Site icon ETHIO12.COM

አሜሪካ የጋራ ዉሉን ልትስርዝ ነዉ‼ «ህወሓትን አውላላ ሜዳ ላይ ጥላዋለች»

መረጃ በርባሪዉ የምዕራባዉያንን የዉስጥ ሚስጥር አፈንፍኖ ይፋ የሚያወጣዉ የፈረንሳዩ “Press Tv Francias’s” የመረጃ አዉታር ኢትዮጰያን በተመለከተ አዲስ ሚስጥራዊ መረጃን በድህረ ገፁ ይዞ ወጥቷል፤ እነሆ እኛም ጀባ ብለናችኋል።

የኢትዮጲያ ጦር የትግራይ ክልል አማፂያን የያዙትን የአማራ’ና አፋር ክልል ከተቆጣጠሩ በኋላ የአሜሪካ መንግስት በህወሓት ላይ ያለዉን የጋራ ዉል ሊስርዝ መሆኑን የመረጃ ማዕከሉ ዘግቧል። ለዚህም እንደ ምክንያት የተጠቀስዉ አማፂያኑ የህወሓት ሠራዊት በወረራ በያዛቸው ከተሞች የፈፀመዉ ግፍ የሕዝብን የቁጣ ማዕበልን ቀስቅሶ የመተላለፊያ ቀዳዳዉን መድፈኑ USAን ተስፋ ማስቆረጡን በስፋት አስነብቧል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ የምታደርገዉ የእጅ አዙር ጦርነት የቋመጡበት የድል ተስፋዉ ተመናምኗል ያለዉ የመረጃ አውታሩ አዲሱን ዕቅዷንም እንዲሁ ይፋ አድርጓል። ዋሽንግተን በሉዓላዊ ሐገራቴ የውስጥ ጉዳይ ጥቅሟን ያማከለ የዉክልና ጦርነት ስትፈፅም ሴናተሮቿን በሁለት ጎራ ከፍላ አንዱ የመንግሥት ሌላኛዉን የተቃዋሚ ቡድን ደጋፊ አድርጋ ታስቀምጣለች።

በሁለቱም የተፋላሚ ቡድኖች ዉስጥ የሚገኙት የአሜሪካ ሴናተሮች አሽናፊዉን ቡድን ከአሜሪካ ማዕከላዊ መንግሥት ጋር ድፕሎማት በመሆን በሽምግልና በወዳጅነት ለማስተሳስር የተጣለበት ማዕቀብ ተነስቶለት ኢኮኖሚዉ የሚያንሠራራበትን ሁኔታ እንዲመቻች ይማፀኑታል። Press Tv Francain’s የመረጃ አዉታር የዋይት ሐውስ የወደፊት ዕቅድ በኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥቱን አቋም ሲደግፉ የነበሩ ሴናተሮቹንና ፖለቲከኞቹን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ትስስሩን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ሥራ እንደሚሆን ዘግቧል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለዉ ጦርነት በድርድር መቋጫን ያግኝ በማለት አማፂያኑን ህወሓትን ከሞት ለመታደግ በቱርክ፣ ቻይናና ሩሲያ ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚያደርጉትን የመሳሪያ ድጋፍ እንዲያቆሙ ያደረገችዉ ጥረት አለመሳካቱን ተከትሎ ህወሓትን አውላላ ሜዳ ላይ ጥላዋለች ሲል የመረጃ ማዕከሉ አስታውቋል።

የአማፂያኑ ፍፃሜም ከጫፍ መድረሱን የገለፀዉ Press Tv Francaic’s የዜና አዉታር የቡድኑ መሪዎች የሚጠብቃቸዉን ሁለት ዕድል መርጠዉ እንደሚጠቀሙም አስታውቋል።

⓵ እጅ ስጥተዉ ለፈፀሙት ወንጀል የሕግ ፍርዳቸውን በፀጋ መቀበል፣
⓶ በቀረች ጥይትና አቅማቸዉ ተፋልመዉ መደምሰስ ሲል የመረጃ ትንታኔዉን አሳርጓል።

Mohammed_jemal

Exit mobile version