Site icon ETHIO12.COM

ከሃገራዊ ምክክሩ በፊት መንግስት ለእነ ስብሃት፣ጃዋርና እስክንድር ምህረት አደረገ፤

“በሂደቱ የተጎዱ ወገኖች እንደሚኖሩ መንግሥት ያምናል። የእነዚህ ተጎጂ ዜጎች ቁስል በሽግግር ፍትሕ የሚካስ ይሆናል። እነዚህ ተጎጂ ዜጎች ሕመማቸው ለኢትዮጵያ የከፈሉት ዋጋ በመሆኑ ሸክማቸውን መንግሥትና ሕዝብ በጋራ እንሸከምላቸዋለን። ከእሥር የተፈቱ ወገኖችም ጭምር የተጎጂዎችን ሸክም የመሸከም ዕዳ አለባቸው።መንግሥት ይሄንን ውሳኔ የወሰነው በዋናነት ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ነው። ኢትዮጵያ የመሐሪነቷን ዋጋ እንድታገኝ፣ የኢትዮጵያን ምሕረት ያገኙት አካላት፣ ምሕረቱን ያገኙበትን ዋጋ ይረዱታል ብሎ መንግሥት ያምናል” መንግስት አስታውቋል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕገ-መንግስት እና የሽብር ችሎት እየታየ ከነበሩት ተከሳሾች መካከል በነጃዋር ሲራጅ መሃመድ እና በእነ እስክንድር ነጋ ፈንታ መዝገብ ያሉ ተከሳሾች ክሳቸው በአዋጅ ቁጥር 943/2008 መሰረት እንዲነሳ ተደርጓል።

ክሱ እንዲነሳ የተደረገው በቀጣይ የሚደረገውን ሃገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ በማሰብ ነው። እንዲሁም በእነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዐሾ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ውስጥ የጤና እና የዕድሜ ሁኔታን ከግምት በማስገባት የስድስት ግለሰቦች ክስ እንዲነሳ ተደርጓል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕገ-መንግስት እና የሽብር ችሎት እየታየ ከነበሩት ተከሳሾች መካከል በነጃዋር ሲራጅ መሃመድ እና በእነ እስክንድር ነጋ ፈንታ መዝገብ ያሉ ተከሳሾች ክሳቸው በአዋጅ ቁጥር 943/2008 መሰረት እንዲነሳ ተደርጓል። ክሱ እንዲነሳ የተደረገው በቀጣይ የሚደረገውን ሃገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ በማሰብ ነው።

(ፍትሕ ሚኒስቴር)

በዚህ መሰረትም ከተፈቱት መካከል

1. አቶ ስብሐት ነጋ

2. ወሮ ቅዱሳን ነጋ

3. አቶ ዓባይ ወልዱ

4. አቶ አባዲ ዘሙ

5. ወሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር

6.ወ/ሮ ኪሮስ ሐጎስ

7. አቶ ጁሐር መሐመድና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ

8. አቶ እስክንድር ነጋና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ ከእስር እንዲፈቱ ተወስኗል፡፡


Exit mobile version