Site icon ETHIO12.COM

” ከሩስያ ጋር በዩክሬን ምድር አንዋጋም፣ የኔቶ አባል አገራትን ግን ኢንች እንዳይነኩ እንከላከላለን ” አሜሪካ

ለስዊዲንና ፊላንድ የሰሜን ቃል ኪዳን አገሮች ህብረትን እንዳይቀላቀሉ ሩሲያ አስጠነቀቀች

ጆ ባይደን ግን ” የእኛ ሃይሎች በዩክሬን ውስጥ ከሩሲያ ጋር ግጭት ውስጥ አይደሉም። አይገቡበትም ” የሚል ዜና ነው ያሰሙት። ” ሰራዊታችን በዩክሬን አይዋጋም። የኔቶ አጋሮቻችንንና የኔቶ ግዛትን እያንዳንዱን ኢንች ግን እንከላከላለን ” የሚል የዩክሬን ፕሬዚዳን ተከዳን ያሉትን ሃሳብ አጽንተዋል። በሌላ አነጋገር ዩክሬን የኔቶ አባል ባለመሆኗ እንደማይዋጉላት አጉልተው አሳይተዋል።

የአሜሪካ ሽማግሌው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን ውስጥ ከሩስያ ጋር ወደ ውጊያ እንደማይገቡ በግልጽ አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንቱ በመግለጫቸው ” ፑቲን ጠብ አጫሪ አጥቂ ናቸው ፤ ይህንን ጦርነት መርጠዋል። አገራቸውም እሳቸውን ጣጣውን ይሸከማሉ ” ሲሉ ተደምጠዋል። ባይደን ሩሲያ ዩክሬንን እየተቆጣጠረች ባለችበት ለሊት ” ዓለም በጸሎቱ ከዩክሬን ጋር ነው” ብለውም ነበር።

ጋዜጠኞችን የማይለዩትና ስም እየጠሩ እድል በመስጠት የሚታወቁት ጆ ባይደን በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሉን ገልጸዋል። የዩክሬን ፕሬዚዳንት ” በሩቅ ሆነው ያዩናል፤ ተክድተናል” ሲሉ በሰጡት መግለጫ ላይ “የአስካሁኑ ማዕቀብ ምን አመጣ” ብለው ጠይቀው ” ምንም” ሲሉ ለራሳቸው በመለስ ዓለም ከዩክሬን ጎን በተግባር እንዲሰለፍ ተማጽነዋል።

እሳቸው እምባ እምባ እያላቸው ቢማጸኑም፣ አሜሪካና ኔቶን አምነው እዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ውስጥ መግባታቸው ቢታወቅም፣ ጆ ባይደን ግን ” የእኛ ሃይሎች በዩክሬን ውስጥ ከሩሲያ ጋር ግጭት ውስጥ አይደሉም። አይገቡበትም ” የሚል ዜና ነው ያሰሙት። ” ሰራዊታችን በዩክሬን አይዋጋም። የኔቶ አጋሮቻችንንና የኔቶ ግዛትን እያንዳንዱን ኢንች ግን እንከላከላለን ” የሚል የዩክሬን ፕሬዚዳን ተከዳን ያሉትን ሃሳብ አጽንተዋል። በሌላ አነጋገር ዩክሬን የኔቶ አባል ባለመሆኗ እንደማይዋጉላት አጉልተው አሳይተዋል።

ከቀድሞውቹ በተጨማሪ ሰባት ሺህ የሚሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች ወደጀርመን እንደሚያመሩ ጆ ባይደን አስታውቀዋል። አያይዘውም ” ሩሲያ በኩባንያዎቻችን ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሳይበር ጥቃቶችን የምትቀጥል ከሆነ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነን ” ብለዋል።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና የአውሮፓ ሕብረት ሦስተኛ ዙር ማዕቀብ ሲል ያስቀመጠው ማዕቀብ የሩሲያ የገንዘብና የኃይል ዘርፎችን ይበልጥ የሚጎዳ ነው ተብሏል። ይህንኑ ተከትሎ ሩሲያ መላ እንዳላት አስታውቃለች። የአጸፋ ማዕቀብ በምዕራቡ ዓለም ላይ ልትጥል እንደምትችል ይፋ አድርጋለች። ከክሬምሊን የወጣ መረጃ እንዳለው ሩሲያ ተዘጋጅታበታለች።

በቤላሩስ በኩል ሩሲያናና ዩክሬንን ለማደራደር ዝግጅት መኖሩ የተነገረ ሲሆን፤ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የድርድር ሃሳቡን የምትቀበለው የዩክሬን ወታደሮች መሣሪያቸውን ካስቀመጡ ብቻ እንደሆነ ማስታወቋን ሮይተርስ በትዊተር ገጹ ጠቁሟል። ፑቲን ወታደራዊ ሃይሉ መንግስት ቢገለብጥ ለድርድሩ ይበልጥ አመቺ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ሩስያ – ስዊድንንና ፊንላንድን አስጠነቀቀች

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዊድን እና ፊንላንድ ናቶን ለመቀላቀል እንዳይስቡ አስጠነቀቁ። ከሞከሩትም ” ጎጂ ” የሆኑ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ጣጣዎች ሊኖሩ እንደሚኖሩ አመላክተዋል። ሩሲያ ምን ተማምና በዚህ ደረጃ ልታስፈራራ እንደደፈረች ለበርካቶች እንቅፕቅልሽ ሆኗል።

Exit mobile version