Site icon ETHIO12.COM

በ2020 “ይወድማል” የተባለው ብልጽግና፣ ከትህነግ ጋር የሚሰሩትን ጎርዶ እንደሚጥል አስታወቀ

ከተመሰረት ሶስት ዓመት ያልሞላው ብልጽግና ” እሳት ውስጥ ያላች ነፍስ” ሲሉ የሚጠሩት በርካቶች ናቸው። ሕዝብና በኢህአዴግ ውስጥ የተነሳው የለውጥ ሃይል በአንድነት ለውጥ በተቀዳጁ ማግስት ለውጡን የሚመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ያሰሙት ንግግር በድፍን ኢትዮጵያ፣ በመላው ዓለም፣ በእያንዳንዱ ቤትና ህሊና ውስጥ ተስፋን ያጋመ ቢሆንም፣ ከዚህ ስሜት ጎን ለጎን የተጠነሰሰ ሴራም ነበር።

ብልጽግና ዛሬ ላይ ደርሶ እንኳን ጉባኤ ሊያካሂድ በ2020 ከምድረ ገጽ እንደሚወገድ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መረሃ ግብር አዘጋጅቶለት ነበር። ትግራይ ኦንላይን “2020 will be the end of the illegal Prosperity party and the birth of victorious real Federalist Forces in Ethiopia” በ2020 ብልጽግና አክትሞለት ድል አድራጊዎቹ እውነተኛ የፌደራሊስት ሃይሎች ይወለደሉ” በሚል እርዕስ በስፋት እንዳብራራው ” የትህነግ ውሳኝ ውሳኔ የፌደራሊስ ሃይሎችን በማሰባሰብ የፈረሳቸዋን ኢትዮጵያን መልሶ መገንባት ነው» ሲል መርሃ ግብሩን ጠቅልሎ ማስፈሩ በ360ና በሌሎች ሚዲያዎች በስፋት ሲነገር እንደነበር አይዘነጋም።

ለውጡ ይፋ እንደሆነ አፍታም ሳይቆይ አበባ እየተነጠፈላቸው የገቡትን ጨምሮ ሁሉም የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ” እኛ ነበርን አሸባሪዎች” ሲሉ ይቅርታ በመጥየቅ መድረኩን ክፍት አድርጎ የጋበዘው የለውጡ አመራር በብርሃን ፍጥነት ኢህአዴግ የሚባለውን በዘርና ጎሳ ላይ የተተከለ ድርጅት አከስመ።

ዘረኝነትን በህዝብ ሃብት እየሰበከ፣ ልዩነትን እያስተማረና የጎሳ አስተሳሰብን እያሰረጸ ቀስ በቀስ ኢትዮጵያዊነትን የበላውን ኢህአዴግን በበላይነት ሲነዳው የነበረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ “ብልጽግና አሃዳዊ ነው” ብሎ ከትግራይ ምሽጉ አፍታም ሳይቆይ ዘመቻ ከፈተ። መቀለ በትግርኛ ንግግር አድርገው የተጨበጨበላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ” የትግራይን ሕዝብ ሊያጠፉ የተነሱ” በሚል የፕሮፓጋንዳ ሚሳኤል ከትግራይና ከዛው ከሚቀዳው ዘፈን ጋር ተጋምደው የሚሰሩ ያዘንቡ ጀመር።

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል ዶክተር አለሙ ስሜ ለውጡ ይፋ በሆነ ማግስት በየአካባቢው እሳት ይነድ ጀመር። ቀጥሎም ይፋ የሆነ ወረራ ተፈጸመ ሲሉ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በነጻ አውጪ ስም ሲጠራ የኖረውን ትህነግን “የለውጡ ነቀርሳ” ሲሉ ይጠሩታል።

ሰሞኑንን ከፋና ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዳሉት ከሆነ ብልጽግና ስሙ እንጂ በትክክል ፓርቲው አልተመሰረተም። ከልውጡ ማግስት ጀምሮ እዛም እዚህም እሳት ሲለኩስና ሲያስለኩስ የነበረው ትህነግ፣ የኮቪድ ወረሽኝ፣ አንበጣና በዚሁ በአኩራፊው ትህነግ የተካሄደው ወረራ ፓርቲው ብልጽግናን እንዳይሆን አድርጎታል።

እሳቸው ባነሱዋቸው ምክንያቶች ፓርቲው ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ላይ አደረጃጀቱን ቀይሮ በአምለካከት ደረጃ የተቀየረና የበቃ መሪ ሳይደራጅ እያነከሰ ዛሬ ላይ የደረሰው ብልጽግና ” ተቸካይ” በሚብሉ የዘረኛ እምነት አራማጆች መተብተቡን፣ የበላይ አመራሩ ሳይቀር ያልጸዳና የትህነግን ዓላማ የሚያስፈጽም የተቀላቀለበት እንደሆነ ዶክተር አለሙ በግልጽ አስቀምጠዋል።

ከለውጡ ጀመሮ የማሰቢያ ጊዜ የተከለከለውና “ተቸካይ” በሚባሉት ተላላኪ አመራሮቹ አማካይነት በችግር ላይ ችግር እየተመረተለት ዛሬ ላይ የደረሰው ብልጽግና፣ አሁን ላይ ምርጫ ቦርድ ባስቀመተው የጊዜ ገደብ መሰረት ጠቅላላ ጉብኤውን ለማካሄድ ደፋ ቀና እያለ ባለበት ወቅት ከዛና ከዚህ ፍትጊያው በርትቷል።

ይፋ ያልሆኑ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ብልጽግና “ተቸካይ” የሚላቸውን የዘር ፖለቲካ አራማጆች፣ ሌቦችና ብቃት የሌላቸውን ይቆርጣል። ዶክተር አለሙ ስሜ ” አዘኔታ የለም። የሚቆረተው ይቆረጣል” ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ማስተማርና የሰዎች ልማት ላይ ትኩረት ቢደረግም መለወጥ የማይችሉት ላይ የመግረድና የማጽዳት እርምጃ ይወሰዳል። እንደ እሳቸው አባባል አራት “ማ” ዎች አሉ። ማስተማር፣ ማበልጸግ፣ ማሳደግና ማስወገድ፤

ከጉባኤው በሁዋላ ብልጽግና የሆነ፣ የብልጽግናን ዓላማ መሸከምና ማስፈጸም የሚችል፣ የበቃ፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ተፈትነው ያለፉና የተመሰከረላቸው አመራሮችን ጉባኤው እንደሚሰየም ዶክተር አለሙ አምለክተዋል።

ከሰላምና ጸጥታ አንጻር ” ታሪክና የክልል መንግስታት ወደፊት ምስክር ይሰጡበታል” ሲሉ ስሜታቸውን እያነቃቸው ” በኦሮሚያ ሙሉ ካቤዎች ያለቁበት ሁኔታ አለ። በርካታ ሃላፊዎችና የጸጥታ አካላትም አልፈዋል” ሲሉ ትህነግ የሚረዳውና የሚያስታጠቀው ሸኔ በደፈጣ ያደረሰውን ጉዳት አመልክተዋል።

ትህነግ አፋርና አማራ ክልልን ሲወር አላማው አገሪቱን መበተን እንደነበር አስታውሰው፣ አዝማሚያው ለጊዜው የሚባል ስላልነበር ከሁሉም አካባቢዎች የመከላከያና የፌደራል ሃይል በማንሳት ወደ ሰሜን በመንቀሳቀሱ የአገር ብተናውን ለመመከት በነበረው ርብርብ ሳቢያ ሸኔ ሊራባ እንደቻለ ጠቁመዋል። ይህ ለማንም አዕምሮ ላለው ገሃድ መሆኑንን ያመለከቱት ዶክተር አለሙ፣ የአሸባሪውን ትህነግን ወረራ ለአፍታ ቸል ቢባል ኖሮ ዛሬ ኢትዮጵያ ብሎ መነጋገር ተረት ይሆን እንደነበር ገልጸዋል።

በየአካባቢው እሳት እሳት እየለኮሰ ሴራውን ሲገምድ የኖረው ትህነግ ለይቶለት ያካሄደውን የሽብር ተግባር መቀልበስና ማስተንፈስ ከተቻለ በሁዋላ ሰፊ የጸጥታ ማስከበር ስራ በጥምረት እየተሰራ መሆኑንን ዶክተር አለሙ አስታውቀዋል። በየአካባቢው የሸኔ ሃይል እየተመታና እየተመናመነ መሆኑ ገልጸዋል። ሆኖም ግን ሰፊ የፖለቲካ ስራ መሰራት እንደሚገባ፣ ፓርቲውን ማጽዳት አስፈላጊ እንደሆነ፣ አሁን የሚደረገው የመጀመሪያ ጉባኤ አዲስ አመራር እንደሚያፈራ፣ በአገር ደረጃም ልዩነትና የሚያሻኩቱ ጉዳዮችን ተመካከሮ የጫካ ውስጥ የነውጥ ትግልን ለመጨረሻ ጊዜ ላማስወገድ ጥረት መጀመሩን አመልክተዋል።

በፓርቲያቸው ውስጥ አፈገኛ የሚባል ሌብነት መኖሩን ያልሸሸጉት ሃላፊው በሰፊው ምክክርና ምርመራ የተደረገበት ጉዳይ በመሆኑ እገሌ ከገሌ ሳይባል እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።

ሲወለድ ጀምሮ ከመከራ ያልተለየው ብልጽግና እንኳን ጉባኤ ሊያካሄድ፣ በየአካባቢው የተለኮሰውን እሳት በማጥፋት ይተወጠረ፣ ተፍናቃዮችን በመመለስና እርዳታ በማመላለስ የተጠመደ፣ የሚቀያየር ሴራ እየተዘጋጀለት ሲዳክር የቆየ፣ ራሱን ለማጽዳት እንዳይችል ፋታ የተከልከለ፣ ከተፈጥሮ ጀምሮ በሴራ የተተበተበ፣ በሁለት እሳቤ የሚያነክሱ ተስፈኞችን እንዳያራግፍ መሰናክል የበዛበት፣ አንዱን ሲል ሌላው ችግር እየተቀበለው የሚፈታተነው፣ ሙሉ ጦርነት የገረፈው፣ በጦርነቱ ስሜት አሁንም እየተለበለበ ያለ፣ በዚህ ሁሉ ውስጥ እያለፈ ሴረኞች የፕሮፓጋንዳ ዘመቻቸውን የሚያወርዱበት፣ በተቀናቃኞች ምን ቢያደርግ የማይመስገን፣ በገሃድ አባይን ሸተ፣ መስቀል አደባባይን አፈራረሰ፣ ቅርስ አበላሸ፣ ወልቃይትን ሰጠ ወዘተ እያሉ የሚሰድቡት አካሎች አባይ ሲያበራ፣ መስቀል አደባባይ አምሮ ሲመረቅ፣ ወልቃይትም እንዳለ ሲቆይ፣ ወደመ የተባለው ቅርስ ይበልጥ እንዲዋብ ሲደረግ ይቅርታ አልተጠየቀም።

በውስን ጽንፈኞች ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ያለማቋረጥ የሚዘንብበት ብልጽግና አሁን ላይ በኢኮኖሚ ጉዳይና በኑሮ ዋጋ ንረት እየታሸ ይገኛል። ጦርነቱን ተከትሎ “ሃያላን” የሚባሉት አገራት በደቦ ያሳደሩት ጫና፣ አሻጭረኛ ነጋዴዎችና በብልጽግና ውስጥ የተከማቸው የቀደመው አመለካከት አራማጅ አሰስ ገሰስ በጣምራ አልጋ ስር ሳይቀር ዘይት በመደበቅ ፓርቲውን ለመገርሰስ እያደቡ ነው።

የትህነግ ትራፊና አሽከር ሚዲያዎች ገና መቋቋሙ ያልተነገረለትን የቤራዊ የምክክር ኮሚሽን “ስልጣን እንደሚለቅ አስጠነቀቀ” በሚል የሽብር ዜና ሊያስተዋውቁት ቢከጅሉም፣ መንግስት ” ለአገር የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ በበርካታ ጉዳዮች ላይ አዎንታዊ መግባባት ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ” ሲል ሙሉ ደጋፉን እንደሚሰጥና ጣልቃ እንደማይገባ የኮሚሽኑ አመራሮች ሳይናገሩ ይፋ ማስታወቁን ራሳቸው መስክረዋል።

ዶክተር አለሙም ያሉት ይህንኑ ነው። ፓሪያቸውን በብቃት የሚመሩ አመአሮችን ከመሰየምና ከማጥራት ጎን ለጎን ለአገራዊ መክክሩ እጅግ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚደረገና፣ የጫካ ትግል የሚባል ነገር እንዲያከትም እንደሚሰራ ያስታወቁት። በዚህ አገራዊ የመግባባት አጀንዳ ድባብ ውስጥ ብልጽግና ራሱን አጥርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ “ብልጽግና” የሚባለውን ፓርቲ በአሰትሳሰብ ጽዳት ላይ እንደሚያቆም አመልክተዋል። ይፋ አያድርጉት እንጂ ብልጽግና አዳዲስ አመራሮች ወደ ፊት እነደሚያመጣ ፍንጭ ሰጥተዋል። ያዛኑ ያክል የፓርቲውን ስብሰባ ለዩቲዩብ ጉሊት ገበያ የሚሸጡ አቃጣሪ አመራሮችም ከመጎረዳቸው በፊት እየተወራጩ ነው።

ዶክተር አለሙ እንደሚሉት ከሆነ ብልጽግና ማናቸውንም ዓይነት ውሳኔ ለወሰንና ተጋባራዊ ለማድረግ ሙሉ አቅም አለው። ሲጎረድ ብሄር ውስጥ በመወሸቅ ” እኔ ለዚህ ብሄር ይህን በማድረጌ ነው” በሚል የዘር ምሽግ ለመማበጀት የሚሞክሩ ካሉ የሚጎረዱበት ምክንያት ለህዝብ ይፋ ስለሚሆን ብዙም እንደማያሳስብ ገልጸዋል።

እንደሚሰማው ከሆነ መጠነኛ ችግር የሚስተዋለው በአማራ ብልጽግና በኩል ሲሆን ፓርቲው ራሱን ማጽዳት ካልቻለና አደጋው ቅድሚያ ለአማራ ህዝብ ይህናል። ሚዲያ ተቀራምተው አንዱ ሌላው ላይ ዘመቻ እያስከፈተ ክልሉን ለዳግም ፈተና እንዳይጥሉት ስጋት ያላቸው አሉ።

ብልጽግና ዛሬ ላይ ደርሶ እንኳን ጉባኤ ሊያካሂድ በ2020 ከምድረ ገጽ እንደሚወገድ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መረሃ ግብር አዘጋጅቶለት ነበር። ትግራይ ኦንላይን “2020 will be the end of the illegal Prosperity party and the birth of victorious real Federalist Forces in Ethiopia” በ2020 ብልጽግና አክትሞለት ድል አድራጊዎቹ እውነተኛ የፌደራሊስት ሃይሎች ይወለደሉ” በሚል እርዕስ በስፋት እንዳብራራው ” የትህነግ ውሳኝ ውሳኔ የፌደራሊስ ሃይሎችን በማሰባሰብ የፈረሳቸዋን ኢትዮጵያን መልሶ መገንባት ነው» ሲል መርሃ ግብሩን ጠቅልሎ ማስፈሩ በ360ና በሌሎች ሚዲያዎች በስፋት ሲነገር እንደነበር አይዘነጋም።

Exit mobile version