ተግባራት የሚዘግቡ ዝግጅቶችም እንደሚደረጉ ተካቷል። እንደ ቀይ ሽብር ሰላባዎች የመታሰቢያ ኤግዚቢሽን ማዕከል በቋሚነት በህዝብ ተሳትፎ እንዲገነባ ሃሳቡ ይጠይቃል። ከዚህም በላይ መጻህፍት፣ ሙያዊ ደረጃው ከፍ ባለ ደረጃ ለሰነድ የሚሆኑ ፊልሞች እንዲሁም የመስል መጋዘኖች እንዲዘጋጁ የሚል በሃስቡ መነሻ ላይ ተቀምጧል።

መንግስት ሰሞኑንን የትህንገ ወራሪ ሃይል እግሩ በደረሰበት ሁሉ የፈጸመውን ተግባራቱን የሚያሳይ የመስል ድረ ገጽ ይፋ ማድረጉ ከዚህ ሃሳብ ጋር የሚገናኝ ስለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም።


Exit mobile version