Site icon ETHIO12.COM

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በተከሰከሰበት ስፍራ ለሚገነባው መታሰቢያ የኢትዮጵያዊው አርክቴክት ንድፍ አሸናፊ ሆነ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737-800 ማክስ አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ በደረሰበት ስፍራ ለሚገነባው ሀውልትና ፓርክ የወጣውን ዓለም አቀፍ የንድፍ ውድድር የኢትዮጵያዊው አርክቴክት አለበል ደስታ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ግምቢቹ ወረዳ ለሚሰራው ይሄው የመታሰቢያ ሀውልት እና ፓርክ በ4 ሄክታር መሬት ላይ ሊገነባ የታሰበ ሲሆን ቦታው የማስታወሻ፣ የአረንጓዴ ቦታና የውጪ መሰብሰቢያ ስፍራ ያካተተ ነው ተብሏል።

የአርክቴክት አለበል ደስታ ድርጅት ውድድሩን በማሸነፉ የ10 ሺህ ዶላር ሽልማት ሲያገኝ ሁለተኛ የወጣው ባይቦን አማካሪ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች ድርጅት 7ሺህ ዶላር እንዲሁም በረከት ተስፋዬ አማካሪ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች ድርጅት ሶስተኛ በመውጣት የ5 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆነዋል።

አርክቴክቱ ከዚህ ቀደምም በመስቀል አደባባይ የተካሄደውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአለ ሲመት መድረክ ንድፍ እና ግንባታ በማካሄድ እውቅና ያተረፈ ባለሞያ ነው።

Exit mobile version