Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ በአውሮፓ ተደመጠች፤ ዓለም ባንክ 64 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ

አምባሳደር ሂሩት

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና ልዑካቸው በብራስልስ የአፋሪካ አውሮፓ ህብረት የጋራ ጎባኤ ኢትዮጵያ እንድትደመጥ በማድረግና ተክክለኛውን መረጃ በመስጠት ተቀባይነት ማግኘቷ ተሰማ። ዓለም ባንክ ስልሳ አራት ሚሊዮን ዶላር መስጠቱ ተገለጸ።

በአፍሪካ እና አውሮፓ ህብረት የጋራ ጉባኤ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው ሰፊ ሀሳቦች ተቀባይነት ማግኘታቸውን በቤልጂየም፣ ሉክሰንበርግና በአውሮፓ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛና አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ለኢዜአ ከሰጡት መረጃ ተመልክቷል።

ከትህነግ ጋር ኢትዮጵያ ሳትወድ የገባችበትን ጦርነትና ጦርነቱን ተከትሎ የተከፈተውን ዘመቻ ሚዛን ለማስያዝ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ አውሮፓ የገቡት የጦር መሪ ሆነው ወራሪው ሃይል በሁለት ሳምንት ውስጥ እንዲከስም ከተደረገ በሁዋላ ነው።

ሁሉም ነገር ተቀርቅሮባት በደቦ ዘመቻ ሲካሄድባት የነበረችው ኢትዮጵያ ወታደራዊ የበላይነት በመያዝ የተባለውን ሁሉ አምክና የአፍሪካ ህብረት ድርጅትን ስብሰባ ማካሄዷ የዓመቱ ታላቁ የተባለ ዲፕሎማሲያዊና ስትራቴጂካዊ ድል እንደሆነ ፖለቲከኞች ሲናገሩ ከርመዋል። ይህን ተከትሎ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ብራስልስ ያመሩት።

አምባሳደሯ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ገልጸዋል አምልከተዋል። ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የየሰአቱን ተጋባራቸውን በይፋ ሲያስታውቁ ነበር።

በአውሮፓ ታላላቅ የሚባሉትን መሪዎች፣ የህብረቱን ባልስልጣኖችና የዓለም ዓቀፍ ተቋማት አመራሪችን ፊት ለፊት በመገናነት ውይይት ማድረጋቸው ” አለቀላት፣ ፈርሳለች፣ ትህነግ መንግስት ሊሆን ነው…” የተባለው ሁሉ ተረት ሆኖ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በቅርቡ የሚታዩ የአቋም ለውጦች መሰረት መገንባቱ ተሰምቷል።

በጋራ ጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው የትብብርና የአጋርነት ሁኔታ፣ በሰላምና ጸጥታ ጉዳይ የአፍሪካ ድምጽ ስለሚሰማበት እንዲሁም የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት መሪ ቃል የተመለከቱ ጉዳዮች ተቀባይነት እንዳገኙ አምባሳሰድ ሂሩት አመልክተዋል። የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነት በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንዲሆን ኢትዮጵያ በጉባኤው ላይ ሃሳቧን እንዳራመደችም ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከተለያዩ አገሮች መሪዎች ጋር በነበራቸው የጎንዮሽ ውይይት በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለው ግንኙነት መጠናከር ስለሚኖርበት ሁኔታ ምክክር መደረጉን ጠቅሰዋል።

በዚህም ለስድስት ወር የአውሮፓ ህብረት ሊቀመንበር ከነበረችው ስሎቬኒያ እና አሁን ሊቀመንበርነቱን ከተረከበችው ፈረንሳይ መሪዎች ጋር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መወያየታቸውን አስታውሰዋል።

በጉባኤው የአፍሪካ ድምጽ በሰላምና ጸጥታ፣ ድህነትን በመዋጋት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመቀነስ፣ የታዳሽ ሃይል ልማትን በማጠናከር እንዲሁም በስደተኞች ጉዳይ የአህጉሩንና የኢትዮጵያን መብት ባስጠበቀ መልኩ ተነስቶ የጋራ መግባባት እንደተደረገበት አምባሳደር ሂሩት አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ መጠናከር ለቀጣናው መጠናከር ወሳኝ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሯ፤ በችግር ውስጥ ሆና የልማት ትልሟን ለማሳካት እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።

በመስኖ ልማት፣ በበጋ የስንዴ ልማት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በአረንጓዴ ልማትና በመሳሰሉት ሰፊ ርብርብ እያደረገች የምትገኘው ኢትዮጵያ እውነቷን ለማስረዳት መቻሏን ጠቁመዋል።

በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል አጋጥሞ የነበረው ጦርነት ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበት መሆኑን ማስገንዘብ መቻሉን ተናግረዋል። የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆነ በአግባቡ መረዳት እንዳለባቸው ለበርካታ አገራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአካል ተገኝተው ያደረጉት ምክክር አጥጋቢ እንደነበር አምባሳደር ሂሩት ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በሌላ ዜና ዓለም ባንክ ከ64 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ምስተቱ ተውቋል። የመንግስት ሚዲያዎች እንዳሉት ድጋፉ የተሰጠው በሶማሌ ክልል ለደረሰው የድርቅ አደጋ ነው።

በአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን የተመራው ልዑካን ቡድን በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ከክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባለው ሁኔታና ለድርቁ እየተሰጠ ባለው ምላሽ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

ከምክክሩ በኋላ ዓለም ባንክ በሶማሌ ክልል ለተከሰተው ድርቅ አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት የሚያግዝ 64 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ገልፀዋል።

ከተመደበው ድጋፍ ውስጥ 38 ሚሊዮን ዶላሩ አሁን የሚሰጥ መሆኑን የታወቀ ሲሆን የዓለም ባንክ በዚህ ወሳኝ ጊዜ ድጋፉን በማድረጉም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

Exit mobile version