Site icon ETHIO12.COM

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር የሞክሩ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ተማሪዎች እና በግቢው ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፤ የጸጥታ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ከከተማው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ተማሪዎች እና በግቢው ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይም ዩኒቨርሲቲው መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባሩ እንደቀጠለ ፕሬዚዳንቱን ጠቅሶ የዘገበው ኢፕድ ነው። በኢፒድ ዘገባ ባይጠቀስም ሰሞኑንን በተላያዩ አውዶች ስሙ አይጠቀስ እንጂ መዋቅራቸውን ተጠቅመው ረብሻ እንደሚጀሙ ራሳቸውን ተቆርቋሪ ያደረጉ ክፍሎች ሲያስታውቁ ነበር። መንግስትም መረጃው እንዳለው አውቆ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ አይዘነጋም።

Exit mobile version