Site icon ETHIO12.COM

በየቀኑ የአየር በረራ ወደ ትግራይ እንዲደረግ ተወሰነ – በየብስ ማጓጓዝ መጀመሩ ታወቀ

ወደ ትግራይ ክልል በሳምንት 2 ጊዜ ይደረግ የነበረው የአየር በረራ በየቀኑ እንዲደረግ ለተለያዩ ዓለምአቀፍ የሰብአዊ ርዳታ አቅራቢ ተቋማት ፈቃድ ተሰጠ፡፡ ከመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የወጣው መግለጫ እንደሚከተለው፤ «የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን ለማሳለጥና በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ ለሰብአዊነት ሲባል ግጭት መቆሙን ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ውሳኔው ከተወሰነበት ቀን አንስቶ የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ ርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ በሳምንት ሁለት ጊዜ ይደረግ የነበረውን የአየር በረራ በየቀኑ እንዲደረግ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ርዳታ አቅራቢ ተቋማት ፍቃድ ሰጥቷል፡፡
በዚህም መሠረት የመድኃኒት፣ የሕክምና መሣሪያዎች፣ ገንዘብና አልሚ ምግቦችን ረጂ ድርጅቶች በቻሉት መጠን በአየር ትራንስፖርት መጓጓዝ ጀምረዋል፡፡ ሌሎች በአየር ትራንስፖርት ሊጓጓዙ የሚችሉ የሰብአዊ ድጋፎችን እንዲያጓጓዙም የኢትዮጵያ መንግሥት ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ከዚህ አኳያ በረጂ ድርጅቶች አቅም ማነስ ወይም በራሳቸው አሠራር ሥርዓት የመዘግየት ሁኔታ ካልገጠመ በቀር በመንግሥት በኩል ፈጣን ርምጃ ተወስዷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ሕይወት ለመታደግ የትኛውንም አማራጭ በመጠቀም የርዳታ አቅርቦቱ እንዲሳለጥና ዜጎች በተረጋጋ ሁኔታ ኑሮአቸውን እንዲመሩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ቀና ተባባሪ ይሆናሉ ብሎ ተስፋ ያደርጋል፡፡» via DW

በአፋር ክልል በአብኣላ መንገድ የሰብአዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ ተጀምሯል

በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከበድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ መንገድ የሰብአዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሰታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም የሰብአዊ እርዳታን ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩ የሚታወስ ነዉ፡፡

ዉሳኔዉ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ የመድኃኒት፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ገንዘብና አልሚ ምግቦችን ረጂ ድርጅቶች በቻሉት መጠን በአየር ትራንስፖርት በየእለቱ መጓጓዝ መጀመራቸዉንም ማሰወቃችን ይታወሰል፡፡

በዛሬዉ ዕለት ደግሞ በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከበድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጨን በአፋር ክልል በአብኣላ መንገድ የሰብአዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በተሟላ ሁኔታ ለማስኬድ ከተባበረና ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት ዛሬም ቁርጠኛ መሆኑን በድጋሚ ያሳውቃል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Exit mobile version