ETHIO12.COM

ቻናል 29 ትግራይና የታደሰ ወረዳ “የጦርነት ዝግጅት ጨርሰናል” ዜና

በጋምቤላና ጊምቢ የተሞከረው ወረራ መክሸፉ ይፋ ከሆነና በወለጋ ንጹህ ዜጎች በተጨፈጨፉ ማግስት የሱዳን መንግስት የጦርነት እስክስታ እየወረደ ይገኛል። ይህን ተለትሎ የግብጽን ምኞት ለማሳካት የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ ታጣቂዎች አዛዥ ናቸው የተባሉት የቀድሞ ሌተናል ጀነራል “ለጦርነቱ ዝግጅት ጨርሰናል” ሲሉ ተሰምተዋል። ከዛ በፊት ትህነግ ያደራጃቸው እንደሆኑ ከሚነገርላቸው መድረኮቹ አንዱ የሆነው ቻናል 29 ” መንግስት መፍራቱን በድብቅ ሲመከር አገኘሁ” ያለውን መረጃ አሰራጭቷል።

ጭፍጨፋው የህዝቡን ማህበራዊ ዕረፍት ለመንሳት የታቀደ መሆኑ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል። “ቀጥሮ ያስተዳድራቸዋል” በሚባሉት የኦነግና ራሱ ያሰረጋቸው የትህነግ የውጭ አገርና የአገር ውስጥ ስኳዶች የፈጸሙትን አሳዛኝ ጭፍጨፋ ተከትሎ ” ለጦርነት ዝግጅት ጨርሰናል” ሲሉ ታደሰ ወረደ መናገራቸው ሁሉም ነገር በዕቅድና በመናበብ የሚሰራ መሆኑንን አመላካች እንደሆነ የትህነግን አሰራር በቅርብ የሚያውቁ አመልክተዋል። በቅንጅት ከተሰራው ስራ ጎን ለጎን ደግሞ የፈጠራ ዜና መመረቱን አስታውቀዋል።

ትህነግ በዲጂታል ወያኔ የድረ ገጽና የማህበራዊ ሚዲያ ጦሩ አማካይነት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ከህዝብ ለመነጠል ያካሄደው የማጠልሸት ዘመቻ በድል መሳካቱን ከገመገመ ብሁዋላ ጦርነት መክፈቱ አይዘነጋም። ይህን ያስታወሱ ወገኖች እንደሚሉት አሁንም ይህንኑ ለመድገም ባሰበ መልኩ የጦርነት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ያስታወቀው የወለጋውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ሕዝብ የተሰማውን የሃዘን ስሜት በመንተራስ መሆኑንን ተናግረዋል።

“ቻናል 29 ትግራይ” የሚባለው የትህነግ ማህበራዊ አውድ አስቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች ” ወልቃይትን ከመስጠት ውጭ ምንም አማራጭ የለንም” ማለታቸውን፣ ይህንንም ያሉት የትህነግን ሃይና ፈርተው መሆኑንን በትግራይ ስም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሚስጥር ጠቋሚ ሆኖ አመልክቷል።

ስማቸውን ያልገለጹና ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወቅታዊ ዝግጅት የሚያውቁ ” ትህነግ ከተነኮሰ የሚደርስበትን ከኢትዮጵያ ህዝብ በላይ ያውቃል” ብለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ማናቸውንም ሃይል የመመከትና በአነስተኛ መስዋዕት፣ በአጭር ጊዜ የሚሰጠውን ተልዕኮ በአየርና በምድር ተዋዶ የሚወጣ ሰራዊት መግንባቱን በተደጋጋሚ እያስተዋወቁ ነው።


ዲጂታል “ወያኔ”፤ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል”

በርካታ መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰ ቀንተሌት ተግተው የሚሠሩ “የሳይበር ወታደሮች” ተመድበዋል። እነዚህ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በትጋት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ዓላማቸው መረጃ ማዛባት፤ የሃሰት መረጃ መበተን፤ የሚወጡ መረጃዎችን ማወዛገብ (ሕዝብ እውነቱንና ሐሰቱን እንዳይለይ ማድረግ)፤ ወዘተ


“መሳሪያ የተሸከመውና የኢትዮጵያን ሰራዊት የመደምሰስ ስራ የሰራው የትግራይ ህዝቡ ነው” በማለት መግለጫ የሰጡት መንግስት በአገር ክህደትና የኢትዮጵያን መከላከያ በተኛበት በማሳረድ ወንጀል የሚፈልጋቸው የቀድሞ ሊተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ለምን “ህዝብ መከላከያን ጨረሰ” ለማለት እንደፈለጉ በግልጽ ባይታወቅም ንግግራቸው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ለተፈጸመው ክህደት ሌላ ዋቢ መሆኑ ተተቁሟል።

ከትህነግ ጋር አብሮ የሚሰራውና ” የራሱን ህዝብ ጭምር ይበላል” የተባለው ኦነግ ሸኔ በወለጋ ንጹሃንን መጨፍጨፉን ተለትሎ “ከብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ የወጣ መረጃ” በሚል ትህነግ “የፈጠራ ዜና ይረጭባቸዋል” ከሚባሉት መገናኛዎች መካከል አንዱ በሆነው ቻናል 29 ባሰራጨው ወሬ አብይ አህመድ ” ምዕራብ ትግራይን አስረክበን ለድርድር መቀመጥ አለብን” ማለታቸውን ከወቅቱ የኢትዮጵያ የሰላም ፍላጎት እንቅስቃሴ ጋር አስታኮ ጽፏል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በግልጽ ወልቃይት የቤገ ምድር አካል መሆኗን መናገራቸው፣ ከወልቃይት ነዋሪና ሚሊሻ፣ ከአማራ ልዩ ሃይል በተጨማሪ የመከላከያ ሃይል ከሙሉ ሜካናይዝድና ተወርዋሪ ኮማንዶ ጋር በክፍለጦር ደረጃ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ሰራዊት ማሰለፋቸውን “የፈጠራ ዜና” የተባለው አላነሳም።


ባለፉት 3 ዓመታት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ 49%ው በዲጂታል ወያኔ የተከፈቱ ናቸው

የሀሰት መረጃ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ መሆናቸውን አጀንሲው ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም የህውሐት ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ህዳር ወር ብቻ 17,000 የሚሆኑ ሀሰተኛ የቲዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ  ቡድን ተከፍተው ነበር 

ኢትዮጵያ ለድርድር የሰየመቻቸው ባለስልጣናት ማንነትና የወከሉት ድርጅት እየታወቀ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የብልጽግና መንግስት ቀጣይነት በዚህ ድርድርና መፍቴ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው” ሲሉ ትህነግ የጠየቀውን ሁሉ ማድረግ ግዴታ እንደሆነ መግለጻቸውን ያተተው የትህነግ ልሳን ” የምንፈልገውን የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው” ሲሉ ታደሰ ወረደ ከተናገሩት ጋር ተመሳስሏል። ለዚህም ነው “የመናበብ የፈጠራ ዜና” ሲሉ የትህነግን አካሄድ የሚያውቁ ያመለከቱት።

የትግራይን ሕዝብ አሁንም አጀግነው ለጦርነት እንዲነሳሳ ምልጃ በሚደረግበት ወቅት ” አሸባሪው የህወሃት ቡድን የመዋጋት አቅምም ሞራልም የሌላቸውን በማስገደድ ወደ ውጊያ እንደሚያስገባ እጃቸውን ለምዕራብ ዕዝ የሰጡ ወዶ ገቦች መናገራቸው ተሰምቷል። ወዶ ገቦቹ እንደሚሉት የሽብር ቡድኑ ከ13 ዓመት ጀምሮ ያሉ ህፃናቶችን እና አዛውንቶችን ጭምር በማስገደድ አጭር ስልጠና ሠጥቶ ወደ ጦርነት እንደሚማግድና ወደ ኋላ የሚመለስ ከጀርባው እንደሚመታ ምስክርነታቸውን አኑረዋል። ቀደም ሲል መቶ ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ነዋሪዎች ፈልሰው ወደ አማራ ክልል መግባታቸውም ይታወሳል።

ቡድኑ የኢትዮጵያ ሰራዊት የማያውቀው ተተኳሽ ደብቆ እንደነበር ታደሰ ወረደን ጠቅሶ አል አይን ከትግርኛ ወደ አማርኛ በቀየረው ዘገባ አመልክቷል። አያይዞም የዚሁ ታጣቂ ሃይል መሪ “አሉ” ሲል ትህነግ ለቀጣዩ ጦርነት ሙሉ በሙሉ መዘጋጀቱን አመልክቷል።

የቡድኑ ታጣቂዎች አዛዥ ታደሰ ወረደ ዘጠና ደቂቃ በፈጀ ንግግራቸው አሁን የሚደረገውን ጦርነት “የፈለግነውን ነገር መፈጸም የሚንችልበት ነው” ነው ብለውታል። ፍላጎታቸውን ግን በግልጽ አላበራሩም። እሳቸው ይህን ሲሉ በርክታ የትህነግ ሰልጣኝ ስኳዶች በወለጋው ጭፍጨፋ መሰማራታቸውና መያዛቸው ተውቋል።

“አሁን ጊዜ አግኝተን ሰርተንበታል” ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ “ሁሉንም ዝግጅታችንን ጨርሰናል”ሲሉ በቀጣይ የሚደረጉት ጦርነቶች ከዚህ በፊት ከነበሩት የገዘፉ እንደሚሆኑ አስረድተዋል። “ከትግላችንም መጨረሻ የሚያደርሱን ናቸው” በማለት በብዙ ቁጥር የሰየሟቸውን ጦርነቶች ከባድነት ገልጸዋል። ጦርነቶቹ በየት አቅታጫዎች እንደሚተገበሩ ግን አልዘረዘሩም። ድብረጽዮንና ጌታቸው ረዳ ግን “ወልቃይትን በሃይል ደምስሰን እንያዝለን” በማለት መነጋራቸውና “የአብይ ጦር” የሚሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዳግም እንደሚበትኑት መግለጻቸው ይታወሳል።

ከኤርትራና ከኢትዮጵያ ጋር በተደረገ ጦርነት ይህን ያህል ሞተ የሚባለው ሃሰት እንደሆነ ን ሲገልጹ አንደ አል አይን ትርጉም “ይህን ያህል ሞተ ገደልን፤ ገለመሌ የሚባለው ውሸት ነው፤ እርግጠኛ መሆን ያለባችሁ አንድ ነገር ነው፤ዝግጅታችንን ጨርሰናል” ሲሉ ፎክረዋል። የትህነግ ወታቶች ክንፍ መቀለ ሆኖ ይፋ ባደረገው መግለጫ ከ300 ሺህ በላይ የትግራይ ወጣቶች የገቡበት አልታወቅም ማለቱ፣ በክልሉ ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ የነጻ አውጪ ሃይሎችም እስከ ሰባት መቶ ሺህ የሚደርሱ የትግራይ ወታቶች ማለቃቸውን መናገራቸው አይዘነጋ። ከዛው ከትግራይ በሚወጡ ዜናዎች እናቶች ” ልጆቻችንስ” ሲሉ ጥያቄ ማቅረባቸውን ቢቢሲና ቪኦኤ አስታውቀው ነበር። ለዚህ የምስላል ታደሰ ወረደ የትግራይን ህዝብ እንደተለመደው ” ጀግናና ልዩ ሕዝብ” ሲሉ ያቆላመጡት። ማቆላመጥ ብቻ ሳይሆን ጦርነት እንዲከፍቱ ስማቸውን ያልዘርዘሩዋቸው ክፍሎች እንደሚወተውቷቸው፣ ውጊያ መቼ፣ የትና እንዴት እንደሚጀመር ግን የትህነግ ዕቅድ ብቻ መሆኑንን ገልጸዋል።

ባለሙያዎች እንደሚሉት ቁትሩን በስድስትና ከዚያ በላይ ባገዘፈው፣ ዘመናዊ የምድርና የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሚያ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀው፣ ቲክኖሎጂን የተላበሰውና በተደጋጋሚ የተፈጸመበት ጥቃት የሚያንገበበውን ጦር በዚህ ደረጃ ለመዳፈር ትህነግ ከምላስ የዘለለ ሃይል የለውም። ” እንኳን አሁን እሱ መንደር ውስጥ ገብቶና በትጥቅ ተመናምኖ፣ የኢትዮጵያን መከላከያ በመበተን፣ ሰፊ ሃይል በያዝበትና የኢትዮጵያን ሁሉ ትጥቅ በወረሰበት ወቅት ያላሳካውን ዛሬ ላይ አያደርገውም” ሲሉ የታደሰ ወረደን ፉከራ አጣጥለውታል።

” በትግራይ ውጊያ የማድረግ ፍላጎት የለም” ያሉት ባለሙያዎቹ፣ ” አያደርጉትም፣ ካደረጉት ግን ምቱ መራራ ይሆናል። የመከላከያ አዛዦች ደጋግመው እንዳሉት ይቅርታም እይኖረውም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ” ምነው ባልጀመርነው” የሚል አስተማሪ ቅጣት እንደሚሰጥ ደጋግመው መናገራቸውን፣ ይህም የሚሆነው የሰላሙ አማራጭ ሲገፋና ትንኮሳ ሲጀመር እንደሆነ አመልክተዋል።

መንግስት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ተደራዳሪ መሰየሙን ይፋ ባደረገበት መግለጫው ” ትንኮሳ ካለ መከላከያ አሳፋውን ምላሽ ይሰጣል” ማለቱን ይታወሳል። የሰላም ውይይት እንደሚደረግ በሚነገርበት ወቅት ትህነግ ጦርነት እንደሚጀምር ማወጁ በርካቶችን አስገርሟል። ይሁን እንጂ የህ ነጻ አውጪ ነኝ የሚል ቡድን ከፍተኛ መጠን ያለው እርዳታና ነዳጅ ማግኘቱን ተከትሎ የጦርነት ዝግጅት ማጠናቀቁን ማስታወቁ አስገራሚ ሆኗል። ወሰኑ ትግራይ ሆኖ ሳለ ለምን ወደ ሌሎች አካባቢዎች በወረራ ለመግባት በድጋሚ ማቀዱን እንዳስታወቀ ግልጽ ያልሆነላቸው አሉ።

በአዲስ አበባ ሰሞኑንን “ድርጅታችን ጦርነት ሊጀምር ነው። መዘግየት የለበትም” የሚሉ እንደበዙ የሚናገሩ ዜጎች ” እንደ 1983 አንሸወድም” እያሉ ነው።

Exit mobile version