Site icon ETHIO12.COM

የሱዳኑ ጄኔራል ሐሜት አዲስ አበባ መግባት ድንጋጤ ፈጥሯል

ለሁለትዮሽ ንግግር የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ መግባታቸው ” ነገሩ ምንድን ነው” የሚያሰኝ ዜና ከየአቅጣጫው እያስነሳ ነው። ከሁሉም በላይ ሱዳንን ተማነው በነበሩ ሃይሎች ዙሪያ ስጋት መፍተሩ ተሰምቷል።

የመከላከያ ሚንስትሩ ዶ/ር አብርሀም በላይና የብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል ያደረጉላቸው የሱዳን ትልቁ በለስልጣን በድንበር አካባቢ በለው የሁለቱ አገራት ውዝግብ ጉዳይ ለመነጋገር አዲስ አበባ ማቅናታቸውን የአገራቸው ሚዲያዎች ዘግበዋል። የአሜሪካ ባልስልጣናት ሱዳን ከደረሱና ከተወያዩ በሁዋላ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው ጉዳዩ ከዛም ያለፈ እንደሆነ የሚተቁሙ መረጃዎችም እየተሰሙ ነው።

ሔሜቲ በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት እኚሁ የሱዳን ወታደራዊ አስተዳደር ሁለተኛ ሰው፣ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ነው የመጡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት አቅርበዋላቸዋል።

 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በማህበራዊ አውዳቸው እንዳስነበቡት በራሳቸው የኢትዮጵያና የሱዳን ሕዝብ ያላቸውን ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር እንደሚያደንቁ አስታውቀው፣ በየትኛም ሁኔታ እንደማይነጣጠሉ ገልሰዋል። ለሀገራቱና ለህዝቦቻቸው ተጠቃሚነት ሲሉም ይህንን ግኑኝነት ለመጠበቅ ብሎም የበለጠ ለማጠናከር ጥረት እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል። በድፈናው ለሁለቱም አገር ህዝብ ጠቀሜታ ሲባል ግንኙነትን ስለማጠናከር ይግለጹ እንጂ ዘርዝር ጉዳዩን አላመላከቱም።

ሱዳን የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ በድንገት ፊቷን ካዞረችና የግብጽ ስራ አስፈሳሚ ከሆነች በሁዋል ለወትሮም ጥርት ብሎ ያልኖረው የድንበር ጉዳይ አጀንዳ መሆኑ ይታወሳል። መንግስት ከትህነግ ጋር የገባበትን ችግር ተስታከው በግብጽ መሪነት ወረራ የፈጸመው የሱዳን ወታደራዊ አስተዳደር፣ አሁንን ላይ ከገተመው ከፍተኛ የፖእቲካና አለመረጋጋት ቀውስ ጋር ተያይዞ ከወዳጅ አገር ኢትዮጵያ ጋር ለመስማማት ስለመውሰኑ ፍንጭ አለ።

ሱና እንዳስታወቀ መሐመድ ሐምዳን በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ገልጿል። ኢትዮጵያና ሱዳን በአል-ፋሽጋ የይዞታ ጉዳይ ውዝግብ ይግቡ እንጂ ሱዳን የቤኒሻንጉል አማጺዎችን፣ የትህነግ ታጣቂዎችን፣ እንዲሁም ግብጽ በምታዘውና በምታፈሰው ሃብት መሰረት እነዚህኑ ታጣቂዎች ዘመናዊ መሳሪያ በማሲያዝ ወደ ኢትዮጵያ በማስረግ በኩል ታላቅ ሚና እንዳላት ይታወቃል። የተማረኩና የተገደሉ የሱዳን ዜግነት መኖራቸውን የወታደሮችን ማንነት በሚያረጋግጥ ማስረጃ መንግስት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የተማረክትም ቃላቸውን ሲሰጡ ይህንኑ አረጋግጠዋል።

በዚህ ደረጃ ተካረው ጫፍ የደረሱት ኢትዮጵያና ሱዳን ለመነጋገር ያበቃቸው ወይም እንዲነጋገሩ መነሻ የሆናቸው ጉዳይ ሱዳንን ተመክተው ለቆዩ አገራትና አማጺያን መርዶ እንደሆነም ተመልክቷል። በሱዳን የተነሳው ህዝባዊ ቁጣ መባረድ ባላሳየበት ሁኔታ፣ ኢትዮጵያ የጎደለባትን አሟልታ በቂ ወታደራዊ ሃይል መገንባቷና የትህነግ የመዋጋት አቅም መመናመን እንዲሁም አሜሪካ ፊቷን ወደ ኢትዮጵያ ማዞሯ ተዳምሮ የመሐመድ ሐምዶ አዲስ አበባ መምጣት አጓጊ አድርጎታል።

Exit mobile version