Site icon ETHIO12.COM

ኬንያዊው ከደቡብ አፍሪቃ በአውሮፕላን ጎማ ውስጥ ተደብቆ አምስተርዳም ገባ

-ከደቡብ አፍሪቃ በአውሮፕላን ጎማ ውስጥ ተደብቆ አምስተርዳም የገባው ኬንያዊ መሆኑ ተገለጸ በሙሉ ጤንነት ላይ ነዉ፤ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደሚፈልግ ተነግሮአል

ከደቡብ አፍሪቃ በተነሳ የአውሮፕላን ጎማ ክፍል ውስጥ ተደብቆ በሕይወት አምስተርዳም ኔዘርላንድ የደረሰው የ22 ዓመት ወጣት ኬንያዊ መሆኑ ተገለፀ።

ሕክምና እየተከታተል ነገር ግን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የተገለፀዉ ኬንያዊ ወጣት ጥገኝነት ለመጠየቅ ነዉ በአዉሮፕላን ጎማ ዉስጥ ተደብቆ ኔዘርላንድ የደረሰዉ ተብሎአል።

አዉሮፕላኑ ከደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ እስከ ኔዘርላንድ አምስተርዳም አስራ አንድ ሰዓታት ተጉዞአል።

ኬንያዊዉ ወጣት ከደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ ከተማ ተነስቶ በኬንያ ናይሮቢ በኩል ወደ ኔዘርላንስ ዋና ከተማ አምስተርዳም በበረረዉ ካርጎሉክስ በተባለው የጭነት በረራ አዉሮፕላን ዉስጥ ተደብቆ መድረሱም ተዘግቦአል።

አዉሮፕላኑ ከጆሃንስበርግ ተነስቶ ናይሮቢ ላይ አርፎአል። ይሁንና ኬንያዊዉ ከጆሃንስበርግ አልያም ከናይሮቢ ስለመነሳቱ እስካሁን የተሰጠ ዝርዝር ነገር የለም። DW

Exit mobile version