ከአዲስ አበባ ለህብረተሰቡ የሚውለውን የምግብ ዘይት በድብቅ ይዘው ለማሸሽ የሞከሩ ህገወጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በትናንትናው እለት ለሊቱን ከአዲስ አበባ ለህብረተሰቡ የሚውለውን የምግብ ዘይት በድብቅ ይዘው ለማሸሽ የሞከሩ ህገወጦችን ግብረ-ሃይሉ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡

ሆነ ብለው መንግስትንና ህብረተሰቡን ለማጋጨት እና ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረትን በመፍጠር ህዝቡን ለማስጨነቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሃይሎች በመኖራቸው ህብረተሰቡ በየአካባቢው ጥቆማዎችን ለመንግስት አካላት እንዲያቀርብ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው አለአግባብ የምግብ ፍጆታዎችንና ሌሎች ጥሬ እቃዎችን የሚሸሽጉና የሚያሸሹ ደላሎችንና ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ግብረ ሃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል ሲል የከንቲባ ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡

Leave a Reply