Site icon ETHIO12.COM

ጦርነቱ አይቀሬ ሊሆን? በአፋር መከላከያ ምላሽ ሰጠ

“ሕዝባችን የተቃጣበትን የኅልውና ፈተና በከፍተኛ ርብርብ እንደመከትነው ሁሉ ፈተናው ዛሬም ያንዣበበ መሆኑን አውቆ ሁሉን አቀፍ ዝግጅት እንዲያደርግ እና ጠላቶቻችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስጋት በማይሆኑበት መልክ እስኪዳከሙ በርትቶ ይታገል ዘንድ ለማሳሰብ እንወዳለን” የሚል ጥሪ ያቀረበው የአማራ ክልል ነው።

ለጦርነት ናፋቂና አተራማሾች ልቦና ካላችሁ

1 . በሶሪያ ጦርነት የቆሰለው ህፃን ለዶክተሩ «እኔ ወደ ፈጣሪ መሄዴ ነው የሆነውን ሁሉ እነግረዋለው»

2 . ኢራቅ ሞሱል ውስጥ ቆስላ እየሮጠች ካሜራማኑ ሲቀርፃት «አጎቴ እባክህ ቪዲዮ አትቅረጸኝ ምክንያቱም ሂጃብ አለበስኩም»

አንድ ህፃን በፍልስጤም እጅግ በጣም ይራብና «ፈጣሪ ሆይ እባክህ በቶሎ ወሰደኝ አንተ ከወሰድከኝ በገነት ውስጥ አልራብም እዛ እበላለሁ»

በአፍጋኒስታን ጦርነት እጁ ክፉኛ የቆሰለው ህፃን ለሕክምና ዶክተር ጋ ወስደውት ለዶክተሩ «ዶ/ር እጄን ስትቆርጠው ልብሴን አትቁረጠው ተጠንቀቅ ምክንያቱም እኔ ሌላ ልብስ የለኝም እና» አለው።

የጦርነት አስከፊነትን እንማር።

ከመጻሕፍት ዓለም – Book Shelf

addisadmassnews.com

ትግራይን እያስተዳደረ ያለው ትህነግ በበኩሉ የወታደር ምልመላውን መስፈርት ዕድሜ በማሻሻል፣ መስፈርት በማላላት አጠናክሮ መቀጠሉንና ራሱን ” ከበባ” ከሚለው ማነቆ ነጻ ለማድረግ ጦርነት አማራጩ እንደሆነ እያስታወቀ ነው። መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጁን ተከትሎ ትህነግም ስምምነቱ እርዳታ ያለገደብ የሚገባ ከሆነ እንደሚቀጥል አስታውቆ መስማማቱ ይታወሳል።

በቅርቡ ይፋ የሆነ ይቪዲዮ መረጃ  የትህነግ ፅ/ቤት ኃላፊ ዓለም ገብረዋህድ ይህንን ብሎ ነበር፤ “ከግምባር የተመለሱትም (ቁስለኛውም፤ የሸሸውም) ቢሆን 10 ቀን ሰልጥነው በድጋሚ መዝመት አለባቸው። አሃዱ (ጓድ) የነበረው ቀድሞ ወደ ነበረበት አሃዱ (ጓድ) ይመደባል። አሃዱ የሌለው ወደ አዲስ አሃዱ ይመደባል። እነሱን መልሰን እንዲዘምቱ ካላደረግን አዳዲስ ልጆችን እንዲዘምቱ ማድረግ አንችልም። አንድ ሰው መቅረት የለበትም። ይሄን የማያደርግ አመራር ካለ እንዳናየው፤ ከፊታችን ዞር ይበል” ሲሉ ተደምተዋል። ቢቢሲ “ልጆቻቸውን አንሰጥም ያሉ የትግራይ እናቶች እየታሰሩ ነው” ሲሉ የትህነግን የጦርነት ዝግጅት ምልክት ዘግቧል።

ሰሞኑንን አቶ የአብን ከፍተኛ አመራር አቶ ጋሻው መርሻ “ህወሐት ለሌላ ዙር ጥፋት ዝግጁ መሆኑን እየገለፀ ነው። ከሰሞኑ እርዳታ ለማስገባት አስቦ በአፋር በኩል ያሰማራውን ሰራዊት አስወጥቶ ነበር። እርዳታው ከገባ በኋላ ለቆት በነበረው የአፋር ግዛት በኩል መልሶ ወረራ ሞክሮ በመከላከያ ኃይል ክፉ ቅጣት ቀምሶ ተመልሷል።” ሲሉ መረጃቸውን ጠቅሰው አስታውቀዋል።

በሕልውናው ዘመቻ ከአቶ ዩሱፍ ጋር ጎን ለጎን፣ እንዲሁም ከመላው የአብን አመራሮች ጋር በውጊያ አውድ ግልጽ የሚታይ ተሳትፎ ያበረከቱት አቶ ጋሻው ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ይህንኑ አረጋግጠዋል። የትህነግ ሃይሎች ዳግም ወደ አፋር ክልል ለመግባት ሲሞክሩ መከላከያ ከምድርና ከሰማይ የአጭር ሰዓታት ግን ከባድ የተባለ ምላሽ ተሰጥቷል።



እቶ ጋሻው አክለውም “ህወሐት ከአፋር በተጨማሪ በኤርትራ ታችኛው ግዛት በኩልና በወልቃይት በኩል እንዲሁ ጦሩን አስጠግቷል። ህወሐት ጦርነት መኖሪያው ነው። ህወሐት ያለ ጦርነት እና ግጭት መኖር አይችልም። ስለሆነም የሰብል ወቅቱን ጠብቆ ለጥፋት ተዘጋጅቷል። በእርግጥ የሐገር መከላከያ ሰራዊት ከሁል ጊዜው በበለጠ ሁኔታ አሁን ዝግጁ ነው። የአማራ ክልል ኃይልም እንዲሁ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ዝግጁ ነው። የአፋር ወንድሞቻችንም ከአምናው በበለጠ ደርጅተዋል። የኤርትራ ኃይል ያው ጠንካራነቱ ጥያቄ የለውም። ወያኔም የኤርትራን ኃይል በሚገባ ያውቃል።” ካሉ በሁዋላ ጥያቄ ሰንዝረዋል።

“የገረመኝ ነገር ህወሐት በዚህ ሁሉ እሳት አጥር ውስጥ አልፌ እመጣለሁ ብሎ የማሰቡ ነገር ነው። አንዳንድ የእኛና የጎረቤት ባንዳዎች ለህወሐት የተሳሳተ ግምገማ መረጃ ሳይሰጡ አይቀሩም። ባንዳዎቹ በህልማቸው ያሰቡትን ለህወሐት ያቀብላሉ። ህወሐት የእነሱን መረጃ እንደ ትክክለኛ መረጃ ወስዶ ለዳግም ጥፋት እያዘገመ ነው” ያሉት አቶ ጋሻው፣ “ህወሐትን ከእነ ባንዳዎቹ መደምሰስ የኢትዮጵያዊያን ኃላፊነት ይሆናል። ደግሞ እናደርገዋለን” ብለዋል። “የውጭ” ሲሉ የጠሩዋቸው ባንዳዎች የሚታወቁ ቢሆንም ስለውስጥ ባንዶች ግን አላብራሩም።

ትህነግ በራማ በኩልና በባድመ አቅጣጫም ከኤርትራ ጋር ውጊያ ሞክሮ እንደነበር መረጃዎች ይፋ ሆነዋል። የኢትዮጵያ ሃይሎችም ይህንን አረጋግጠዋል። ሰሞኑንን ይፋ የሆኑ መረጃዎች እንደሚሉት ኤርትራ ራሺያ ሰራሹን ድሮን ታጥቃለች። ትህነግ በርዳታ ስም በአንቶኖቭ ገብቶለት ይሁን አይሁን ግልጽ መረጃ ባይኖርም የኤርትራ ዘመናዊ ድሮን መታጠቅ ለትግራይ ሃይሎች መልካም ዜና አልሆነም።

በሃይል አሰላለፉ አንጻር ያለው ጉዳይ የማያወላዳና ግልጽ ሆኖ ሳለ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ የሚሰሙ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያ ከትህነግ ጋር ወደ ዳግም ጦርነት ልትገባ እንደምትችል ነው። ትህግም ለውጊያ እየተዘጋጀ መሆኑን ዘገባዎች እያመላከቱ ነው። ኤርትራም በሩሲያ ሠራሽ ዘመናዊ ድሮኖች ጡንቻዋን ማፈርጠሟ ከዜና በላይ ሆኗል። 

በዚህ ሁሉ የመረጃ ፍሰት ውስጥ የኢትዮጵያ መካላከያ ሠራዊት አዲስ የማጥቃት ዘመቻ በቅጽበት ሊጀምር ይችላል የሚሉም አሉ። እንደነዚህ የዜናና ምንጮች ኢትዮጵያ ከትህነግ ጋር ያላትን ጉዳይ ለማጠናቀቀ አዳዲስ ድሮኖችንና ለጊዜው በስም ያልተጠቀሱ ተዋጊ ጀቶችን አስገብታለች ወይም የተጨማሪ ጀቶች ባለቤት ሆናለች። በሌላም በኩል ቱርክ ሰራሹ ባይራክ 32 ድሮን ከቀደመው በተጨማሪ አገር ቤት መግባቱ ተሰምቷል።

ረጅም ርቀት ሚሳኤሎች በወጉ የታጠቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ወታደራዊ ደህንነቶችን፣ የሜካናይዝድ ብርጌድ ባለሙያዎችንና የከባድ መሳሪያ ኦፕሬተሮችን፣ የመቶና የጓድ መሪዎችን፣ በተለያዩ ዘርፎች የነበሩበትን ጉድለቶች በአራት ተከታታይ ዙሩ አስለጥኖ ማብቃቱ፣ አስር ወር የሰለጠኑ የልዩ ፓራ ኮማንዶና አየር ወለድ ወታደሮች፣ እንዲሁም ስሙ በግልጽ ባልተተቀሰ አገር የተዘጋጁ ልዩ ሃይሎች ያካተተ ዘመናዊ ጦር መገንባቱን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በየአጋጣሚው እየተናገሩ ነው።

ሰሞኑንን የውግዘት ባለተራ የሆኑት ጀነራል አበባው ባዶ ቤት እንደነበር በአስደንጋጭ ሁኔታ የገለጹት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዛሬ መልኩ ሌላ ነው። ከውጭ አገር ተመልሰው አገራቸውን ለማገልገል መከላከያን ከተቀላቀሉት ጀምሮ፣ ከዚህ በፊት በተለያየ ዙር ሲሰለጥኑ የኖሩና በመጀመሪያው የክተት አዋጅ፣ የተመዘገቡ ወታደሮች እስካሁን ማስልጠኛ ካምፕ ውስጥ ቆይተው ሰሞኑን ወደ ወደ ተለያየ ክልል በተለይም ወደ አማራ ክልል በመግባት አዲሱን ጦር ልምድ ካላቸው ጋር የማዋሃዱ ስራ መተናቀቁ እየተነገረ ነው። ቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ ተጨማሪ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የገባ ሲሆን በሁመራ ግንባር ወደር የሌለው የኢትዮጵያ ወታደር ሰፎሮ እንደሚገኝ የሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት አመላካች ነው።

በዚሁ ሁሉ ዝግጅት ውስጥ የከረመው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአየር ሃይልና ሜካናይዝድ ሃይል ጋር በመሆን ልምምድ እያደረገ የሚያሳዩ ምስሎችና ቪዲዮዎችን መንግስት አሳይቷል። በውጤቱም አሁን ያለው ሰራዊት ለሁሉም አይነት ዝግጁ እንደሆነም ተመልክቷል።

ከትህነግ በኩል ያለው ዝግጅት ዝርዝሩ ባይታወቅም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችን መልምሎ በወልቃይትና በኤርትራ በኩል ጥቃት ለመጀመር ዝግጁ መሆኑ ተመልክቷል። ልጆቻቸውን የከለክሉ እየታሰሩና ብር እየተቀጡ መሆኑ ቢነገርም ዝግጅቱ እንደቀጠለ ታውቋል። በዚህና በሌሎች መመዘኛዎች ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑንን በርካቶች ቢስማሙም፣ ትህነግ ዕቅዱ ክረምት ሲገባ እንደሆነ፣ በኢትዮጵያ በኩልም ይህ መረጃ በመኖሩ የመቅደም እርምጃ ሊኖር እንደሚችል እየተሰማ ነው።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት መንግስት ለአሜሪካና ዓለም ዓቀፍ አካላት ያለውን ሁኔታ በተደጋጋሚ እያሳወቀ ሲሆን አምባሳደሮች በሙሉ በዚህ ስራ ላይ ተጠምደው ስራቸውን እንዲሰሩ ታዘዋል።

የአውሮፓ ህብረት ወኪሎችና የእንግሊዝ መንግስት ይህንኑ የትህነግ አካሄድ እንዲያውቁ አገር ቤት በመጋበዝ ሳይቀር በስፋት እየተሰራ መሆኑ ተሰምቷል። ይህንኑ የሚያሳዩ ዜናዎች ዝርዝር ጉዳዩን ሳያደሙ በመንግስት ሚዲያዎች እየተሰሙ ነው።

የትግራይ ህዝብም ሆነ ማንኛውም የአገሪቱ ዜጋ ዛሬ ላይ ዳግም ወደ ጦርነት ማምራት እንደሌለባቸው የሚያሳስቡ ጦርነት ከተጀመረ ጉዳቱ ከዚህ ቀደም ከደረሰው ሁሉ የከፋ እንደሚሆን ግምት እያስቀመጡ ነው።

ሃያ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ምግብ በሚገልጉበትና ድርቅ የከፋ አደጋ እያስከተለ ባለበት በዛሬው ወቅት ዳግም ወደ ጦርነት መግባት ለየትኛውም ወገን አትራፊ ስላለሆነ ለሰላም ዋጋ መክፈሉ እንደሚቀል፣ በየአቅጣጫው በአክቲቪዝምና ግራ በሚያጋባው የጋዜጣኛነት ካባ ትርምስ የሚያውጁ እዚህ ላይ ትኩረት በመስጠት ትግሬ አማራ ሳይሉ ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጡ በርካታ የጨነቃቸው እየለመኑ ነው።

ለትግራይም ሆነ ለሌሎች ዜጎች አንድም ፋይዳ በማያስገኝ ጦርነት ላይ ቤንዚን የሚረጩና አቶ ጋሻው ” ባንዳ” ያሉዋቸው ወገኖችን ሕዝብ መርጦ እንዲያገላቸው የሚማጸኑ ” ዛሬ ስላምን ከሚሰብኩት በስተቀር ሌሎች ባለቅኔዎችና የትርምስ ዜማ አውራጆች መቀመጫቸው ከሚቆሰቁሱት እሳት የራቀ በመሆኑ እሳቱ ዳር ያሉ ዜጎች ፊት ሊነሷቸው ይገባል” የሚል አሳብ አላቸው።

ትግሬ፣ አማራ፣ ወላይታ ወይም ኦሮሞ ቢሞት ዜጋ በመሆኑ ህሊና ላለው ሁሉ ሃዘን መሆኑንን የሚገልጹ ” ይበቃል” በሚል ዕርቅ ላይ ትኩረት መስጠቱ፣ ለዕርቅና ለሰላም ሲባል የሚከፈለውን ሁሉ ዋጋ መክፈሉ ይሻላል” እያሉ ነው።

በትግራይ ክልል ያገባናል የሚሉ የአካባቢው ተወላጆች ከወትሮው በተለየ ትህነግ ላይ ተቃውሞ እያሰሙ ቢሆንም በአማራ ስም የሚጮሁና ክልሉን ለማተራመስ የሚሰሩ አስመሳዮች ግን ብሶባቸዋል። ለዚህም ይመስላል ክልሉ ምስጋና ለሚጋባቸው ምስጋና፣ ሽልማት ለሚገባቸው ሽልማት ሰጥቶ ” ለህልውና ዘመቻው እንደተነሳነው አሁንም አንድ ሆነን እንነሳ” ሲል ከፊት ችግር እንዳለ አመላክቶ ጥሪ ያቀረበው።

Exit mobile version