Site icon ETHIO12.COM

“መከላከያ የማያዳግም ሙሉ ማጥቃት ሊሰነዝር እንደሚችል ፍንጭ ሰጠ”

ሰሞኑንን በተለያዩ አውዶችና ክፍሎች የማዕረግ እድገትና የሜዳሊያ ሽልማት በማከናወን ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ከትግራይ እየተነሳ ወረራ የሚያካሂደውና በተለያዩ አካባቢዎች ትንኮሳ እያካሄደ ነው ያሉትን ትህነግን ለመምታት የማያዳግም ማትቃት ሊያካሂዱ እንደሚችሉ እየተናገሩ ነው። ለዚሁ ዕቅዳቸው ይመስላል ዓለም ዓቀፍ ተቋማትና መንግስታት በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረጋቸውን እያስታወቁ ነው።

በአፋር ክልል የተፈጸመውን ዳግም ወረራ መንግስት ለምን ዝም አለ በሚል ከፍተኛ ቅሬታ እየቀረበበት ያለው መንግስት ከነበረበት ሁሉ አቀፍ ጫናና ማየማዕቀብ ማስፈራሪያ በመነሳት ሰፊ የዲፕሎአማሲ ስራ በመስራት ላይ ስለሆነ ወዲያውኑ ጥቃት ከመሰንዘር መታቀቡን የሚጠቁሙ አሁን ላይ ጊዜው ያበቃ እንደሆነ እየገለጹ ነው።

“መንግስት የሰጠውን የሰላም ጥሪ እየጣሰ የሚገኘው ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ ተቆጥቦ ወደ ሰላማዊ መንገድ ካልመጣ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ሰራዊቱ ዝግጁ ነው” ሲሉ የመከላከያ የውጪ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ ዛሬ አስታውቀዋል። ይህን ሲሉ በሳምንት ውስጥ እሳቸው አራተኛ ከፍተኛ መኮንን ሲሆኑ፣ ይህን የተናገሩት ደግሞ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በወቅታቂ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ ሲደረግ ነው።

ከቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ጸሃፊን በዳግም ወረራው ከሶስት መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ የተፈናቀለበት አፋር ክልል ድረስ ሄደው የውንጀሉን መጠን በዓይናቸው አይተው እንዲሄዱ መደረጉ ለሚወሰደው ህዝብን የመከላከል እርምጃ ምክንያታዊነት አሳማኝ ማስረጃና መረጃ ለመስጠት እንደሆነ ገልጸን መዘገባችን ያታወሳል።

የአገር መከላከያ በየትኛውም ሰዓትና ጊዜ ሙሉ በሙሉ ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጁ መሆኑን ጀነራሉ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በወቅታቂ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ ሲደረግ በይፋ ማስታወቃቸውን የዘገበው ፋና ከስር ያለውን አስፍሯል።

ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ሀገርና ህዝብን ሲበዘብዝ ቆይቶ በመጨረሻም በህዝብ እምቢተኝነት ከስልጣን መወገዱ በገለጻው ወቅት ተነስቷል።

በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገሮችና የኢጋድ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍስሃ ሻውል፥ ሽብርተኛው ህወሓት እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ሀገር መፍረስ አለበት ብሎ ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጅ ከቆየ በኋላ የሰሜን እዝን መውጋቱን አስታውሰው፥ መንግስት ተገዶ ህግ የማስከበር እርምጃ ውስጥ መግባቱን አብራርተዋል።

ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ከጣልቃ ገብነት ነጻ ነው፣ በመግባባትና በመረዳዳት ላይ የተመሰረት ሰላምን መሰረት ያደረገ ግንኙነት ያላት ኢትዮጵያ የሰላም ሀገር መሆኗን በተለያየ ጊዜ አሳይታለች ብለዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት ቻርተር መሰረት ለተለያዩ ሀገራት በሰላም ማስከበር ላይ በመሰማራት ለሰላም ዋጋ ከፍላለች፤ ለሰላም ሁሌም ቁርጠኛ ናት ብለዋል።

ሽብርተኛው ቡድን የተሰጠውን የሰላም እድል ካልተጠቀመ ግን ሰራዊቱ በማንኛውም ጊዜ በዚህ ቡድን እርምጃ መውሰድ በሚችልበት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ጀነራሉ ይፋ አድርገዋል።

በተመሳሳይ ዜና በማራ ክልል አናንድ አካባቢዎች ትንኮሳ ስለበዛና አርሶ አደሩ በሰላም እንዳይኖር የሚፈጸመው ትንኮሳ እንደሰለቸው ያስታወቀው የአማራ ክልል ትህነግን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ ዝግጅቱን ማተናቀቁን በትናትናው ዕለት ” በቀድሞ ብአዴናዊ እነሳቤ” የሚያነክሱትን ያለ አንዳች ርህራሄ እንደሚያጸዳ ባስታወቀበት መግለጫው አመልክቷል። የአፋር ክልል ልዩ ሃይልም ከመከላከያ ጋር ተጣምሮ መንቀሳቀስ እንደጀመሩ ተሰምቷል። ይሁን እንጂ በይፋ የተባለ ነገር የለም።

የሰላም ተስፋ አለ በሚባልበት በአሁኑ ወቅት አፋር ክልልን ዳግም የወረረው ትህነግ ሶስት መቶ ሺህ ወታቶች የት እንደገቡ እንደማያውቅና ለዚህም መንግስትን ተጠያቂ ማድረጉን በወጣት ክንፉ አማካይነት ማስታወቁ ይታወሳል። ቀደም ሲል የባይቶና መሪ ከሶስት መቶ ሺህ በላይ የትግራይ ወጣቶች መሞታቸውን መግለጹ አይዘነጋም።

Exit mobile version