አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል – ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል

,,, በቂ መረጃ እንዳለ የሚታወቅ ስለመሆኑ በርካቶች ይናገራሉ

ከትሀንግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ የተያዘባቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሰፊ መነጋገሪያ ሆነዋል። በአዎንታና በአሉታዊ ጎን የተሰነዘረባቸው ተቃውሞ መነሻው ” ታፈንኩ” በማለት ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ወዳጆቻቸው ወይም የቅርብ ታዛዦቻቸው ካሰራጩና ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኤፒ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በቲውተር ገጻቸው ካሰራጩት በሁዋላ ነው።

ቪዲዮውን ተከትሎ ሙስሊም የኢትዮጵያ ልጆች የአፍጢር ስነ ስርዓት በመስቀል አደባባይ ለማካሄድ ያቀረቡትን ጥያቄ ” ከቶውንም አይቻልም” በሚል በደብዳቤ እንዲታገድ መጠየቁ ” መገጣጠም ፈጥሯል” በሚል ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል። ጉዳዩ ከመነጋገሪያ ሃሳብነቱ በዘለለ መናበብ የሚታይበት አገሪቱን የማዛልና የማዳከም አካሄድ ተደርጎ ተወስዷል። በማህበራዊ ገጾች ሲሰራጩ ውለው ያመሹት ሃሳቦች ” የተልዕኮ ሴራ ነው” ሲሉም ነቅፈዋል። የደገፉም የበኩላቸውን ብለዋል። ከተቃውሞው ጋር ሲነጻጸር እጅግ አነስተኛ ነው።

ብጹዕነታቸው “ስለ ትግራይ ስናገር ድምጼ ይታፈናል” ሲሉ የሚጀምሩበት የቪዲዮ ቅጂ በእሳቸው ቢሮ ሰራተኞች ወይም የሚዲያ ባለሙያዎች መቀረጹ እየተነገረ ነው። በቪዲዮ የተናገሩት ሃሳብ ለኤፒ ከሰጡት ቃለ ምልልስ ጋር ተዳምሮ ” በትግራይ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል” የሚል ሃሳብ ያለበትና ቢናገሩ ቢገስጹ ሰሚ ማግኘት አለመቻላቸውን የሚያመላክት ነው።

በቀርቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስም ORTHODOX TEWAHDO AGAINST GENOCIDE IN ETHIOPIA /O.T.A.G.E “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የዘር እልቂት መከላከል” በሚል የተቋቋመ ህገወጥ ድርጅት በገሃድ ገንዘብ እየሰበሰበ መሆኑ እየታየ ቤተክርስቲያን ዝምታ መምረጧ እያነጋገረ ነው። የሚሰበሰብው ገንዘብ በቀጥታ አቶ ይልማ ወልደመድህን Yilma Woldemedhen የሚባሉ የትግራይ ተወላጅ ኪስ የሚገባ ስለመሆኑ መጻፉን ያስታወሱ የፓትሪያርኩን ቪዲዮ የጨዋታው አካል አድርገው እንደሚያዩት ይገልሳሉ።

ዛሬ ” በትግራይ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል” ሲሉ አሁን ላይ ጊዜ ጠብቀው አባ ማቲያስ መናገራቸው በቤተ ክርስቲያኗ ስም እነ ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ የዘረጉት ክንፍ ገንዘብ ሲሰበስብ ለምን ዝምታ እንደመረጡ አመላካች አድርገው የወሰዱም አሉ።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

በድጋፍ ድምሳቸውን ያሰሙና ሃሳባቸውን በማጋራት ያሰራጩላቸው ” ለትግራይ መቆርቆራቸውና ስለ ትግራይ ድምጻቸውን ማሰማታቸውን አድንቀዋል። “ታፈንኩ” ማለታቸውንም በመጥቀስ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። በሙሉ ድጋፍ የሰጡዋቸው ክፍሎች ” እውነተኛ የሃይማኖት አባት” እያሉ አቆለጳጵሰዋቸዋል። ከጎናቸው መሆናቸውን የገለጹም አሉ።

መካከል ላይ ቆመው አስተያየት የሰጡ ” ትግራይ ላይ ያለው ቀውስ በዝምታ የሚታለፍ ባለመሆኑ መናገራቸው ትክክል ነው። ነገር ግን በቅርቡ በማይካድራ፣ በወለጋ፣ በሻሸመኔ፣ በዝዋይ፣ በጊዲዮ፣ በቡራዩ፣ በጉርዳ ፈርዳና በመሳሰሉት ቦታዎች ሰፊ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ሲታረዱ፣ ሲጨፈጨፉና ሲፈናቀሉ፣ ንብረታቸው ሲወድምና ለመስማት የሚቀፍ ወንጀል በጭካኔ ሲፈጸምባቸው የሚያሳይ ቪዲዮ በገሃድ እያዩ ዝምታን መርጠው መኖራቸው ሚዛን የጎደላቸው አባት እንደሆኑ ያሳያል” ሲሉ ይወቅሷቸዋል። መንፈሳዊነታቸውንም ያሳንሱታል።

ከሁሉም በላይ የአገር ባለ አደራ፣ እሳቸው የሚከራከሩለትን አካባቢ በተለየ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ሲጠብቅ የነበረ የአገር ደጀን ሰራዊት ባላሳበው መልኩ ሲታረድ፣ ሲጨፈጨፍና ትጥቅ የፈቱትም እንደ ባዕድ ግፍ ሲፈጸምባቸው ብጹዕነታቸው ድማጻቸውን አለማሰማታቸውን በስፋት የተቃወሙዋቸው አንስተዋል። ” ዘረኛ” ሲሉም ስም ለይተው አውግዘዋቸዋል።

ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት በተደረገበት ወቅት በተመሳሳይ “በትግራይ ጄኖሳይድ ተካሂዷል” ብለው ስለነበር ቤተክርስቲያን ገለልተኛ አካላ አቋቁማ እንዲጣራ ተጠይቀው ፈቅደኛ እንዳልሆኑ መዘገባችን ይታወሳል። በዚም ሳቢያ ቅሬታ ተፈጥሮ ነበር።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት “በነጋዴዎች” እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ ” ቸልተኛነት አይተናል”

አሁንም ይህ ቪዲዮ ከተሰራጨ በሁዋላ የሲኖዶስ አባላትን ያላስደሰተ መሆኑና ምን አልባትም አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል ለአካባቢው ቅርብ የሆኑ እየተናገሩ ነው። እንደ ቅርብ ሰዎቹ ከሆነ ሲኖዶስ የፓትሪያርኩ ሃሳብ ቤተክርስቲያንን የሚወከል አለመሆኑን በይፋ በመግለጫ ለዓለም ያሰራጫል። በተለይም ለአቻ ቤተክርስቲያናትና ለዓለም ቤተክርስቲያናት ህብረት አቋሙን ግልጽ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት ተገዶ የገባበት ጦርነት ምንም እንኳን ምስኪን ዜጎችን ሰለባ ቢያደርግም፣ በምስኪን ዜጎች ላይ ችግሩ የጠና ቢሆንም፣ የትግራይ ተራ ሕዝብ በምሽግነት ተይዞ ለስቃይ መዳረጉ አሳዛኝና መፍትሄ የሚያሻው አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ ቢታመንም፣ የችግሩን ባለቤትና ምንጭ ወደ ጎን ትቶ ክስ ማሰማት ከሃይማኖት አባት የሚተበቅ እንዳልሆነ አብዛኞች ገልጸዋል።

ተቃዋሚ ካለ እንዲቀርብ ጥሪ ተላልፎ ባለመቅረቡ በአሸባሪነት የተሰየመው ትህነግ፣ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ እጅግ ዘግናኝ በደል ሲፈጽም  ብጹዕነታቸው ምንም ብለው እንደማያውቁ ያነሱ ” ትህነግ እንዲሰደዱ ያደረጋቸው ጳጳስ ዛሬ አገር ቤት ገብተው በህይወት እያሉ አባ ማቲያስ ለምን መንበሩን ይይዛሉ። ይህን ጥያቄ ሲኖዶስ አይቶ በቤተክህነቷ ቀኖና መሰረት ቡይን ሊሰጥ ይገባል” እስከማከት ደረሰዋል። ከታች ያለው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቪዲዮ የተናገሩት ነው። ጨዋ አስተያየት እናስተናግዳለን።

ስለ ትግራይ ስናገር ድምጼ ይታፈናል!!የአረማውነት ሥራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጊዜያት ሞክሬ አልተሳካም።በምስጢር ተቀድቶ የወጣው የቪድዮ መልእክታቸው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ታፍኛለሁ አሉ። ስለ ትግራይ ስናገር ድምጼ ይታፈናል። በትግራይ ጭካኔ የተሞላበት የአረመናዊነት ድርጊት እንዲቆም ብዙ ጊዜ ሞክሬ አልተሳካም።  ሚያዝያ 7 ያደረኩት ኢንተርቪው ታግዷል። ስቃወም ድምጼ ይታፈናል። የአለም ሚዲያ እየተናገራው እኛ እንዳንናገር ታፍነናል።በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ብዙ ግፍ ተሠርቷል። በትግራይ ላይ የተደረገው ግን ይበልጣል በማለት ተናግረዋል። ለዓለም መንግሥታት፣ ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት የተለየ የድጋፍ ጥያቄ ጠይቀዋል።“የአለም ሚዲያ እየተናገረው እኛ እንዳንናገር ታፍነላል ባሁን ጊዜ በሀገራችን በኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው አረመኔያዊነት፣ የአረማውነት ስራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጊዜያት ሞክሬ አልተሳካም ፤ ምክንያቱም ፍቃድ አልተሰጠም። እናገራለሁ ይመልሱታል፣ እናገራለሁ ይመልሱታል፤ ይኸው እስካሁን ጊዜ ምንም አይነት ፍቃድ አልተገኘም።እናም ሁላችሁም ወገኖቻችን ማወቅ ያለባችሁ፣ እዚህ ያለውን ችግር፣ የኔን ችግር የማውቀው እኔ ነኝ።”ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት!


አቡነማቲያስ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ማን እንደመለሰባቸው ስም ጠቅሰው አልተናገሩም። ከመንግስት ከፍተና የደህንነትና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጋር ስላደረጉት ውይይት ያሉት ነገር የለም። ጠባቂዎቻቸው የተቀየሩበትን ምክንያት እንዴት እንደትብራራላቸው አልገለጹም። በአጭሯ መልዕክታቸው ያቀረቡት ጥሪ ነው።

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

በትግራይ አረማዊነት እየተፈጸመ መሆኑንን አመልክተው የዓለም መንግስታትና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት እርዳታ እንዲያደረጉ ጠይቀዋል። ለሲኖዶስ ቅርብ የሆኑ እንዳሉት አካሄዱ ኢትዮጵያ ላይ ለተጀመረው ጫናና ጫና ለመፍጠር ለተነሱ አካላት ምክንያት ለማመቻቸት በቤተክርስቲያኗ ስም የተላለፈ ጥሪ ስለሆን ቤተክርስቲያን ምላሽ እንደምትሰጥ ገልጸዋል። ጉዳይ በዘዴ የሚያዝና ጥንቃቄን የሚሻ በመሆኑ ስማቸውን እንዳይተቀሱ የጠየቁት እኚሁ አባት ” ሳይውል ሳያድር አንድ ነገር ይሆናል” ብለዋል። አቡነ ማቲያስ ከትህነግ ጋር እንደሚገናኙ በቂ መረጃ እንዳለ የሚታወቅ ስለመሆኑ በርካቶች ይናገራሉ።


Leave a Reply

%d bloggers like this: