Site icon ETHIO12.COM

ካጫጫታ ቡዋላ – ግማሽ በግማሽ አምባሳደሮች ቢሯቸው አዲስ አበባ ነው

Ethiopia smoke flag

“ወሳኙ ጉዳይ አገልግሎት ማቀላጠፍ፣ በዋናው መስሪያ ቤት የኦንላይን አገልግሎት ማስፋት፣ የአገሪቱን የዲፕሎማሲ ፓኬጅ መተግባር እንጂ ሰፊ ቤትና ሕንጻ ተከራይቶ፣ ወጥ ቤት ሳይቀር አሰልፎ ውጭ አገር ከሙሉ በኤሰብ ጋር በመኖር በመከራ የሚገኝ ምንዛሬ ማመንዠግ ለምን ቀር ብሎ ማልቀስ አግባብ አይደልም። አልቃሾቹና አስለቃሾቹ ይህ ጥቅም ለምን ቀረ የሚሉት ወገኖች ናቸው። አዲሱ አሰራር ሊመዘን የሚገባው በውጤቱ እንጂ ቪላና ህናጻ በመከራየት ውጭ አገር ተንሰራፍቶ መኖር ላይ ሊሆን አይገባም”

የላብ ቶፐ አምባሳደር የሚባሉት ሁሉንም ስራ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው የሚሰሩ፣ ጉዳይ ካላቸው ራሳቸው መኪናቸውን እየነዱ ጉዳያቸውን ፈጽመው የሚመጡ፤ ጸሃፊም፣ አምባሳደርም፣ ጉዳይ አስፈሳሚም ሆነው በትንሽ ወጪ ተግባራቸውን የሚከውኑን ናቸው። መንግስት ይፋ ባያደርግም አብዛኞቹ ኤምባሳሲዎች ይህን አሰራር የከተላሉ። እንደ ድሮው ትልቅ ግቢ ተከራይተው ከፍተኛ ወጪ እያስወጡ፣ በሾፌር፣ በልዩ ተሽከርካሪ፣ በአጀባ መንቀሳቀስ ብሎ ነገር የለም።

አዲስ ከተሾሙት አምባሳደሮች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተቀማጭነታቸው በሀገር ውስጥ እንደሚሆን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል አቀባዮ አማካይነት ይፋ አድርጓል። በፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ሹመት ከሰጧቸው ሃያ ሰባት አምባሳደሮች ውስጥ የላብ ቶፕና (non-resident ambassadors) ሆነው የሚሰሩ እንዳሉበት በደፈናው ያስታወቁት አቶ ዲና ሙፍቲ ናቸው። “ዲፕሎማሲያዊ ሙያን መሰረት ያደረገ ነው” ያሉት ይህ ሹመት በልምድና በአገልግሎት የተሰተ መሆኑንን አመልክተዋል።

ዲና ሙፍቲ ትናንት በሰጡት ሳምንታዊ የተቋማቸው መግለጫ ሲናገሩ የአምባሳደሮች ሹመት የተከናወነው “በጥናት” መሆኑን ተናግረዋል።ሹመቱ ሶስት አሰራሮችን የተከተለ መሆኑንም አስረድተዋል። በተመደቡበት አገር በቋሚነት እየኖሩ የሚሰሩ፣ አገር ቤት ሆነው ሲያስፈልግ ብቻ እተመደቡበት አገር የሚሄዱና የሚመለሱ፣ በላብቶፕ የሚሰሩ አምባሳደሮች መኖራቸውን አመላክተዋል። ይህ አሰራር በብዙ አገሮች እየተለመደ የመጣ፣ ወጪ ቆጣቢና የዘመኑንን ቲክኖሎጂ በመጠቀም ስራን የሚያቀላጥፍ እንደሆነ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ አስተያየት ይሰጣሉ።

“Non-resident አምባሳደር የሚባሉት አገር ቤት ተቀምጠው ስራቸውን እንደሚሰሩና ከአዲሶቹ ተሿሚዎች ውስጥ በዚህ መልኩ የሚሰሩ እንዳሉ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል ዝርዝር መረጃ ግን አላቀረቡም።

የአምባሳደሮቹ ምደባና የምደባቸው ስፍራ ለጊዜው ይፋ ያልሆነ የአምብሳደሮች ሹመት ስለ ሙያውም ሆነ ስለ ሹመቱ ምን መረጃ የሌላቸው ትችትና ማበሻቀጥ የጀመሩት ወዲያውኑ ሹመቱ ይፋ በሆነበት ምሽት ነበር። ለማሰብና ለማጣራት እንኳን ጊዜ ሳይወስዱ ከጀርባ የአሜሪካን ህንጻዎችን በመደገፍ “ሳቄ መጣ” በሚል ለመወረፍ የሞከሩትን በስፋት እየሰሙ በላይቭ አድናቆት ሲያዘንቡ የነብሩም ታይተዋል።

“በአገራችን ሁሉንም ጉዳይ ለመተቸት ወደሁዋላ የማይሉ ደፋሮች ሳይሆኑ እነሱን ቁጭ ብሎ በየቀኑ የሚያዳምጡና በገንዘብ የሚደጉሙ ያስገርሙኛል” ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያው አቶ ይስሃቅ ሃይሉ ግርምታቸውን አኑረዋል። ” ለማሰደብ ቢያንስ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ቢጋብዙ ምን አለበት?” የሚሉት አቶ ይስሃቅ ” አንድ አናጢ ወይም የመድረክ አነጥናጭ፣ ወይም ጥሩ ድምጽ ያለው ቀዳሽ፣ወይም … ሁሉንም ጉዳይ በየሃያ አራት ሰዓቱ ሲያቸው አንዴ ፣ አለያም ሁለቴ አየር ላይ እየወጡ ያለ ሙያቸው ጥንቃቄ በሚያሻቸው ጉዳዮች ላይ ሲያቦኩ እፍረት የሚባል ነገር አይታይባቸውም። ተከታዩም ዝም ብሎ ይሞላል። አይጠይቅም? አይመራመርም? ይህ ውድቀት ነው” ብለዋል። አያይዘውም “ደግነቱ ይህ ክፍል ከ120 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ከመቶ አይሆንም” ሲሉ አደጋው እንደ ቅስቀሳው መጠንና ፍላጎት አገሪቱን ሊያነዳት እንዳልቻለ ተቁመዋል። ሙሉ ቃለ ምልልሳቸውን እናትማለን።

ይህ የአምባሳደሮች ሹመት ከፍተኛ መተን ያለውን የምንዛሬ ብክነትና የጓተተ አሰራር የሚቀርፍ ፣ ሙሉ ቤተሰብ በማጋዝ የሚባክን ሃብትን የሚታደግ ዘመናዊ አሰራር እንደሆነ በበርካቶች ዘነዳ ይታመንበታል። በተለይም በርካታ ኢትዮጵያዊያን በማይኖሩባቸው አካባቢዎች ይፈስ የነበረውን ሃብት ማትረፍ ሊበረታታ እንደሚገባ፣ ችግር ካለም እየታየ እርምት እንዲደረግበት መተቆም እንደሚገባ የገለጹም አሉ።

Exit mobile version