Site icon ETHIO12.COM

የአማራ ክልል ከተሞችን ለማናወጥ የተያዘው ቀጠሮ ከሸፈ

“በፋኖ ስም የሚነግዱ አሉ፤ በነጻነት እና የአማራ የክብር ስም በኾነው ፋኖ እየተንጠላጠሉ ሕገ ወጥ ተግባር ለመፈጸም የሚፈልጉ አሉ፤ ሕግ ስናስከብር ፋኖ ነው የሚባለው ውሸት ነው፣ እኛ ሕገወጦችን እንጂ ፋኖዎችን የመንካት ዓላማ የለንምም” በሚል በግልጽ አስቀምጦ ሴራ የሚሸርቡና ዝርፊያ ላይ የተሰማሩትን፣ እንዲሁም ከትህነግ ጋር በህቡዕ የሚሰሩትንና በሙስናና በመልካም አስተዳደር ችግር ሕዝቡን የሚያስለቅሱ ሁሉ ወደ ህግ የማቅረቡ ተግባር እነደሚቀጥል ክልሉ ይፋ አድርጓል።

ይህን ተከትሎ “ለነገው ሰላማዊ ሰልፍ የወጣቶች ጥሪ” በሚል ከየአቅጣጫው በመላው የአማራ ክልል ከተሞች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች “ፋኖ ትጥቅ እንዲፈታ እየተደረገ መሆኑንን ተቃወሙ” የሚል ሃረግ ያለው ጥሪ በስፋት በማህበራዊ ገጾችና በዩቲዩብ የየዕለት ክፍለ ጊዜዎች ቢሰራጭም በዛሬው ዕለት ክልሉ ውስጥ የተናወጠ ከተማ እንደሌለ ታውቋል።

በተለያዩ የአማራ ከተሞች ለሚደረገው ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍና የስራ ማቆም አድማ ጥሪ መበተኑንን ተከትሎ ክልሉ ህግ ማስከበሩን የሚያስተጓጉሉ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቆ ነበር። አክሎም አንድም አካል የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ እንዳላቀረበና የተሰጠ ፈቃድ እንደሌለ ጠቅሶ መግለጫ አውጥቷል።


ከክልሉ የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ጋር በማህበራዊ ገጽ የግንኙነት መስመር በተደረገ ማጣራትና መረጃ በአማራ ክልል የተናወጠና “መሬት አንቀጥቅጥ” የተባለው ሰልፍ እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።
ለምሳሌ ምድር አንቀትቅጥ የተባለ ሰልፍ ይደረግባታል የተባለችው ባሕርዳር ፍፁም ሰላም መሆኗን ዝግጅት ክፍላችን አረጋግጧል። እንዲያውም ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ከተማዋ ደፋ ቀና እያለች እንደሆነ ታውቋል። የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደወትሮው ናቸው።

በዛሬው ዕለት በባህር ዳር ረብሻ እንዳለ አስመስለው ትግራይ ዴይሊይ የተባለ የለጠፈውን ተስፋዬ ወልደ ስላሴ የተባለ “አሁን ፓፒረስ ሆቴል ፊትለፊት” ሲል በማህበራዊ ገጹ አስራጭቷል

ጎንደርም ሆነ ደሴና ደብረብርሃንም በተመሳሳይ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ተመልክቷል። ሰልፉ ከመጠራቱ በፊት ጀምሮ የትህነግ ደጋፊዎች መሆናቸው የሚታወቁ የማህበራዊ

ትህነግ አማራ ክልልን ወሮ በነበረበት ወቅት ስልጠና ሰጥቶ ለልዩ ተልዕኮ የሰጣቸው የውስጥ አርበኞች መኖራቸውን የክልሉ የፍትህና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አመልክተዋል።

የአማራ ክልልን ልዩ ሃይል ለመበተንና እንዲከዳ ለማድርግ የሚሰሩና ከፍተኛ ሃብት የሚመደብላቸው ሴረኞችን እንደማይታገስ የክልሉ መንግስት ይፋ አድርጓል። ዘመቻውም ይህንኑ ዓላማ ያደረገ እንደሆነ ይፋ አድርጓል። ሕዝብም በሰላም እጦት መቸገሩን ደጋግሞ በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸውን አመልክተዋል። የህዝብን ሰላም ማስጠበቅና ለትህነግ ዳግም ወረራ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑን ክልሉ አክሎ ገልጿል።

Exit mobile version