ETHIO12.COM

የአውሮፓ ሕብረት የፖለቲካና የደህንነት ኮሚቴ አዲስ አበባ መግባት ውጤቱ አጓጉቷል

ኢትዮጵያ የቀይ ባይህር ወይም በምስራቅ አፍሪቃ የሚፈጸሙ ወንጀሎችንና የመሳሪያ እንዲሁም ህገወጥ የሰዎችን ዝውውር በመቆጣተር ረገድ የሬድ ሲ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት (Red Sea Initiative) ከፍተኛውን ሃላፊነት እንደምትወጣ በተነገረ ማግስት የአውሮፓ ሕብረት የፖለቲካና የደህንነት ኮሚቴ አምባሳደሮች አዲስ አበባ መግባታቸው ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል በጉጉት የሚጠበቅ ጉዳይ ሆኗል።

ኢትዮጵያ በሽብርተኝነት፣ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመከላከል ሰፊ ተሞክሮ ያላት መሆኗ ተመልክቶ የኢኒሴቲቩ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን ያላትን ትልቅ ልምድ ለቀጠናው ብሎም ለአፍሪካ የምታካፍል አገር እንደሆነች ሰሞኑንን መገለጹን ጠቁመን ነበር። ኢትዮጵያ ትህነግ አዲስ አበባ ሲገባ ያፈረሰውን ባህር ሃይል በከፍተኛ ወጪና ወዳጅ አገሮች እርድታ ስታቋቁም “ባህር የሌላት አገር ለምን ባህር ሃይል ታቋቁማለች” በሚል ትችት ዚሰነዘርም ነበር።


Landlocked Ethiopia to Rebuild its Navy

France agreed to support Ethiopia to build a naval force, yet it would take years for Ethiopia to procure the ships and train the forces required for a fully-fledged navy.


ሕገ ወጥ የሰዎችና የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን እንዲሁም የተሰረቁና የጠፉ ሰነዶችን የመከላከል ዓላማ አድርጎ ለአምስት ዓመታት የሚቆየው ይህ ፕሮጀክት በአለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም (INTRPOL) አስተባባሪነት በአለም አቀፍ Martime ድርጅት (IMO)፣ በአውሮፓ ህብረት (EU) እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት መድሀኒትና ወንጀል ቁጥጥር (UNODC) በጋራ የሚሰራ ሲሆን በአቅውሮፓ ህብረት ስድስት ቢሊዮን ዩሮ ተበጅቶለታል።

ከአውሮፓ ሕብረት 27 አባል አገራት የተውጣጡ የሕብረቱ የፖለቲካና የደህንነት ኮሚቴ አባል አምባሳደሮች አዲስ አበባ መግባታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያስታወቀው ይህ ዜና በተሰማ ጥቂት ጊዜ ውስጥ ነው።


የአውሮፓ ህብረት ታላቅ ስጋት የስደተኞች ፍልሰት እንዳያጥለቀልቀው ነበር። እንኳን ምስራቅ አፍሪቃ ሙሉ በሙሉ ቀውስ ውስጥ ገብቶ፣ እንዲሁም ስደተኛ እያጥለቀለቃት ያለችው አውሮፓ ይህን ፍልሰት ለመግታት ቁርጠኛ አቋም መያዝዋ አሁን ከኢትዮጵያ ጋር አዲ እየገነባች ያለው የድህነነትና የጸጥታ ስራ ስጋት የወለደው እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ነበር


የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ ረፋዱን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የአውሮፓ ሕብረት የፖለቲካና የደህንነት ኮሚቴ አባል አምባሳደሮቹ በዋናነት ከአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ጋር በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ገልጠዋል። አፍሪካ ህብረት ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ጎን በመሆኑና ኢጋድ የሚመራው በኢትዮጵያ በመሆኑ ስንሰባው የስምምነት ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል።

ከሁለት ሳምንት በኋላም በሚደረገው የአውሮፓ ሕብረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ጉዳዩን በአጀንዳነት ለማስያዝ የሚረዳ ስራ እንደሚሰራ የኮሙኒኬሽን ሚንስትሯ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ባያስረዱም ” በትህነግ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ በጋራ የማጣራት ስራ እንዲከናወን የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ ያቀርባል” ብለዋል።

የሕብረቱ የፖለቲካና የደህንነት ኮሚቴ አባል አምባሳደሮቹ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታዋ በጠቆሙበት መግለጫቸው፣ “የትህነግ የሽብር ቡድን የሚነዛቸውን የውሸት ፕሮፓጋንዳዎች ለማጥራት የአምባሳደሮቹ መምጣት ጠቀሜታ አለው”ብለዋል።

በውይይቱ የሰብዓዊ ድጋፍን በተመለከተ ሕብረቱ በምን ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያን ሊያግዝ ይችላል በሚል ጉዳይ ላይ እና አሸባሪው ሕወሓት በአማራና በአፋር ክልሎች የፈጸማቸውን አሰቃቂ ወንጀሎች በአግባቡ ለማስረዳት ለመንግስት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጠር አስታውቀዋል። በዚህም በአማራና አፋር ህዝብ ላይ የደረሰውን መጠነ ሰፊ ወንጀሎች፣ የመሰረተ ልማት ማውደምና ዝርፊያ፣ የጅምላ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና የመሳሰሉት ወንጀሎች በሰነድና በፊልም ለአምባሳደሮቹ ከበቂ ዋቢ ጋር እንደሚቀርብ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አመልክተዋል። ድንገተኛ የመስክ ምልከታም እንደሚኖር ገልጸዋል። አምባሳደሮቹ ሲመለሱ ኢትዮጵያ ላይ የአንድ ወገን መረጃ በማድመጥና ኢትዮጵያ ላይ በደቦ ሲደረግ የነበረውን ዘመቻ እንደሚቀለብሱ እምነታቸው መሆኑንን ተናግረዋል።

በሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ በጋራ የማጣራት ስራ እንዲከናወን የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ ማቅረቡን ሚንስትሯ መናገራቸው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ለሰጡት መረጃ ትክክለኛነት ማሳያ ይሆናል።

ይህም

Exit mobile version