Site icon ETHIO12.COM

አብሮነት ፈንጂ ቀባሪዎቹን አስወግዷል፤ ሕዝብን የሚበክሉ አደብ እንዲገዙ መደረግ አለበት – ታዬ ደንደአ

የሕዝብ ወንድማማችነትና አብሮነት ጠላቶቹ ራሳቸው ባልጠበቁት ሁኔታ ጎልቶ በመውጣቱ ፈንጂ ቀባሪዎቹን እንዳስወገደ የሰላም ሚኒስትር ዳኤታ አቶ ታዬ ደንደአ አስታወቁ። በአንድነት ውስጥ ያለውን ልዩነታችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የጥላቻና የክፍፍል አመለካከትን በመዝራት የሕዝብን መልካም ጉርብትና የሚበክሉ ግለሰቦችን አደብ ማስያዝ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።



አቶ ታዬ ትህነግን በዚህ መልኩ አሽቀንጥሮ መጣል እንደሚቻል የሚታሰብ ነገር እንዳልነበር ገልጸው. ህዝብ አንድ ሆኖ ሲቀበርበት የኖረውን የጥላቻና የመጠፋፊያ ፈንጂ አምክኖ፣ ፈንጂ ቀባሪዎቹን ማስውገድ መቻሉን አውስተዋል። በተፈጥሮ ያለውን ልዩነትና ፈንጂ ቀባሪዎቹ ያኖሩትን ጥላቻ በመጠቀም አብሮነትን ሊሸረሽሩ የሚሰሩትን መላ ማለት ግድ መሆኑንንም አመልክተዋል። ከዚያ በዘለለ ግን አገራዊ ምክክሩ ታላቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶች አስከፊ የአገዛዝ ስርዓትን በሕዝብ ላይ በሀይል በመጫን ሀብቱን እንደፈለጉ ለመበዝበዝ እንዲያመቻቸው የጥላቻና የመከፋፈል ፈንጂ ቀብረው መቆየታቸውን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የክልሎች ብሎም የሕዝቦች ወንድማማችነትና አብሮነት ጠላቶቹ ራሳቸው ባልጠበቁት ሁኔታ ጎልቶ በመውጣቱ ፈንጂ ቀባሪዎቹን አስወግዷል ብለዋል። በዚህም በአገሪቱ ለውጥ ተመዝግቧል። ከለውጡ በኋላም ለድሉ ምክንያት የሆነውን የክልሎችና የሕዝቦች ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ህዝባዊ መድረኮች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

የክልሎች ሁለንተናዊ ግንኙነት በስትራቴጂካዊ መልኩ መጠናከር ለአገራዊ ምክክሩ መሰረት ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ ደንደአ ገለጹ። የሕዝቦችን ጤናማ ግንኙነትን የሚበክሉ ግለሰቦች ራሳቸውን መፈተሽ ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።

አቶ ታዬ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፤ ስትራቴጂክ በሆነ መልኩ ዘመን ተሻጋሪ የክልሎችን ግንኙነት መፍጠር ለአገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ብሎም በቀላሉ ለማይናወጥ የሕዝቦች አንድነት ወሳኝ ነው። በክልሎች መካከል ባህላዊ፣ ታሪካዊና የልማት ትስስሮችን በማጠናከር ረገድ በልዩ ትኩረት መሥራት ያስፈልጋል።

በሁሉም ክልሎች የተጀመረው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረኮች ከሁኔታዎች ጋር ሳይዋዥቁ ስርዓት ተበጅቶላቸው ማስቀጠሉ የአገራዊ ምክክሩ ግማሽ ሥራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ታዬ፤ አሁን ያሉትና ሊያጋጥሙን

የሚችሉ መሰናክሎች በክልሎቹ ጠንካራ ግንኙነት በመግታት የጋራ ተጠቃሚነታችንን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

ከጥንት ጀምሮ በሕዝቦች መካከል መልካም ግንኙነት እንደነበር የታሪክ ማስረጃዎች ቢያመላክቱም፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዋቂ ነን ባዮች ይህን የሕዝብ ግንኙነት ጤናማ እንዳይሆን ለማድረግ ጥረቶች ሲደረጉ ታይተዋል ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ልዩ ስጦታና የተፈጥሮ ጸጋ የሆነውን በአንድነት ውስጥ ያለውን ልዩነታችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የጥላቻና የክፍፍል አመለካከትን በመዝራት የሕዝብን መልካም ጉርብትና የሚበክሉ ግለሰቦችን አደብ ማስያዝ እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶች አስከፊ የአገዛዝ ስርዓትን በሕዝብ ላይ በሀይል በመጫን ሀብቱን እንደፈለጉ ለመበዝበዝ እንዲያመቻቸው የጥላቻና የመከፋፈል ፈንጂ ቀብረው መቆየታቸውን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የክልሎች ብሎም የሕዝቦች ወንድማማችነትና አብሮነት ጠላቶቹ ራሳቸው ባልጠበቁት ሁኔታ ጎልቶ በመውጣቱ ፈንጂ ቀባሪዎቹን አስወግዷል ብለዋል። በዚህም በአገሪቱ ለውጥ ተመዝግቧል። ከለውጡ በኋላም ለድሉ ምክንያት የሆነውን የክልሎችና የሕዝቦች ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ህዝባዊ መድረኮች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

እንደ አቶ ታዬ ገለጻ፤ በሁሉም ክልሎች ሕዝብ ዘንድ ያለው አመለካከት አገርን በአንድነት የመገንባት መንፈስ ነው። ምክንያቱ የሁሉም ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው በመልካም ግንኙነትና በወንድማዊ እሴት ውስጥ በመሆኑ ነው። የተጠናከረ ሕዝባዊ ግንኙነት ባይኖር ኖሮ የአሸባሪው ሕወሓት ሀይል ተሸቀንጥሮ የዛሬውን ለውጥ ማየት የሚታሰብ እንዳልነበረም ጠቅሰዋል።

ጠላት የተለያዩ መለያዎችን ለሕዝቡ በመለጠፍ ለማለያየት ቢሞክርም፤ ነገር ግን ሕዝቡ በተለያዩ መንገዶች ግንኙነቱን በማጠናከር አገርን በጋራ በማቆየት ረገድ በዚህ ትውልድም ተረጋግጧል ብለዋል።

ዛሬም ከዚህም ከዚያም የጠላት አጀንዳ ለማስፈጸም የክልሎችም ሆነ የሕዝቦችን ግንኙነት ለመበረዝ የሚታትሩ ጽንፈኞችን ሕዝቡ መታገል እንዳለበትም አስረድተዋል።

በዋቅሹም ፍቃዱ
አዲስ ዘመን የካቲት 9/2014

Exit mobile version