Site icon ETHIO12.COM

“ትህነግ ሰብዓዊ የእርዳታ ማጓጓዙን እያስተጓጎለ ነው” ዲና ሙፍቲ፤ “በቀን 300 ተሽከርካሪ እርዳታ ያስፈልጋል”ትህነግ

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑንን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ። ዶ/ር አትንኩት የሚባሉ የትግራይ ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ በቀን 300 ተሽከረካሪዎች እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ መግባት እንዳለባቸው አስታውቀዋል። የትግራይ ሕዝብ ከመንግስት እርዳታ የማግኘት መብት እንዳለውም ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ የሰብአዊ እርዳታ በሮችን ክፍት ለማድረግ መወሰኑን ተከትሎ የእርዳታ ምግብና ነዳጅ የጫኑ ተሽካርካሪዎች ትግራይ እና አፋር የመድረሳቸው ዜና ያስደሰታቸው መሆኑን ቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዱያሪች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡ ዋና ጸኃፊ ሁሉም ወገኖች እርዳታውን ለሚፈልጉ ሰዎች ተደራሽነትን ለማመቻቸት የገቡትን ቃል በማክበር የጀመሩትን ጥረት እንዲገፉበት አሳስበዋል፡፡በትግራይ የባንክ፣ የመብራትና የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን ጨምሮ የንግድ አገልግሎት ተደራሽነት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱም በድጋሚ ጥሪ ማድረጋቸውን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወደፊቷን ሰላማዊና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመርዳት ከዚህ በፊት የገባውን ጽኑ አቋም በድጋሚ እንደሚያረጋግጥ አመልክቷል።

የቪኦኤ ዘገባ ነው – ወደ ሰላም የሚደረገው ጉዞ ዋጋ እንደሚያስከፍል ግልጽ ነው

 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አፈ ቀላጤ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጎንደር ሆነው በሰጡት መግለጫ ትህነግ ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ላይ ችግር እየፈጠረ አመልክተዋል። በመግለጫቸውም መንግስት ለእርዳታ እና ሰላም ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ አስታውቀዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ባለፈው ሳምንት 20 ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ የገቡ መሆኑን አስታውሰው፥ መንግስትም ይህን ድጋፍ ለማስቀጠል ዝግጁነቱ እንዳለው ቃል አቀባዩ አመላክተዋል። ይሁን እንጂ ትህነግ የእርዳታ ማጓጓዙ እንዳይቀላጠፍ ችግር መፍጠሩን ወቅሰዋል። የአፋርና የአማራ ክልልም ለነዋሪዎቻቸው ዕርዳታ ማድረስ እንዳልቻሉ፣ የክልላቸው ነዋሪዎች በትግራይ ነጻ አውጪ ወራሪ ሃይል ስር ሆነው እየተሰቃዩ መሆናቸውን ማመልከታቸው ይታወሳል።

ትናንት “የርዳታአቅርቦትን መጠን ማን ይወስናል” በሚል የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ሃላፊ እንዳሉት የትግራይ ክልል ሕዝብን አስቸኳይ የምግብ ፍላጎት ለማሟላት በየቀኑ 300 የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ ወደ ትግራይ ክልል የሚገቡ የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ቁጥር የሚወሰነው በለጋሾች አቅም መሆኑን ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ማስታወቁን አመልክተዋል። እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ወደ ክልሉ በሚገቡ የጭነት ተሸከርካሪዎች መጠን ላይ የተቀመጠ ገደብ አለመኖሩን አስረድተዋል።

የትግራዩ ሃላፊ እንደሚሉት የትግራይ ሕዝብ ከመንግስት የሚፈልገውን የማግኘት መብት አለው። እንኳን በዕርዳታ የሚመጣውን ድጋፍ ለመወሰን ቀርቶ ራሱ ሸምቶ ሊያቀርብ እንደሚገባው አመልክተዋል። የተገኘው እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይገባ መሰናክል ስለማጋጠሙ ጥያቄ ያልቀረበላቸው ሃላፊው፣ የትግራይ ሕዝብ መብት እንዳለው ጠቅሰው መንግስት ሸምቶም ሆነ ካስቀመጠው አንስቶ የትግራይን ፍላጎት የሟሟላት ግዴታ እንዳለበት ሲናገሩ በተመሳሳይ ክልሉ እንደ ክልል ለፌደራል መንግስት ሊታዘዝና በህግ በተቀመጠ አግባብ ሊተዳደር አለመፍቀዱ የችግሩ መነሻ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ቢነሳም እሳቸው ያሉት ነገር የለም። በጥያቄም አልተነሳላቸውም።

ዶክተር ለገሰ ግን ለቪኦኤ አቤቱታውን አስመልክቶ ሲናገሩ “መንግሥት በሌሎችም ክልሎች ያለውን ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ አቅም በፈቀደ ድጋፍ ማቅረብ ይቀጥላል” ብለዋል በኢትዮጵያ ዝናብ መቁረጥና በሰላም እጦት ከአስራ ሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ቀለብ ፈላጊዎች ሲሆኑ፣ ዓለም ላይ የተፈጠረው የምግብ መወደድና በጦርነት ሳቢያ የአቅርቦት መላላት ቸግሩን ለመቅረፍ አዳጋች እዳደረገው ጉዳዩ የሚመለከታቸው እያስታወቁ ነው። ችግሩ እንደ ኢትዮጵያ አይነት ደሃ አገርን ብቻ ሳይሆን ሃብታም የሚባሉትንም እያንገዳገደ መሆኑ የሚያሳዩ ሪፖርቶችና የህዝብ ጩኸት እየተሰማ ነው።

ከዕርዳታ ጋር በተያያዘ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ጩኸት እየተሰማ ሲሆን መንግስት በከፍተኛ መጠን ስንዴ በማምረትና ግዢ በመፈጸም ችግሩን ለመፍታት እየጣረ መሆኑንን፣ በግብርና የሚተዳደሩ ብቻ ሳይሆኑ የከተማ ነዋሪዎችም በላቸው ጓሮ አትክልት ተክሎ የመመገብ ባህላቸውን እንዲያዳብሩ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑ እያስታወቀ ነው።

የትግራይ ግብርና ሃላፊ 300 ተሽከርካሪ ወደ ትግራይ መግባት እንዳለበት ሲያስታውቁ ምን ያህል መድሃኒት፣ የመጸዳጃ መጠቀሚያዎች፣ ነዳጅና የመሳሰሉትን መንግስት እንዲያሟላ በግዴታ ሲያስቀምጡ፣ አቀራረባቸው ልክ በሌላው ክልል እንደሚሆነው በትግራይ እንዲሆን ፍላጎት መኖሩን አመልካች ሆኖ ታይቷል። ለዚህ ጥያቄ በመንግስት በኩል በግልጽ መልስ ባይሰጥም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የትግራይን ሕዝብ የመርዳት ሃላፊነት የመላው ሕዝቡ ጭምር ነው። መንግስትም በሃላፊነት ይሰራል ማለታቸው ይታወቃል። እዛው ላይ ያነሱት ትልቅ ጉዳይ ቢኖር ትህነግ ከወረራቸው የአፋርና የአማራ ክልል ለቆ መውጣት እንዳለበት ነው።

የትግራይ ሕዝብና በየአካባቢው ተፈናቅለው፣ እዲሁም በዝናብ እጥረት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉት ወገኖች ከስቃያቸው ለመታደግ ከዕለታዊ ዕርዳታ ባሻገር ፖለቲካዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ በርካቶች ሲመኙት የነበረው የአገራዊ የሰላም ኮሚሽን ተቋቁሟል። የህ አገራዊ መግባባት እንዲሰፍንና አገሪቱ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሲነክባለል የኖረው የአለመግባባት ችግር እንዲፈታ ጥረቱ ቢቀጥልም፣ ሌላ ጦርነት እንዳያገረሽ ስጋት እየተሰማ ነው።

ትህነግ ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑንን የሚጠቁሙ መረጃዎች መኖራቸውን የሚጠቁሙ ወገኖች አማራ ክልልም ሰፊ ሃይል መገንባቱን እያስታወቁ ነው። በተመሳሳይ መከላከያ ማንኛውንም ዓይነት ትዕዛዝ ለመፈጸም ብቁ ዝግጅት ማድረጉ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ይገኛል። ትህነግም ከነ ሙሉ ትጥቁ ሳይሸነፍ ወደ ትግራይ መመለሱን ሲያስታውቅ ” አስፈላጊ ሆን ሲገኝ የተፈለገውን ቦታ መቆጣጠር ለትግራይ ሃይሎች ቀላል ነው” ሲል ማስታወቁ አይዘነጋም።

ሁሉም ወገን ያለው ዝግጁነትና ስጋት ይህን ቢመስልም ከሁሉም አቅጣጫ ምስኪኑ ሕዝብ ስቃዩ ስለበዛ ፖለቲከኞች የዳግም ጦርነት አጀንዳና ዝግጅታቸውን በመተው ወደ ጠረጴዛ ውይይት፣ ድርድርና በሰጥትቶ መቀበል ሁሉንም አሸናፊ ለሚያደርግ ስምምነት እንዲዘጋጁ የሚለምኑ ይበረክታሉ። በየስፍራው “የፍየል ወጠጤ” የሚሉ ግጭትን ” ስራና ቀለባቸው” ያደረጉ ወገኖችም ሰላም እንዲሰፍን ግፊት እንዲያደርጉ እነዚሁ ዜጎች ደጋግመው እየለመኑ ነው።

“በስመ ጋዜጠኛነት በየገጹ እርጥባን በመለመን ኪሳቸውን የሚሞሉና ራሳቸውን አዋቂ ያደረጉ ለዚህ መከረኛ ሕዝብና አገር ሲሉ በቃኝ” እንዲሉ ቤተሰቦቻቸው፣ ልጆቻቸው በተለይም ሚስቶቻቸው እንዲማጸኗቸው በጭንቀት ብዛት የሚማጸኑ ጥቂት አይደለኡም። አሉባልታና የፌስ ቡክ ስልታዊ ፕሮፓጋንዳን ሳያላምጡ የሚያሰራጩትን ሽብር ነጋሪዎች የሚረዱና የሚያበረታቱ ወገኖችም ቆም ብለው እንዲያስቡ እነዚሁ ወገኖች ያሳስባሉ።

“ሽው አለብኝ፣ ሰማሁ፣ ይመስለኛል…” የሚሉ መነሻዎችን በመያዝ፣ መንግስት ሁሉንም ጉዳይ አደባባይ ወጥቶ እንዲዘረግፍ የሚወተውቱ፣ የሚያስፈራሩና አገርና ፓርቲን ሳይለዩ ዓመቱን ሙሉ ነገር እየሰነተቁና አውዱ እያሳቱ መርዝ የሚረጩ ክፍሎች ችጋር እየጠበሰው ላለው ሕዝብ ሲሉ አደብ እንዲገዙ እያለቀሱ የሚጸልዩ መኖራቸው፣ ደረታቸውን የሚድደቁና ” ፈጣሪ ሆይ” የሚሉ ከሁሉም ወገን እየታዩ ነው።

በተራ የግል ችግርና የስልጣን ጥማት ለውጡን ተከትለው ማተራመስ ውስጥ የገቡ ሃይሎችና ወገኖች ለደሃው ምስኪን ሕዝብ ሲሉ ወደ ቀልባቸው እንዲመለሱ፣ በተለይም እያማተቡ ጀመረው፣ ቡራኬ አስከትለው እለት እለት መእርዝ ረጭተው ሲጨርሱ ” ቀለቤን አደራ፣ በሱፐር ቻት…” የሚሉትን ክፍሎች ሕዝብ ሊታገላቸውና ፊት ሊነሳቸው እንደሚገባ የሚያሳስቡ፣ የትግራይ ተወላጆችም በተመሳሳይ ለሰላም ጫና እንዲያሳደሩ እየተማጸኑ ነው።

ላለፉት ዓምስት ዓመታት ሰላም የራቃት ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ሰላምና የመቻቻል መንገድ ካልሆነ በቀር ሊሎች አማራጮችን መሸከም የማትችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችል ስጋት ያላቸው፣ መሬት ላይ ያለው እውነታ እጅግ አስደንጋጭና ጤና የሚነሳ በመሆኑ ከእልህና ከክፋት ይልቅ “ይብቃ” በሚል ስሜት እርቅ ላይ እንዲያተኩሩ ይመክራሉ። በተለይ ሚዲያ ለሳንቲም ለቀማ ሲባል የሚያመርቱትን የጥፋት መርዝ እንዲያቆሙ ያሳስባሉ።

Exit mobile version