Site icon ETHIO12.COM

የድሮ ሪፖርት ቃል በቃል ገልብጦ ሪፖርት ያቀረቡት ሚኒስትር “ ነውረኛ” ተባሉ

የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲያቀርብ በተገኘበት መድረክ ምንም ዓይነት የሪፖርት ማሻሻያ ሳያደርግ በቀጥታ እየገለበጠ እንደሚያስተላልፍ ደርሼበታለዉ ሲል የዉሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አከባቢ እና አከባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

ቋሚ ኮሚቴ የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት ባደመጠበት ወቅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፖርቶችን በቀጥታ ገልብጦ ከማምጣቱም ባሻገር የተቋሙ የበላይ ሃላፊዎች የማያዉቁት እና ያልተገመገመ ሪፖርት ለ ምክርቤት መላኩ እጅግ ነዉር ነዉ ሲል ቋሚ ኮሚቴዉ ወቅሷል፡፡

ሪፖርቱ በ ከ 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስካለንበት 2014 የግማሽ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርቶች በቀጥታ ተገልብጠዉ የተላለፉ ናቸዉ ብሏል ቋሚ ኮሚቴዉ፡፡

ለማሳያነትም በስነምግባር እና ጸረ ሙስና ብልሹ አሰራሮች ናቸዉ ተብለዉ ከቀረቡት 16 ጥቆማዎች መሀል 13ቱ ተጣርተዉ መልስ የተሰጣቸዉ ሲሆኑ 3 ጥቆማዎች በሂደት ላይ የሚገኙ ናቸዉ የሚለዉ አፈጻጸም ከ 2012 የዘጠኝ ወር ሪፖርት ቃል በቃል ምንም ለዉጥ ሳይደረግበት ተገልብጦ የመጣ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፣ ይህንንም ሀሰት ነዉ የሚል አካል ካለ በርካታ ተጨባጭ የሰነድ ማሳያዎች ማቅረብ እንችላለንሲሉ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ፈትያ አህመድ ተናግዋል፡፡

በሚኒስቴር ዲዔታ ማዕረግ የሚኒስቴሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ በሪፖርቱ ላይ የቀረበዉ ትችት ትክክል እንደሆነ አምነዉ የሪፖርት ጥራትና ወቅታዊነት ጉዳይ በፍጹም ለጥያቄም ቢሆን የሚቀርብ ጉዳይ እንዳልሆነ አንስተዉ መስተካከል እንዳለበት እንደሚያምኑ እና የተለያዩ መስሪያ ቤቶች አንድ ላይ መዋሃድ ይህንን ክፍተት መፍጠሩን እንደምክንያት ያነሱ ሲሆን በቀጣይ ይህንን አስተካክለዉ እንደሚቀርቡ ገልጸዉ ፣ ቋሚ ኮሚቴዉን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

ሚያዝያ 07 ቀን 2014 ዓ.ም

እስከዳር ግርማ FM 108

Exit mobile version