Site icon ETHIO12.COM

ውሳኔው ወደ መጨረሻው እየቀረበ ነው – አሜሪካ አደራዳሪ ባለስልታኖቿ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ሃላፊ ሞሊ ፊ በቅርቡ ጄፍሪ ፌልትማንን የተኩትን ዴቪድ ሳተርፊልድን ይዘው የሱዳንና የሪያድን ጉዟቸውን ሲያጠናቅቁ  ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። ባለስልጣናቱ ከሰኞ ጀምሮ አራት ቀን ይፈዳጃል በተባለው የስራ ጉዞ በዋናነት ሱዳንና ኢትዮጵያ አጀንዳ እንደሚሆኑ ከወዲሁ ዕቅዱ ይፋ ሆኗል።

ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን በስልክ ካናገሩ በሁዋላ በሚደረገው በዚህ የስራ ጉዞ ውስጥ ለውስጥ ከሚደረገው ውጭ ቅድሚያ ተሰጥቶ ይሰራበታል በሚል ይፋ የሆነው መረጃ ምንም አዲስ ነገር የሌለውና ቀደም ሲል ሲባል የኖረው ነው። በገሃድ የተመለከተውና ከመጋረጃ ጀርባ በአስገዳጅነት ስለሚሆነው ጉዳይ ፍንጭ ባይሰጥም የአየር ጥቃትን ጨምሮ ተመሳሳይ የጦርነት ግጭቶች መላ ማለት፣ ዝርዝሩ ያልየገለጸና ድርድር ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ( መንግስት የፖለቲካ እስረኞች ሳይሆን ወንጀለኞችና አገር ከሃዲዎች የሚላቸው እስረኞች ብቻ እንዳሉ ነው የሚገልጸው) ወደ ትግራይ የሰብአዊ እርዳታ የሚገባበት ሁኔታ እንዲመቻችና የብሄራዊ ውይይቱ እንዲሳካ፣ ሌሎችም ዕድሉን እንዲተቀሙበት መንግስትን እንደሚያግዙ ነው የተገለጸው።

ለጠቅላይ ሚኒስትር ስልክ ደውለው ውይይት ያደረጉት ጆ ባይደን ተነገሩት ተብሎ ከተነገረው ውጭ ምንም አዲስ መረጃ ያልያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግልጽ ባያደርገውም፣ በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ወደ ጦርነት የተቀየረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በምንም ይሁን በምን በድርድር እንዲያበቃ ቁርጥ አቋም ስለመያዙ ግን አመላካች ጉዳዮች አሉ። ለማመን በሚከብድ ደረጃ ኢትዮጵያ ላይ በደቦ የተከፈተው ዘመቻ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ጉዳይና በሕዝብ ሰላማዊ ኑሮ ላይ ያስከተለው ቀውስ ከፍተኛ ቢሆንም ወረራውን ሕዝብ አንድ ሆኖ መቀልበሱ የደቦ ጠላቶቿን አቋም እንዳስቀየረ ከየአቅጣጫው እየተገለጸ ነው።

በተለይም እጣው መበተንና መፍረስ እንደሆነ በማርትና በቅዠት ሲገለጽለት የነበረው የአገር መካላለከያ ሰራዊት ወረራውን በመከላከል በጎንዮሽ ራሱን እንደገና አደረጃቶ ሰፊ ሃይል መገንባቱ የአሜሪካንን አቋም ሊያስቀየር እንደቻለ ለዲፕሎማት ቅርብ የሆኑ ወገኖችን ጠቅሰው አስተአየት የሰጡም በርካታ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የቻይና አፍሪቃ ቀንድ ላይ አጀንዳዋና መሰረቷ መተከሉና በቀይ ባህር ፖለቲካ ላይ ድርሻዋ እንዲበዛ ከኤርትራ ጋር ያደረገቸው ስምምነት አሜሪካን እንዳነቃነቃት የሚገልጹም አሉ።

በቀውስ ለተነከረችው ሱዳን መፍትሄ ለማፈላለግና ፣ በሲቪሎች የሚመራ ዴሞክራሲያዊ ሽግግርን ሂደትን አስመልክቶ በሪያድ ከተማ የተባበሩት መንግሥታት በሚካሄደው ስብሰባ ከተሳተፉ በሁዋላ ወደ ሱዳን የሚያመሩት የአሜሪካ ባለስልታናት ካርቱም ይገባሉ። በካርቱም ከአክቲቪስቶች፣ ከሴቶችና ከወጣቶች እንዲሁም ከሲቪል ማኅበራት፣ ከወታደሩ መሪዎችና ከፖለቲከኞች እንደሚመክሩ ስለ ጉዞ ዕቅዳቸው የወጣው መግለጫ ያስረዳል። በማብቂያው አዲስ አበባ ይግባሉ።

ትህነግን በ1991 አመለካከቱ ላይ የተቸከለና የማይሰማ እንደሆነ አስታውቀው ከሃላፊነታቸው የተነሱት ጄፍሪ ፌልትማን በመንግስት ጥሪ አዲስ አበባ ደርሰውሲመለሱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና ዐቢይ አሕመድን በስልክ ማነጋገራቸው የተበላሸውን የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማሻሻል ውሳኔ ስለመኖሩ አመላክች እንደሆነ አፍታም ሳይቆይ ተገልጿል። ምንም እንኳን እንደ አምባሳደር ዴቪድ ሺን ዓይነት ዲፕሎማቶች ” የአቋም ለውጥ” የለም በሚል ” የቀለም ቅብ” ስራ ሊሰሩ ቢሞክሩም በመርህ ላይ የተመሰረተ መሻሻል ስለመጀመሩ ማስተባበል እንደማይቻል አብዛኞች ይስማማሉ።

የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ከሆኑ ገና መንፈቅ ያልሆናቸውና ቀደም ሲል የደቡብ ሱዳን አምባሳደር የነበሩት ሜሪ ካትሪን ሞሊ ፊ ሜሪ እና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት የዲፕሎማሲ ልምዳቸው ከፈተኛ እንደሆነ የተነገረላቸው አዲሱ የአፍሪቃ ቀንድ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ በኢትዮጵያ የሚደርሱበት ውጤት ከወዲሁ የሚታውቀም ሆነ ፍንጭ የሚሰጥ አይደለም።

ትህነግ አልፎ አልፎ እዛም እዚህም የሚተኩሳው የመደራደሪያ ሃይሉን ለማጎልበት በሚል እንጂ ከዛ የዘለለ አቅም እንደሌለው፣ ከሞከረም እንደሚጎዳ ጀነራል ባጫ ደበሌ ማስታወቃቸው ይታወሳል። በዋናነት ግን ተተኳሽም ሆነ ሃይል ስለተመናነመነበት ባለስልጣኑ እጃቸውን እንዲሰጡ ወይም አምነስቲ አግኝተው አገር ለቀው የሚወጡበት አግባብ እንዲፈለግ እጅግ ለአሜሪካ ፖሊሲ አውጪ ቅርብ የሆኑ የምክርና ሃሳብ ለጆ ባይደን ማቅረባቸው አይዘነጋም። አሜሪካ ያረጁና የታመሙ በመሆናቸው ክስ ተቋርጦ እንዲለቀቁ በተደረጉ የትህነግ ቁኝጮዎች ሳቢያ በአገር ውስጥ ሕዝብ ያሰማው ተቃውሞ እጅግ ከፍተኛ መሆኑንን አሜሪካ መገምገሟ፣ አምብሳደር ፌልትማንም ሕዝብ ትህነግን ዳግም ማየት እንደማይፈልግ በይፋ በሪፖርታቸው ማካተታቸው አሁን በሚያዙ አቋሞች ላይ ተሳቢ እንደሚሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

የቱርክ አምባሳደር ከመሆናቸው በፊት በዶናልድ ትራምፕ ዘመን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ማይክ ፖምፔዮ ልዩ አማካሪ የነበሩት አዲሱ የአፍሪቃ ቀንድ መልዕክተኛ ይህንን ሁሉ ጉዳይ እንዳጠኑት ጥቆማ አለ። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በህገመንግስት በተቀመጠው መሰረት አንድ አገር ውስጥ ሁለት የመከላከያ ሃይል ሊኖር እንደማይችል፣ በዚህ ሃሳብ ከቶውንም እንደማትደራደር፣ አሜሪካም ይህን አቋም መደገፏ ለትህነግ ከፍተኛ ራስ ምታት፣ ነገር ግን አሜሪካ ” አድርጉ” ካለች ሊከራከሩበት የማይችሉት ጉዳይ መሆኑ የሰላም ድርድሩን ከወዲሁ የጠቆረው ቢመስልም ይህ ደረጃ ከታለፈ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ መንገድ ሊኖር እንደሚችል በርካቶች ግምት አላቸው። በሁሉም መስክ ወደ መጨረሻ እየተቃረበ ስለመሆኑ ግን ጥርጥር የለም።

Exit mobile version