Site icon ETHIO12.COM

የፓትሪያርኩ የውጭ ጉዞና – “ተቀነባብሯል” የሚባለው ሴራ እያነጋገረ ነው

የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ እግራቸውን ላይ “ገጠመኝ” ባሉት ችግር የሚፈልጓቸውን መርጠው ወደ አሜሪካ ለመጓዝ መወሰናቸው ውስጡ “መርዝ አለው” የሚል አስተያየት እያስነሳ ነው። በህክምናቸው ጉዳይ ሳይሆን አብረዋቸው እንዲጓዙ የመረጧቸው፣ በተለይም የሙሴ ሃይሉ ጉዳይ የህግ ጥያቄም አካቷል።

“ከትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ጋር ቁርኝት አላቸው” በሚል የሚከሰሱት አቡነ ማትያስ እንደ አባት ሁሉን በዕኩል እንደማያዩ ይተቻሉ። ” በእኔ እድሜ ኢትዮጵያ ስትፈርስ በማየቴ እኮራለሁ” በሚል ኢትዮጵያን ለመበትን እንደሚሰራ ከሚናገረው “ትግራይ ሚዲያ ሃውስ ” ለሚሰኝ የትህነግ ሚዲያ የሰጡት ቃለ ምልልስና ከዛም በፊት ለውጭ አገር ሚድያዎች በሰጡት ሚዛን ያልጠበቁ አስተታየቶች በርካቶች እንዳዘኑባቸው ሲገለጽ ቆይቷል።

ፓትሪያርኩ ዛሬ የሰላም ዜና ሲሰማ ትህነግ ጦርነት ለማወጅ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በይፋ በገለጸበት ወቅትና፣ ይህን ለማገዝ እንደ በፊቱ የሚዲያ ዘመቻ ለመጀመር ዝግጅቱ በተፋፋመበት፣ እንዲሁም አሜሪካ በኡጋንዳ ለሚስለጥነው አምስት ሺህ የሚጠጋ ሰርጎ ገብ የደፈጣ ተዋጊ 200 ሚሊዮን መለገሷ ይፋ በሆነበት፣ ከዚህም በላይ ንጽሃን ወገኖች በተጨፈጨፉ ማግስት ሲኖዶስ በከፊል በዚህ ጉዳይ ሙግት ውስጥ የገባው “ሴራ አለ” በሚል መነሻ እንደሆነም እየተሰማ ነው። እነዚህ ወገኖች ፓትሪያሪኩ ሊኮበልሉ እንደሚችሉም እየጠቀሱ ነው። ይህንኑ የኩበለላ ጉዳይ ” ግልግል” ሲሉ እንደ አንደ በረከት የሚወስዱ ያሉትን ያህል ” ሊከፈት ከታሰበው ፕሮፓጋንዳ ጋር ሲመዘን ጉዳት አለው” ሲሉ መላ ምት የሚሰጡም አልጠፉም።

ፓትሪያሪኩ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ግን “እመለሳለሁ። ለመታከም ብቻ ነው የምሄደው” ሲሉ መናገራቸውን ያነጋገሩዋቸውን አባቶች ጠቅሰው የሚጽፉ አሉ። ይህንኑ አምነው የሚቀበሉ ጥቂቶች ቢኖሩም መሄዳቸው ቅንጣት ያላሰሰባቸው በርካታ ናቸው። እንደ አባት መታከማቸውን ተቀብለው ያነጋገሯቸው የቤተክርስቲያኒትን ስም፣ ክብር፣ መንፈሳዊ እሴትና የፍቅር መንገድ እንደ ትልቅ አባት አክብረው እንዲመለሱ ያሳሰቧቸውም አሉ። እሳቸውም ይህንኑ እንደሚያደሩ ግብረ መልስ እንደሰጡ ተሰምቷል።

በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክነት በየሳምንቱ ሮብና አርብ ፓትራሪኩ በብፁ አቡነ ማትያስ ሰባሳቢነት የሚመሩት የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ እንደሚካሔድ የጠቆሙ ሰኔ አስር በተካሄደው የቋሚ ሲኖዶስ ሳምንታዊ ስብሰባ የተለያዩ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተው ውሳኔዎች እንዳሳለፉና በተጨማሪም ፓትሪያሪኩ ብፁዕ አቡነ ማትያስ “በእግሬ ላይ የጤና እክል ደርሶብኛል ስለዚህ ወደ አሜሪካን ሀገር ሄጄ መታከም አለብኝ” የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ለጉዳይ ቅርበት ያላቸው አስታውቀዋል።

የፓትራሪኩ የቅርብ ፕሮቶኮል ሰራተኛና በቤተ ክርስትያኑዋ በተደጋጋሚ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ከሚንቀሳቀሱ ማህበራት ጋር በቅንጅት ይሰሩ እንደ ነበር የሚገርባቸውን ሙሴ ሀይሉን ጠቅሰው፣ ” እኚህን ከህዋሃት የሽብር ቡድን ጋር ግኑኝነት እንዳላቸው ተጠርጥረው በተደጋጋሚ ታስረው የተፈቱ ፣ እንዲሁም ፓትሪያሪኩን ቀደም ብሎም ወደ ትግራይ እንዲሄዱ የመገፋፋትና የማመቻቸት ስራ ሲሰራ የቆየ ግለሰብ” ነው ሲሉ እነዚሁ ክፍሎች መቃወሚያ የሚያነሱት ቅዱስነታቸው እሳቸውን ይዘው ወደ አሜሪካ ለመሄድ መጠየቃቸውን ተከትሎ በተነሳ የህግ ጥያቄ መሆኑን አመልክተዋል።

አባ ኤፍሬም የተሰኙት የፓትሪያሪኩ የቅርብ ምግብ አዘጋጅ ሰራተኛ አብረዋቸው ወደ አሜሪካ እንዲሄዱ ፓትሪያርኩ ጥያቄ ማቅረባቸውን ለሲኖዶሱ ቅርብ የሆኑ ገለጸዋል። በማስታመም ስም ሁለቱ ተጠቃሾች አብረዋቸው እንዲጓዙ፣ የአውሮፕላን የጎዞ ትኬት በአንድነት እንዲዘጋጅላቸው፣ካልሆነም ግን በራሳቸው ትኬት ቆርጠው ለመሔድ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀው የጠቅላይ ቤተክነት ዋና ስራአሰኪያጅም ብፁ አቡነ አብርሃም ትኬቱን እንደሚያዘጋጁላቸው እንደገለጹላቸውና በልዩ ጽ/ቤት በኩልም ለኤምባሲ የቪዛ ጉዳይ ለማስጨረስ ደብዳቤ ለመጻፍ ዝግጅት ላይ እንዳሉ መረጃዎች አመልክተዋል።
“ፓትሪያሪኩ ከዚህ በፊት በነበራቸው እንቅስቃሴ በተደጋጋሚ የህወሓት የሽብር ቡድንን ደግፈው በተለያየ መንገድ ሀሳባቸውን ይገልጹና መልዕክትም ያስተላልፉ ነበር” ያሉት እነዚሁ ክፍሎች “በተለይም መቀመጫቸውን አሜሪካን አገር አድርገው ለሕወሐት ከሚሰሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች እና አሜሪካን አገር ከሚገኝ T.M.H ከተባለው ቴሌቪዥን ጣቢያም ጋር እየተገናኙ መረጃ ሲለዋወጡ እንደነበረ አስታውሰዋል። አያይዘውም አሁንም የፓትሪያሪኩ የአሜሪካ ጉዞ ጥያቄ ከዚህ ቀደም ካላቸው እንቅስቃሴ ህክምና ለማግኘት የሚደረግ ጉዞ እንደማይመስልና እስካሁን ድረስ በአገር ውስጥ የከፋ ህመም ገጥሟቸው ህክምና እንዳላደረጉና ሆን ብለው ፓለቲካዊ አላማ ያለው ጉዞ እንደሆነና በትግራይ በኩል ከተቋቋመው የትግራይ ሲኖዶስ ጋር ተያያዥነት እንዳለው ለመረዳት ችለናል” ባይ ናቸው።
“ይህ የፓትራሪኩ የውጭ ጉዙ ጥያቄ በተለያዩ የሀይማኖቱ አባቶች ዘንድ ጥርጣሬን እየጫረ ይገኛል” ሲሉ መረጃውን የሚጋሩ “እንዴት እንደ ሌሎች የውጭ ተጓዥ የሃይማኖት አባቶች ሌሎች አባቶችን ይዘው ለመጓዝ አልፈለጉም፤ ለምንስ ሁለቱን ግለሰቦች ብቻ መረጡ” ሲሉ ይተይቃሉ። በተለይ አብሯቸው እንዲሄድ በፈለጉት ሙሴ ሀይሉ ላይ የህግ ጥያቄ ያነሳሉ። በግለሰብ ዙሪያ የተለያዩ ጥርጣሬዎች እየተነሱ ሲሆን የአሜሪካውም ጎዞ በሙሴ ሃይሉ የተቀነባበረ እንደሆነ ያምናሉ። ይህንኑ አሳብ ለማስቀየር የተለያዩ ሙከራዎች እያደረጉ እንደሆነ በመጠቀስ ሙሴን ይከሷቸዋል።
ሲያብራሩም ሙሴን ጠቅሰው ካደረጓቸው እንቅስቃሴዎች መካል በተለያየ ሰነድ ምክንያት ወደ አሜሪካን ሀገር መግባት የማይችሉ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን በጠቅላይ ቤተክነት የልማት ኮሚሽን መምሪያ ሀላፊን አብረዋቸው እንዲሄዱ ማነጋገራቸውን ይጠቅሱባቸዋል።

በተጨማሪም ፓትራሪኩም ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኩል በሰኔ14 ረፋዱ ረፋዱ አቡነ ሳሙኤልን ቢሮአቸው አስጠርተው እንዳነጋገሯቸው ምንጭ ጠቅሰው አመልክተዋል። በንግግራቸውም አብረዋቸው ወደ አሜሪካ እንዲጓዙ እንደጠየቋቸውና እሳቸውም በዚህ እንደማይስማሙ ማስታወቃቸው ተመልክቷል። አቡነ ሳሙኤል ጥያቄው መቅረብ ካለበትም በቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ “አብረውኝ የሚሔዱ አባቶች ይመደቡልኝ” በሚል ማቅረብ እንደነበረባቸው ቢገልጹላቸውም እሳቸው ከሌላ ከማንም ጳጳስ ጋር አብረው መሄድ እንደማይፈልጉና ፈቃደኛ ከሆኑ ግን ከእሳቸው ጋር እና ከላይ በስም ከጠቀሷቸው ግለሰቦች ጋር ብቻ መጓዝ እንደሚፈልጉ መናገራቸው ተመልክቷል።
በተጨማሪም በንግግራቸው ወቅት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን “እርሶ ከመረጧቸው ሰዎች መካከል ሙሴ ሀይሉ ከዚህ ቀደም ተከሰውና ታስረው በገንዘብ ዋስ መፈታታቸውን በማስታወስ በፍርድ ቤት የህግ አግባብ “ከአገር መውጣት አይችሉም ቢባሉና ቢመለሱ ለዕርሶ መጉላላት አይሆንም ወይ” ብለው ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ፓትራሪኩም “ሙሴ ሰኔ 13 ቀን ፌደራል ፖሊስ ሔዶ አነጋሯል። ሰኔ 14 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶታል” ሲሉ መልስ እንደሰጡ አሁንም መረጃ አቅራቢዎቹ ለጉዳይ ቅርብ ናቸው ያሉዋቸውን ጠሰው ሰዓትና ቦታ አመላክተው ተናግረዋል። ፓትሪያርኩ “አይሆንም ብለው ቢመልሱትም ይመልሱት እንጂ ከሌላ ሰው ጋር አልሔድም” ሲሉም አቋማቸውን እንደማይቀይሩ መናገራቸውን የመረጃው ባለቤቶች ገልጸዋል። በዚህም ቋሚ ሲኖዶሱ በበነጋው ባካሄደው ስብሰባ ወቅት የፓትራሪኩን የውጭ ጉዞ የፈቀደ መሆኑን ተረጋግጧል።
ይህንኑ ውሳኔ ተከትሎ ከፓትራሪኩ የጉዞ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ጥርጣሬ የገባቸው አባቶች መኖራው ይፋ ሆኗል። ብፁዕ አቡነ አብርሃም አንዱ ሲሆኑ እሳቸውም በግላቸው ሰኔ አስራ አራት ተሲዓት ብፅዕ አቡነ ማትያስ ጽ/ቤት በማምራት አግኝተዋቸው ከጤናቸው ጋር ተያይዞ ስላቀዱት የውጭ ጉዞ እንዳወሯቸውና በውይይታቸውም “ለምን ውጭ ከመውጣትዎ በፊት በግል ዶክተር አይታዩም” የሚል ሃሳብአንስተውላቸው ነበር። እሳቸውም የህንድ ዜግነት ያለው የግል ዶክተር ካሁን በፊት እንደነበራቸውና አሁን ግን እሱም በሕይወት እንደሌለ ገልፀው አንዴ ግን ሀሌሉያ ሆስፒታል ለዚሁ እግራቸው ላይ ለገጠማቸው ህመም ታይተው ብዙም ውጤት እንዳላመጣላቸው ገልጸው መልስ ሰጥተዋል።
አቡነ አብርሃም “ውጭ ሄደው መታከሞትን እኛም እንደግፋለን ግን አንድ ያደረብን ስጋት አለ አሜሪካን ሀገር ያሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ሁለት ቦታ ለመክፈል የሚፈልጉ የተወሰኑ ሰዎች እግሮት ላይ ወድቀው እዛው እንዲቀሩ ለምነው ሊያስቀሮት ይችላሉ የሚል ስጋት አድሮብናል” በማለት እንደገለጹላቸውና እሳቸውም በዛው እንደማይቀሩና ቤተክርስቲያኗም ሁለት ቦታ እንድትከፈልም እንደማይፈልጉ ህክምናቸውን ጨርሰው ተመልሰው እንደሚመጡ የገለፁ መናገራቸውን መረጃውን ከስፍራው እንዳገኙ የሚናገሩ ገልጸዋል።፡፡ አቡነ አብርሃምም “የሲኖዶሱ ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ አሜሪካን ሀገር ኒዮርክ ከተማ ወዳለው አገረስብከታቸው ደርሶ ለመምጣት ስለተጓዙ እሳቸው ይምጡና የጉዞትን ሁኔታ እናስተካክላለን” የሚል ሃሳብ ገልጸውላቸው እሳቸውም “አንድ ሳምት ችግር የለም” በማለት በሃሳባቸው እንደተስማሙ ለመረዳት ተችሏል።
ይህን መረጃ ያጋሩት እንደሚሉት ከላይ በተጠቀሱት ጥርጣሬዎችን ለማስወገድ ሲባል ባልቻ ሆስፒታል የተሻለ ህክምና መኖሩ የተጠቆመ በመሆኑ ፓትሪያሪኩ መጀመሪያ በሀገር ውጥ ያሉ የህክምና አማራጮችን ቢጠቀሙ፣ “ህክምናው የግድ ውጭ ሀገር መሆን ካለበት ደግሞ አብሯቸው እንዲሄድ የፈለጉት ሙሴ የተባለው ግለሰብ የፍርድ ቤት ጉዳይ ስላለባቸው ከጉዞ እንዲቀር ቢደረግ” ሲሉ ሃሳባቸውን ይሰጣሉ።

Exit mobile version