Site icon ETHIO12.COM

«የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ በገንዘብ፣ በሙያ ፣በቴክኒክና በአቅም ግንባታ ድጋፍ ያደርጋል»

ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባቀረቡለት ግብዣ መሰረት በብረት ምርት እና ፋብሪካ ግንባታ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፋቸውን ለመስጠት ከመጡት ታዋቂው የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ ፖስኮ(POSCO) ኃላፊና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል።
የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት በተያዘው ዕቅድ መሰረት ፖስኮ የጥናት ቡድን አካል የሚሆን ሲሆን ኩባንያው በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ ያደርጋል።
በቅርብ ጊዜያትም የአዋጭነት ጥናት ፣ የፋብሪካ ተከላና የሰው ሀብት ልማት ስራዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ከማዕድን ሚኒስቴር ሙያተኞች ጋር ዛሬ ይፋዊ ስራ ጀመሯል።ኢንጂነር ታከለ ኡማ

የኢትዮጵያ የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት የኮርያው ብረት አምራች ኩባንያ ፖስኮ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት ለተያዘው ዕቅድ የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርግ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ አሰታወቁ።

ሚኒስትሩ ከኮርያው ብረት አምራች ኩባንያ (POSCO) ኃላፊና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባቀረቡለት ግብዣ መሰረት በብረት ምርትና ፋብሪካ ግንባታ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፋቸውን ለመስጠት ከመጡት ታዋቂው የኮርያ ብረት አምራች ኩባንያ (POSCO) ኃላፊና ሙያተኞች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የብረት ማዕድንን በመጠቀም የብረትና የብረት ውጤቶችን ለማምረት በተያዘው ዕቅድ መሰረት ፖስኮ የጥናት ቡድን አካል የሚሆን ሲሆን ኩባንያው በገንዘብ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ድጋፍ ያደርጋል።

በቅርብ ጊዜያትም የአዋጭነት ጥናት፣ የፋብሪካ ተከላና የሰው ሀብት ልማት ስራዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ከማዕድን ሚኒስቴር ሙያተኞች ጋር ይፋዊ ስራ መጀመሩ የማዕድን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።

Exit mobile version