Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ታጣቂዎቹን ከወረራቸው አካባቢዎችሙሉ በሙሉ አላስወጣም – እርዳታ ለማድረስ ፈተና ሆኗል

እስካሁን 9 ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 146 የዕለት ደራሽና ሌሎች ቁሳቁሶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደርሰዋል!!!

መንግስት በትግራይ ክልል ያልተገደበ የሰብዓዊ ርዳት እንዲደርስ ከወሰነበት ጊዜ ወዲህ 9 ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 146 የዕለት ደራሽና ሌሎች ቁሳቁሶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቐለ መድረሳቸዉን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ትህነግ ታጣቂዎቹን ከወረራቸው አካባቢዎችሙሉ በሙሉ አላስወጣም – እርዳታ ለማድረስ ፈተና ሆኗል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፤ በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሕግ ማስከበር እንዲሁም በሽብርተኝነት በተፈረጀው የሕወሃት ቡድን እንቅስቃሴ ሳቢያ ለርዳታ የተጋለጡ ዜጎችን ለማገዝ መንግስት እየተጋ መሆኑን አንስተዋል። የፌደራል መንግስት በሥፍራው ለሚገኙ ተርጂ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይና የዕለት ደራሽ እርዳታ እንዲያገኙ እያደረገ በሚገኘው ጥረት እስካሁን ባለው ሂደት 9 ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 146 ሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደርሰዋልም ብለዋል

በክልሉ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ላሉና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተሰጠ ይገኛል ያሉት አምባሳደር ዲና፤ የህወሃት ቡድን አሁንም ከአፋርና አማራ ክልል አካባቢዎች ታጣቂዎቹን ለማስወጣቱ ለእርዳታ ማድረስ ሥራው ፈተና ሆኗል ማለታቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።

የለጋሽ ድርጅቶች እጅ ማጠር በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ክስትቶች ሳቢያ የተረጅዎች ቁጥር መናር ለሰብዓዊ ድጋፉ ተጨማሪ አሉታዊ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ ተብሏል::

ኃይሎቻቸውን ከአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ማስወጣታቸውን ትግራይን እያስተዳደሩ ያሉት ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የህወሓት ታጣቂዎች አፋር ውስጥ ይዘዋቸው ከቆዩ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ አልወጡም ሲሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ፅህፈት ቤት እና የአፋር ክልል ባለሥልጣናት አስተባብለዋል።

በሌላ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳምንቱ ውስጥ የተከናወኑ አበይት ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን በማስመልከት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቅርቡ ህይወታቸው ላፈውን የኬኒያው የቀድሞው ፕሬዚደንት ሟይ ኪባኪ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን መግለጻቸውና ኪባኪ በስልጣን ዘመናቸው የኢትዩ-ኬኒያ ወዳጅነት ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርስ የሠሩ መሆናቸውን እንደገለጹና በሥርዓተቀብሩ ላይ ለመገኘትም ወደ ናይሮቢ ማቅናታቸው ተገልጿለ።

ተመሣሣይ በኢትዮጵያ የማሊ አምባሣደር ህልፈተ ሕይወትን በማስመልከት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሐዘን መግለጫ ማውጣቱ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮንን ዳግም መመረጥ በማስመልከት የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት ማስተላለፋቸውና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ አጋጣሚ እንደሚፈጥርም ተጠቅሷል።

የፌዴራሉ መንግስት በትግራይ ክልል ያልተገደበ የሰብዓዊ ረድኤት እንዲቀርብ እያደረገ ቢሆንም አሸባሪው ህወሓት ከያዛቸው አጎራባች የአፋር ወረዳዎች አለመውጣቱና የለጋሽ አካላት በተፈለገው መጠን ድጋፍ አለማቅረብ ከተረጂዎች ቁጥር እያሻቀበ መምጣት ጋር ተያይዞ ችግር መፍጠሩ ተብራርቷ በምጣኔ ሀብታዊ ዲፕሎማሲ ጋር በተያያዘም፣ “Doing Business in Ethiopia” በሚል መሪ ቃል በህንድና በጃፓን የሚገኙ ኤምባሲዎች የተለያዩ ስራዎችን ማከናወናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም፣ በማልታ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ስዊድንና ብራዚል አዲስ የተሾሙ የኢትዮጵያ አምባሰደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ማቅረባቸው ተወስቷል።

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በኩል በዚህ ሳምንት 2382 ዜጎች ከሳዑዲ ወደሀገር ቤት መግባታቸውና እስከአሁን በተሰራው ስራም ከ 15300 በላይ ዜጎች ወደሀገር ቤት መመለስ መቻሉ ተገልጿል።

በከኢድ እስከ ኢድ ኤክሲፖም ከውጭ ወደሀገርቤት በርከት ያሉ ዜጎች እየገቡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመራ ቡድን ከውጭ ወደሀገርቤት ከተመለሱ ዜጎች ጋር የአፍጥር ሥነሥርዓት ማካሄዱን አምባሣደር ዲና የገለጹ ሲሆን በተመሣሣይም በዱባይ፣ በአንካራና በሳውዲመሠል የአፍጥር ስነሥርዓት መከናወኑ አንስተዋል።

በመጨረሻም፣ ሚኒስቴር መሥሪያቤቱ የዘጠኝ ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እንዳደረገና ጫና በበዛበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ያከናወናቸው ስራዎች በበጎ መልኩ መገምገማቸውን አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል።

source – OBN, ኢፕድ

Exit mobile version