ዳንኤል ክብረት በግሉ ምርጫ ይወዳደራል ፤ ብልጽግና ታዋቂ ሰዎችን ለእጩነት ለማቅረብ እየጣረ ነው

ዋዜማ ራዲዮ- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሀይማኖት መምህርነቱና በሚሰጣቸው ማህበራዊ ሂሶች ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመጪው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በግሉ እንደሚወዳደር ዋዜማ ራዲዮ ሰምታለች።

ዳንኤል ክብረት ምርጫውን የሚወዳደረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር ለማግኘት ሲሆን ፣ የሚወዳደረውም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ባለ የምርጫ ክልል መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሀይማኖት መምህርነቱ በስፋት የሚታወቀው ዳንኤል በርካታ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሂሶችንና ታሪኮችን የያዙ መጻህፍትን ለአንባቢያን ያደረሰ ነው። አንደበተ ርቱዕና በአማኒያን ዘንድም ትልቅ ክብር የሚሰጠው ነው።

በኢትዮጵያ በ2010 አ.ም መጋቢት ወር የፖለቲካ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ዳንኤል ክብረት ከመንግስት ጋር በቅርበት እየሰራ ከመሆኑም ባለፈ በሚኒስትር ዲኤታ ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሆኖም እያገለገለ ይገኛል። ከዚህ በመነሳትም ምርጫ የሚወዳደረው ብልጽግና ፓርቲን ወክሎ ነው በሚል ብዙዎች ቢገምቱም በግሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚወዳደር ነው ዋዜማ ራዲዮ የሰማችው።

ዳንኤል ክብረት መንግስትን አሁን ላይም እያገለገለ ያለው ከፓርቲ ነጻ ሆኖ በፈቃደኝነት ስለሆነ ምርጫውን በግሉ መወዳደር የፈለገው ከዚህ መነሻ መሆኑንም ነው የሰማነው።

ዳንኤል ክብረት በተለይ ከመንግስት ጋር በቅርበት መስራት ከጀመረ ወዲህ የብዙ ውዝግቦች መነሻ ሆኗል። ዳንኤልን በቀደመ የሀይማኖት ስብከቶቹና አሁንም በየመድረኩ በሚያንጸባርቀው አቋሙ “ጸረ ብዝሀነትን ያራምዳል : የቀደመ ስርአትን ይናፍቃል : ጸረ ፌደራሊዝም” ነው እያሉ የሚተቹት አሉ።

ባለፈው አመት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባልነት እንዲጸድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግስት እጩ ሆኖ ሲቀርብም በምክር ቤቱ አባላት ተመሳሳይ ትችት ሲቀርብበት ተሰምቷል።

ከትችቱ ባሻገር ዲያቆን ዳንኤል የጠቅላይ ሚንስትሩ የቅርብ ሰውና በኣአደባባይ ሙግት ስማቸው ከሚጠራ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች አንዱ ነው።

ብልጽግና ታዋቂዎችን ለእጩነት ለማቅረብ እየሰራ ነው

ብልጽግና ፓርቲም ለዚህኛው አመት ምርጫ ታዋቂ ግለሰቦችን እጩ አድርጎ ለማቅረብም እየሰራ ነው።ከነዚህም ውስጥ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ክብር የሚሰጠው ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ይገኝበታል። ኡስታዝ አቡበከር በአዲስ አበባ ቤተል አካባቢ ብልጽግና ፓርቲን ወክሎ እንዲወዳደር በፓርቲው እንደሚፈለግ በተደጋጋሚ እንደተገለጸለት ከታማኝ ምንጮቻችን የሰማን ሲሆን ከአቡበከር በኩል ግን ለብልጽግና ፓርቲም ምላሽ አልሰጠም።

አቡበከር መሀመድ በህወሀት መራሹ የኢህአዴግ አስተዳደር ጊዜ የመንግስትን በሀይማኖት ጣልቃ መግባት በመቃወሙ ለአመታት መታሰሩ የሚታወስ ነው።

ከጋዜጠኞችም በፋና ቴሌቭዥን የምትሰራው ሰላማዊት ካሳም ብልጽግና ፓርቲን ወክላ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት እንደምትወዳደርም ሰምተናል።

ብልፅግና ህዝብ ሊቀበላቸው ይችላሉ ያላቸውን ባለሀብቶችን ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች በማግባባት ዕጩ አድርጎ ለማቅረብ ሰፊ ዘመቻ መጀመሩንም ተረድተናል። [ዋዜማ ራዲዮ]

 • ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ
  ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከምትታወቅባቸዉና ከምትከበርባቸዉ ሀገራዊ ልዩ እሴቶቿ ዉስጥ አንዱ የዘርፈ ብዙ ልዩነቶች የመቻቻል ምድር መሆኗ ሲሆን ህዝቦቿ በፈረሃ አምላክ የሚመሩ ናቸዉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን የሀይማኖት ብዝሃነትን […]
 • Ethiopia tows 2.3bln USD remittance a year less
  ADDIS ABABA – Ethiopian Diaspora Agency disclosed that the country has secured 2.3 billion USD in remittance from the Diaspora over the past eight months. Agency Director-General Selamawit Dawit told the […]
 • Ethiopia, World Bank seal 200 mln USD loan agreement
  ADDIS ABABA—Ethiopia and World Bank signed 200 million USD loan agreements to support the implementation of Digital Foundation project. As to the information obtained from the Ministry of Finance and […]
 • የቆዳ ዋጋ መውደቅና አገራዊ ኪሳራው
  ድሮ ድሮ በደጋጎቹ ዘመን “ጮሌዎቹ” በግ ከአርሶ አደሩ በስሙኒ ገዝተው ቆዳውን መልሰው በስሙኒ በመሸጥ ስጋውን በነጻ “እንክት” አድረው ይበሉ ነበር ይባላል። ታዲያ የስጋን ያህል ዋጋ ያወጣ የነበረ የቆዳ ዋጋ ከቅርብ […]

Categories: NEWS

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s