Site icon ETHIO12.COM

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ 195 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ

ዓለም ባንክ ለኢትዮጶያ አንድ መቶ ዘጠና አምስት ዶላር ድጋፍ መስጠቱ ተገለጸ። ድጋፉ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባትን ለዜጎች ለማዳረስና የጤና ዘርፉን ለማገዝና በጦረነት ለተጎዱ የጤና ተቋማት የሚውል መሆኑንን የገንዘብ ሚኒስቴር አሰታውቋል።

የገንዘብ ድጋፋ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በአገር አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍና በግጭቶች የተጎዱ የህዝብ ጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋምም የሚረዳ ነው ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት ከ30 በመቶ በታች ያለውን የኮቪድ-19 የክትባት ሽፋን ለማሳደግና በመላ አገሪቱ የክትባት ሥራዎችን በማስፋፋት የኮቪድ-19ን ስርጭትና ተጽእኖ ለመቀነስ ይረዳል።

በእናቶች እና ህጻናት ጤና አጠባበቅ ረገድ ፣በሥነ-ምግብና ሌሎች ቁልፍ አገልግሎቶችን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ የገንዘብ ድጋፉ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውና በግጭቱ የተጎዱ የገጠር አካባቢዎችን እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመድረስ ብሎም ለኢትዮጵያ የጤና ስርዓት ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ታወቋል፡፡

ድጋፋ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ግዢ ለማድረግ ፣የሆስፒታል የፅኑ ህሙማን ክፍል (አይሲዩ) መሳሪያዎችን ለማሟላት ፣ በኮቪድ-19 እና በሌሎች ህመሞች ላይ ያሉ ህመምተኞችን አያያዝ የበለጠ ለማሻሻል እንዲሁም የማህበረሰብ ጤና ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ይውላል ተብሏል።

የገንዘብ ድጋፋ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 መጨረሻ ለ60 በመቶ ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባትን ለማዳረስ የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ ሲሆን ይህ የ195 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ምላሽ የሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ከ495 ሚሊዮን ዶላር ያደረሰው መሆኑ ኢፒድ ዘግቧል።


Exit mobile version