Site icon ETHIO12.COM

ዜሌንስኪ በአሜሪካ የቀረበላቸውን የ”ጥፋ”ጥያቄ ውድቅ አደረጉ፤ ሕንድ፣ ቻይናና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከሩሲያ ጎን ሆኑ

ሩሲያ ላይ እንዲጸና የፀጥታው ምክር ቤት የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ሩሲያ ድምጽን በድምጽ በመሻር መብቷን በመጠቀም ውድቅ አድርጋለች። ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ወረራ አካሂዳለች” በሚል ለማውገዝ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ሩሲያ ውድቅ ስታደርገው ከ15ቱ የፀጥታው ምክር ቤቱ አባላት አስራ አንዱ እንደደገፉት ታውቋል። ሕንድ፣ ቻይናና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ደግሞ ድምጸ ታዕቅቦ ማድረጋቸው የድርጅቱ የመረጃ ቋት አስታውቋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ

ለጊዜው አገራቸው ያሉት የዩክሬን መሪ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ ከአሜሪካ የቀረበላቸውን የትብብር ጥያቄ አልተቀበሉም። ይልቁኑም በኪዬቭ ከተማ ሆነው “እኔም እዚሁ ነኝ፣ ሚኒስትሮችም፣ ሌሎችም እዚህ ናቸው … ” እያሉ አገራቸውን በመከላከል ላይ ምሀህናቸውን አመልክተዋል።

ፕሬዝዳንቱ “ውጊያው ያለው እዚህ ነው። የምፈልገው የጦር መሳሪያ እንጂ የማምለጫ መንገድ አይደለም” አሶሺየትድ ፕሬስ ሚስጢር ሰማሁ ሲል መዘገቡን ቢቢሲ አመልክቷል።

አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ለመርዳት ዝግጁ እንደነበረች ሚዲያዎች አመልክተዋል። የዩክሬን መሪ “የዓለም ሃያላን በሩቅ ሆነው ያዩናል። ዩክሬን በናቶ አባል እንድትሆን የሚወስነውና መተማመኛ የሚሰጠው ማን ነው? ሁሉም ፈርተዋል? ሲሉ ተቃውሞ አሰምተው ነበር።

የምዕራቡ አገራት በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ላይ የተለየ ማዕቀብ ከመጣላቸው ውጭ ለዩክሬን ወቅታዊ የድንገተኛ ድጋፍ፣ መሳሪያና ተዋጊ ሃይል ለማሰለፍ የወሰነ አገር የለም።

ዛሬ እንደተሰማው ፈረንሳይ ለዩክሬን መሳሪያና ቁሳቁስ ልካለች። ማክሮንና ዜሌንስኪ በትዊተር ገጻቸው ከፈረንሳይ ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በዛሬው የሰንበት ማለዳ መነጋገራቸውን አመልክተዋል። ትላንት ይፋ እንደሆነው “በዲፕሎማሲው መስክ አዲስ ግንባር ተከፍቷል” መከፈቱን ገልጸዋል። ቃል በገቡላቸው አገራት የመከዳት ስሜት ውስጥ መግባታቸውን ሳይደብቁ ያስታወቁት ፕሬዚዳንቱ በዲፕሎማሲው መንገድ አዲስ ግንባር መከፈቱን ቢያስታውቁም ዝርዝር ነገር አልተሰማም። ፕሬዚዳንት ፑቲን ይትጦር ሃይሉ መንግስትን አባሮ ለድርድር ቢቀርብ ለመግባባት ይበልጥ አመቺ እንደሆነ መጥቀሳቸው አይዘነጋም። ማክሮን ውጊያው ረዥም ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ጠቅሰው ዝግጅት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ቢቢሲ ከድምጻቸው ሰማሁ ሲል ዘግቧል።

በዩክሬኗ ዋና ከተማ ኪዬቭ ውስጥ የጎዳና ላይ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የዩክሬን መንግሥት አስታወቀ – ቢቢሲ

የአገሪቱ የዜና ወኪል ኢንተርፋክስ መንግሥት ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበው “በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ውጊያ እየተካሄደ ነው” ብሏል።

መንግሥት ጨምሮም የከተማዋ ነዋሪዎች በመጠለያ ቦታዎች ላይ እንዲቆዩ ወደ መስኮቶችና በረንዳዎች እንዳይቀርቡም አስጠንቅቋል።

ሌሊቱን በዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ ውስጥ ፍንዳታዎች መሰማታቸውና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ውጊያዎች እንደተካሄዱ የሚያመለክቱ ዘገባዎች እየወጡ ነው።

በዋና ከተማዋ ውስጥ በሚገኘው ሜይዳን አደባባይ አቅራቢያ ከባድ ፍንዳታ የተሰማ ሲሆን፣ ትሮዬሽቺይና በሚባለው አካባቢ ደግሞ በርካታ ፍንዳታዎች መከሰታቸው ተዘግቧል።

የዓይን እማኞች እንዳሉት ከዋና ከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል ሆነው ከፍተኛ የመድፍ ፍንዳታዎችን በቅርብ ርቀት እንደሰሙ ተናግረዋል።

አንድ ዘገባ እንዳመለከተው በከተማዋ ውስጥ ከ50 በላይ ፍንዳታዎችና ከባድ የመትረየስ ተኩስ ተሰምቷል። ኪዬቭ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በሩሲያ ሠራዊት ጥቃት ተከፍቶባታል።

የዩክሬን መንግሥት ባለሥልጣናት እንዳሉት በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ውጊያዎች እየተካሄዱ ሲሆን ከተማዋ የኤሌክትሪክ ኃይል የምታገኝበትን አካባቢ ለመቆጣጠር ውጊያ እየተደረገ እንደሆነ ተነግሯል።

ሩሲያ ኮማንዶዎቿን በቀላሉ ወደ ኪዬቭ ለማስገባት ያስችላታል የተባለውን የቫዚልኪዬቭ አየር ማረፊያን ለመቆጣጠር ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው።

የዩክሬን ኃይሎች በጥቁር ባሕር አካባቢ በምትገኘው ማይኮሌቭ ከተማ ላይ በሩሲያ ሠራዊት የተሰነዘረውን ጥቃት መክተው መመለሳቸውን ተናግረዋል።

Exit mobile version