Site icon ETHIO12.COM

የሸኔ አደረጃጀትና መረጃ መታወቁ ተሰማ

SAMSUNG CAMERA PICTURES

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ በሸኔ ውስጥ የእርስ በእርስ መከፋፈል መፈጠሩን ባስታወቁ፣ መከላከያ፣ ኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ክልል በጥምር ሰፊ የማጽዳት ዘመቻ ላይ መሆናቸውን ባስታወቁበት ሳምንት የሸኔ ሙሉ መዋቅርና የግንኙነት ሰነድ መንግስት እጅ መግባቱ ተሰማ። ከፍተኛ የተባሉና ቁልፍ የቡድኑ አባላት እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆናቸው ተሰማ።

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ መረጃ አቀባይ ለኢትዮ12 የአዲስ አበባ ተባባሪ እንዳሉት ሸኔ ውስጥ በኦሮሚያ እየተፈጽመ ባለው ግድያ፣ ንብረት ማውደምና በተለይም ከትህነግ ጋር በይፋ የተገለጸው ሕዝብረት በታች አመራሮችና ታጣቂዎቹ ዘንዳ ቅሬታ ማስነሳቱ ተሰምቶ ነበር። እጃቸውን በአርሲ አቅጣጫ የሰጡም ድርጅቱን ለመለያት ምክንያት የሆናቸው ይኸው ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል።

እንደ መረጃው ሰው የሸኔ የመዋቅርና የትሥሥር መዋቅር ማመላከቻ ኮድ መንግስት እጅ የገባው እጃቸውን ለመስጠት ፍላጎት ያላቸው ባደረጉት ትብብር ነው። ይህ ቁልፍ ኮድ ድርጅቱን በገንዘብ፣ በሎጂስቲክ የሚያግዙና ጊዜያዊ ስምሪት ሲወሰድ መረጃው እንዴት እንደሚሰራጭ የሚያሳይ ከመሆኑ በላይ የብር ስርጭትና የክምችት “ማማ” ያሳያል። ግንኙነቱን እንዴት ከውጭ ያሉ አመራሮች ወደ አገር ውስጥ ትዕዛዝና መደብ እንደሚያወርዱ፣ ከውስጥ እንዴትና በእነማን ሪፖርት እንደሚላክ ያሳያል። ሚዲያዎችም አሉበ።

የአገሪቱ ደህንነትና የክልሉ መንግስት የጸጥታ መዋቅር ዝምታ በመምረጡና በቀጣይ የሚሰራ ስራ በመኖሩ ዝርዝር መረጃ መስጠት አልተፈለገም እንጂ በቡድኑ ውስጥ ድርጅታዊ መናበብ፣ ድርጅታዊ ግንኙነትና በተለይም ከትህነግ ጋር የነበረው መዋቅር ፈርሷል። በዚህ መረጃ መሰረት አስፈላጊ መረጃዎች በመሰብሰባቸው ሸኔ ልክ እንደ ትህነግ ሁሉ ቡድናዊ አቋሙ በቅርቡ እንደሚወላልቅ፣ በዚህም ሳቢያ እጃቸውን ለመስጠት የውሰኑ ሃላፊዎች በቅርቡ በመንግስት ሚዲያ እንደሚቀርቡ የዜናው ምንጭ አስታውቀዋል።

አልፎ አልፎ በተስፋ መቁረጥ ከሚፈጠር የሽፍታ ስራ ውጭ አቅሙ የላመው ሸኔ፣ እንደ ድርጅት ለመቀጠል ቢፈልግ እንኳ ሊሳካለት እንደማይችል ዜናውን የነገሩን አመልክተዋል። የመዋቅሩ መገነትና የትሥሥሩ ውል መታወቁ ክልሉን እየመራ ያለው ፓርቲ ይፋ ሊያደርገው እንደሆነ ከሚሰማው ማጥራት ጋር ሊገናኝ እንደሚችልም ጠቁመዋል። ከትህነግ እየከሰመ መሄድ ጋር በርካታ ጉዳዮችና ቡድኖች አብረው እንደሚከስሙ ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ተፎካካሪ አስተሳሰብ ያላቸው ሁሉ በተመሳሳይ አገራዊ መጋባባት ላይ ሆነው ልዩነታቸውን በህግ አግባብ ማራመድ የሚችሉበት ስምምነት ላይ የሚያደርሳቸውና ወደ ሰለጠነ ፖለቲካ የሚያሸጋግር ስራ እየተሰራ መሆኑን የመረጃው ምንጭ አመልክተዋል።

መረጃውን በመያዝ በኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የጸጥታ ዘርፍ ማረጋገጫ ወይም ማስተባበያ ለመጠይቅ ተባባሪያችን ሞክሮ አልተሳካለትም።

Exit mobile version