Site icon ETHIO12.COM

እነ ጃዋር ከትህነግ፣ትህነግ ከሚያንቀሳቅሳቸው ሸኔና የጉምዝ አማጺ ጋር ድርድር እንዲደረግ ጠየቁ፣ “…እያለቀስን እንጸልይ ነበር”

አቶ ጃዋርና አቶ በቀለ ትህነግ ከሚያንቀሳቅሳቸው ሸኔና የጉምዝ አማጺ ጋር ድርድር እንዲደረግ መጠየቃቸው ተሰማ። እስር ቤት ሆነው በመላው አገሪቱ ላይ የደረሰውን በማየት የሚያደርጉት ነገር ባለመኖሩ በሃዘን ሲያለቅሱና ሲጸልዩ እንደነበርም አስታውቀዋል።

“በእስር ቤት ውስጥ ሆነን በአውዳሚው ጦርነትና በተፈጠረው ሰብአዊ ውድመት የተጎዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን ችግር በአሰቃቂ ሁኔታ ተመልክተናል። አገራችን የውድቀት አፋፍ ላይ ሆና ከእስር ቤት ልንሰራው የምንችለው ነገር ባለመኖሩ በጭንቀት ስናለቅስና ስንጸልይ ነበር” ሲሉ አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ከተለቀቁ በሁዋላ ለመጅመሪያ መግለጫ አሰራጩ። ሃዘን እንደገባቸው ሲያስታውቁ የሃጫሉ ድንገተኛ ህልፈት ተከትሎ በሻሸመኔ፣ ዘዋይ፣ መቂና በተለያዩ ከተሞች ስለ ደረሰው የንጹሃን ጭፍጨፋና ንብረት ውድመት ምንም አላሉም።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ / ኦፌኮ “አመራሮቼ የታሰሩት በተዘጋጀ የሀሰት ክስ እና ከህግ ውጭ ነው” ሲል በመህበራዊ ገጹ ሁለቱን አመራሮቹ ስለመፈታታቸው ባሰራጨው መግለጫ እንዳለው እስሩ ፓርቲውን ከፖለቲካ ምኅዳሩ ለማስወገድና ለምርጫ እንዳይቀርብ ለማድረግ የተወሰነ መሆኑንን አመልክቷል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ በግድ ከፖለቲካ ምህዳር ከተወገድን በኋላ ብዙ ነገር ተከስቷል” ያለው አመራሮቹን ጠቅሶ ” በእስር ቤት ውስጥ ሆነን በአውዳሚው ጦርነት እና በተፈጠረው ሰብአዊ ውድመት የተጎዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን ችግር በአሰቃቂ ሁኔታ ተመልክተናል። አገራችን የውድቀት አፋፍ ላይ ስትወድቅ ከእስር ቤት ልንሰራው የምንችለው ነገር በጭንቀት ማልቀስ እና ለተሻለ ቀን መጸለይ ብቻ ነበር። በተለይ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋርና በአማራ ክልሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመው ግፍና አሳዝኖናል” ብሏል።

“ባለፉት 13 ወራት በአገሪቱና በሕዝቧ ላይ የደረሱትን ጉዳቶችን መቀልበስ ባይቻልም፤ ተጨማሪ ጉዳቶችን ማስቀረት የምንችልበት ጠባብ ዕድል አለ” ያሉት ሁለቱ የፓርቲው አመራሮች ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋርና አማራ ክልሎች በሲቪል ነዋሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት አሳዛኝ መሆኑንን ጠቅሰዋል። ስም ባይጠሩም “በኦሮሚያ፣ ትግራይ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች በድርድር ይፈቱ” ብለዋል። መንግስት እንዲደራደር የጠየቁት ከትህነግ ጋር አብረው እንደሚሰሩና ትህነግ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው በይፋ ከሚታወቀው ከሸኔ፣ ከቤኒሻንጉል ነጻ አውጪና ከራሱ አሸባሪ ከተባለው ከትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ጋር ነው።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የእርስ በእስር ጦርነት በሰላም እንዲጠነናቀቅና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋገት እንዲሰፍን የውጭ አካላት ከፍተኛ ሚና ሊኖራቸው እንደሚገባ አመልክተዋል። ማድረግ ይችላሉ ያሉዋቸውን የዓለም አቀፍ ማህበረሰብና የቀይ ባህር አካባቢ አገሮች ከላይ ከተገለጹት አገራት ጋር ድርድር እንዲደረግ ጫና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። አክለውም በውጊያ ለሚሳተፉት ፖለቲካዊም ሆነ ቁሳዊ ድጋፎችን ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። አገሮቹን ግን በስም አልጠሩም።

ሕዝብ ለማናቸውም ወታደራዊ ጥሪዎችን ጆሮውን እንዳይሰጥ የጠየቁት አቶ ጃዋርና አቶ በቀለ፤ መገናኛ ብዙኃንም የአንድ ወገን ትርክቶችንና የጥላቻ ፕሮፖጋንዳዎችን ከማስተላለፈ ሊታቀቡ እንደሚገባም አመልክተዋል።

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በማስታወስ ተዓማኒነት ያለው ምርመራ እንዲደረግ ያመለከቱት ሁለቱ ፖለቲከኞች ሃጫሉ ከሞተ በሁዋላ አስከሬን ቤሰቦቹ ይዘው ወደ አምቦ እየሄዱ ሳለ ቡራዩ ላይ ደርሰው ለምን ወደ አዲስ አበባ በርመለስ የኦሮም ባህል ማዕከል መውሰድ እንደፈለጉ ያሉት ነገር የለም። ቤተሰቦቹ በወቅቱ በዚህ ተግባር ማዘናቸውንና የሚወዱትን ጀግናቸውን ለመቀበር እንኳን አለመቻላቸውን በሃዘኔታ መግለጻቸው ይታወሳል። በጉዳዩ ላይ ብዙ ማብራሪያ የሚጠይቁ፣ ይህንኑ ተከትሎ በሻሸመኔ፣ በዝዋይ፣ በመቂ፣ በባሌና በተለያዩ አካባቢዎች ስለደረሰው ውድመት፣ ግድያና መፈናቀል ዝምታን መርጠዋል። እነሱ ቢፈቱም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋትና በተደራጀ ሃይል ከተፈጸመው ዘግናኝ ግድያ፣ ዝርፊያና ውድመት ጋር ተያይዞ ተያይዞ ለአንድ ዓመት ከመፈንቀ በአስር ላይ የቆዩት ሁለቱ አካላት ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እያታየ እንደነበር ይታወሳል።


Exit mobile version