ETHIO12.COM

መከላከያ ዝግጁ መሆኑንን አስታወቀ፤ “ለትውልድም የቤት ስራ አናቆይም” መከላከያ

የምድር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ የሰው ሀብት ም/አዛዥ ሜ/ጀነራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን ” የጠላቶቻችን ግብአተ መሬት ሳይፈፀም የሚታጠፍ ክንድ የለንም፤ለትውልድም የቤት ስራ አናቆይም” በማለት ወቅታውቂውን የተቋሙን ሲያስታውቁ፣ መከላከያ የተጣለበትን ህዝባዊ ሀላፊነት በብቃት ለመፈፀም በሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ህብረት የሰዉ ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተና ጄኔራል አጫሉ ሸለመ አስታውቀዋል።

ሰሞኑንን የትህነግ አመራሮች በወልቃይት በኩል ጥቃት ለመሰንዘር እቅድ እንዳላቸው በስፋት በሚነገርበት ወቅት የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በአንድ ቀን ውስጥ ይህን ማለታቸው የዝግጅቱን መጠን የሚያሳይ መሆኑንን ታዛቢዎች ገልጸዋል። በተመሳሳይ ለሰላም የሚደረገው ዝግጁነት እንዳለ ሆኖ ትንኮሳው ከቀጠለ መልስ እንደሚሰጥ አመላካች መሆኑም ተመልክቷል።

አዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን የተለያዩ የሜካናይዝድ ምድብተኞችንና አሽከርካሪዎችን ባስመረቀበት ስነ ስርዓት ላይ ሃላፊ መኮንኖቹ እንዳስታወቁት መከለከያ ለማናቸውም ዓይነት ግዳጅ ዝግጁ ነው። የትህነግ ወረራ ከተቀለበሰ በሁዋላ በተላይዩ አጋጣሚዎች የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች መከላከያ በምድር ሃይሉ፣ በሚካናይዝድ፣ በአይርና በባህር ሃይል በከፍተኛ ደረጃ እየተደራጀ መሆኑን መተደጋጋሚ ሲያስታውቁ እንደነበር ይታወሳል።

በምረቃው ዝግጅት ላይ የተገኙት የምድር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ የሰው ሀብት ም/አዛዥ ሜ/ጀነራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን ፣ የጠላቶቻችን ግብአተ መሬት ሳይፈፀም የሚታጠፍ ክንድ ስለሌለን ተመራቂዎች በቀጣይ በሚመደቡበት ክፍል የሚሰጣቸውን ግዳጅ በቁርጠኝነትና በፅናት እንዲወጡ አሳስበዋል።

የአዋሽ ውጊያ ቴክኒክ ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥ ብ/ጄ ተመስገን አቦሴ ፣ ጠላቶቻችን የሀገራችንን የለውጥና የዕድገት ጉዞ ለማደናቀፍ ጠንክረው እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀው ፣ የማሰልጠኛ ማዕከሉ እነኝህን የፀረ ሰላም ሀይሎችን ለማጥፋት አቅም ፈጣሪ አቅም ለመሆን በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ መስፈርቱን ያሟሉ ወጣቶችን በመመልመል በሜካናይዝድ ወታደራዊ መኮንንነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ ፣ ይህም ተተኪ የሜካናይዝድ አመራሮችን ለማፍራት ከፍተኛ ሚና እንዳለው አረጋግጠዋል ። በስነ-ስርዓቱ ላይ በተመራቂ ምድብተኞች የተለያዩ የሜካናይዝድ ትዕይንቶች ቀርበዋል።

በተመሳሳይ የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት የተጣለበትን ህዝባዊ ሀላፊነት በብቃት ለመፈፀም በሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ህብረት የሰዉ ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተና ጄኔራል አጫሉ ሸለመ አስታውቀዋል።

ሌተና ጄኔራል አጫሉ ሸለመ

በምረቃው ስነ-ስርዓት በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ህብረት የሰዉ ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተና ጄኔራል አጫሉ ሸለመ

ባስተላለፉት መልእክት የዕለቱ ተመራቂዎች ወታደራዊ ስልጠናችሁን በብቃት በማጠናቃችሁ እና የድል አድራጊው ሰራዊት አባል በመሆችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ቆይታችሁ የቀሰማችሁትን ወታደራዊ ዕዉቀት ወደ ተግባር በመቀየር ህዝብ እና መንግሥት የሰጧቸውን አደራ በቅንነትና በታማኝነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

እንደ ሌተና ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ገለፃ የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ጠላቶች እኩይ ሴራ ለማክሸፍ እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም በተሟላ የዝግጁነት ቁመና ላይ ይገኛል።

የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ የስልጠና ሪፖርት ባቀረቡበት ወቀት እንደተናገሩት የዕለቱ ተመራቂዎች በት/ቤቱ ቆይታቸው በቀጣይ የሚጠብቃቸውን ተልእኮ ግምት ውስጥ ያስገቡ በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የተደገፉ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ስልጠናዎችን መከታተላቸውን ገልጸዋል።

በሻለቃ ወንድማገኝ ታደሰ – ብፎቶግራፍ ሻለቃ ወንድማገኝ ታደሰ

Exit mobile version