Site icon ETHIO12.COM

ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

•210 በነፍስ ግድያ ተጠርጥረው ተከሰው የምርመራ ሂደቱ ለሕልውና ዘመቻው ቅድሚያ በመስጠት ሳይታይ የቆየ፤
•ከ40 በላይ ተጠርጣሪዎች ደግሞ በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ወቅት እና በተለያዩ ምክንያቶች ከማረሚያ ቤት ያመለጡ፤
•39 ተጠርጣሪዎች በግድያ እና በልዩ ልዩ ወንጀሎች ተከሰው በሌሉበት ተፈርዶባቸው የነበሩ፤
•917 ከውስጥ እና ከውጭ ተልዕኮ ሲቀበሉ የነበሩ ጸጉረ ልውጦች ሲኾኑ የመጡበት ዓላማ እየተጣራ እንደሚገኝም ኀላፊው አብራርተዋል፡፡
•ከ1 ሺህ 780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ፣ በልዩ ልዩ ወንጀል በመሳተፍ ጭምር የተጠረጠሩ፣ በጸጥታ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ አባላትም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተጠቅሷል፡፡
•የክልሉ ሰላም እጦት እንዲባባስ፣ ከክልሉ ውስጥ እና ከክልሉ ውጭ ተልዕኮ ተቀብለው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሠሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በሰጡት መግለጫ የክልሉን ሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት ዋስትና ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት የሚታዩ ሕገወጥ ድርጊቶችን የመከላከል፣ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ እና የሕዝብን ደኅንነት የማስጠበቅ ሚናውን እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

ጠላት ለዳግም ወረራ እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ከውስጥ እና ከውጭ የጠላትን ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ወቅት ከማረሚያ ቤት ያመለጡ እና በተለያዩ ሕገወጥ ድርጊቶች የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን መንግሥት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ነው ኀላፊው ያነሱት፡፡

በተወሰደው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ ከ4 ሺህ 500 በላይ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር እንደዋሉም ኀላፊው አስታውቀዋል፡፡

ከዚኽ ውሥጥ ደግሞ፡-
•210 በነፍስ ግድያ ተጠርጥረው ተከሰው የምርመራ ሂደቱ ለሕልውና ዘመቻው ቅድሚያ በመስጠት ሳይታይ የቆየ፤
•ከ40 በላይ ተጠርጣሪዎች ደግሞ በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ወቅት እና በተለያዩ ምክንያቶች ከማረሚያ ቤት ያመለጡ፤
•39 ተጠርጣሪዎች በግድያ እና በልዩ ልዩ ወንጀሎች ተከሰው በሌሉበት ተፈርዶባቸው የነበሩ፤
•917 ከውስጥ እና ከውጭ ተልዕኮ ሲቀበሉ የነበሩ ጸጉረ ልውጦች ሲኾኑ የመጡበት ዓላማ እየተጣራ እንደሚገኝም ኀላፊው አብራርተዋል፡፡
•ከ1 ሺህ 780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ፣ በልዩ ልዩ ወንጀል በመሳተፍ ጭምር የተጠረጠሩ፣ በጸጥታ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ አባላትም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተጠቅሷል፡፡
•የክልሉ ሰላም እጦት እንዲባባስ፣ ከክልሉ ውስጥ እና ከክልሉ ውጭ ተልዕኮ ተቀብለው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሠሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል ብለዋል፡፡

ኀላፊው በመግለጫቸው እንዳነሱት የተለያዩ ወንጀሎችን እየሠሩ በእውነተኛው ፋኖ ስም የሚነግዱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከእውነተኛ ፋኖ ጋር በማስተሳሰር ሥም የሚያጠለሹ ግለሰቦች እና ቡድኖች ተቀባይነት የላቸለውም፡፡

ትክክለኛ ለሀገር የቆመውን ፋኖ በማደራጀት እና በማሰልጠን በመንግሥት አደረጃጀት ስር ኾኖ ለክልሉ አንድ አቅም እንዲኾን ይደረጋል ብለዋል፡፡

የተጀመረውን የጦር መሳሪያ ምዝገባ በተመለከተ ኀላፊው በክልሉ ነዋሪው ያለውን የጦር መሳሪያ ሕጋዊ አድርጎ የሀገሩን ሰላም እንዲጠብቅ መንግሥት የጦር መሳሪያ ምዝገባ ፈቅዶ እየሠራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡ ምዝገባው እስከ 17/09/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድም ኀላፊው ገልጸዋል፡፡ ምዝገባው እንደተጠናቀቀም የትጥቅ አያያዝ እና አጠቃቀም ሕግን አስመልክቶ ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

ኀላፊው የክልሉ መንግሥት እየወሰደ ላለው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ ሕዝቡ እያሳየ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ አኹንም ሕገወጥነትን ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ ሕዝቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version