Site icon ETHIO12.COM

ሩስያ በኢትዮጵያ የብረት ፋብሪካ ለማቋቋምና ልምዷን ማካፈል እንደምትፈልግ ገለጸች

ሩስያ በዓለም ቀዳሚ ብረት አምራች ሀገር እንደሆነችና በኢትዮጵያ የብረት ፋብሪካ ለማቋቋምና ልምዷን ማካፈል እንደምትፈልግ ገለጸች።

በሩስያ የብረት ማዕድን ጉዳዮች ተወካይ በሆኑት ሰሜኖቭ ቪክተር የተመራው ልዑክ ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሚኒስትር መላኩ አለበል ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡

ሩስያ በዓለም ቀዳሚ ብረት አምራች ሀገር እንደሆነችና ኢኮኖሚዋም በዋናነት የሚመራው በብረት ወጪ ንግድ እንደሆነ ሰሜኖቭ ቪክተር ተናግረዋል፡፡

ሩስያ በብረት ማዕድን ዘርፍ ላይ ዘርፉን የማሳደግ ብቃት ያላቸው በርካታ መሃንዲሶች እና የተማረ የሰው ኃይል እንዳላትና በኢትዮጵያም ብረት ፋብሪካ በማቋቋም ልምዷን ለማካፈል እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡

ሰሜኖቭ ቪክተር ኢትዮጵያ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ የምትገኝ በመሆኗ የወጪ ንግድን ለመሳብ ወርቃማ ዕድል ነው ብለዋል፡፡

አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው ሩስያ እና ኢትዮጵያ በወዳጅነት፣ በመተማመን እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን በማውሳት በቀጣይም ሀገራችን ከሩስያ ጋር በትብብር የመስራት ፍላጎት አላት ብለዋል።

ምንጭ: ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

Exit mobile version