Site icon ETHIO12.COM

የትህነግ ሰፈር ጭፈራ – ወደ መርዶና ስጋት


ለአራት ቀናት ሰፊ የስራ ጉብኝት አስመራ የገቡት አዲሱ የሶማሌ መሪ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረው ስምምነት እንደሚፈጽሙ ይጠበቃል። የሶማሌ መንግስ አንደበት የሆነው ሆርሰድ መዲያ ሁለቱ መሪዎች በጋራ ግንኙነታቸውና ቀጣናዊ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን፣ ከዚያም አልፎ ኤርትራ የሶማሌን ጦር በምታስለጥንበት አግባብ መወያየታቸውን አመልክቷል። “The two presidents will discuss bilateral relations and regional issues. The presidents will also focus on the training of Somali troops in Eritrea, which is the main purpose”


ክፍፍሉ ተጀምሯል። ዋናው አስፈላጊ ነገር የተጀመረውን ክፍፍል እንዴት እናሰፋዋለን የሚለው ነው። እርስ በርስ እንደሚገዳደሉ እንዴት እርግጠኛ መሆን እንችላለን? የቀድሞ ጀነራል አበበ የወለጋውን ጭ “The division is beginning, the important thing is how do we make the division wider…, How do we make sure they kill each other?” TPLF General Abebe said in the leaked video.

ያፈተለከ የቪዲዮ ማስረጃ ተጠቅሶ የወለጋን የንጹሃንን ጭፍጨፋ ተከትሎ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ አመራሮች ፌስታ ላይ መሆናቸውን ይፋ በሆነ ማግስት በዚሁ መንደር ጭፈራው ወደ ስጋትና መርዶ መቀየሩ እየተገለጸ ነው። ከኤርትራ የወጡ ሁለት መረጃዎች ናቸው የጅምላ ጭፍጨፋውን ተከትሎ የነበረውን አስረሽ መችው ያከሰመው ተብሏል።

“ክፍፍሉ ተጀምሯል። ዋናው አስፈላጊ ነገር የተጀመረውን ክፍፍል እንዴት እናሰፋዋለን የሚለው ነው” ሲሉ በቪዲዮ የተደመጡት የቀድሞ የትህነግ ጀነራል አበበ ተከለሃይማኖት ” [ኦሮሞና አማራ] እርስ በርስ እንደሚገዳደሉ እንዴት እርግጠኛ መሆን እንችላለን?” ሲሉ ጠይቀው እንዴት እርግጠኛ መሆን እንዳለባቸው አብራርተዋል።

ራሱን የኦነግ ሰራዊት የሚለውና ትህነግ በግልጽ ህብረት ፈጥረው መንግስት ለመገልበጥ እንደሚሰሩ ማስታወቃቸው ይታወሳል። የወለጋው ተደጋጋሚና ዘግናኝ ጭፍጨፋም የዚሁ ጥምረት ውጤት እንደሆነ ሰለባዎችና ከጭፍጨፋ ያመለጡ በመንግስትና በግል መገናኛዎች መስክረዋል። ጀነራሉ እንዳሉት “አማራና ኦሮሞን ማጫረስ” የሚለው አጀንዳ እውን ለማድረግ የትህነግና ትህነግ የሚደጉማቸው መገናኛዎች በስፋት ሁለቱን ሕዝቦች ለማጫረስ በስፋት እየሰሩ እንደሆነ ከየአቅጣጫው የሚወጡ መረጃዎችና ቃለ ምልልሶች እያመረቱ በማከፋፈል ላይ ናቸው።

ለሶስት ዓመታት በኤርትራ ሲሰለጥን የኖረውን የሶማሌ ጦር መጎብኘታቸውን የማነ ገብረ መስቀል በቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል።

“ድንቁርና ሸኔን ከሃጢያቱ ሊያነጻው ደፋ ቀና ይላል” የሚሉና “ትህነግ እስካል ድረስ የአማራ መታረድና የኢትዮጵያ መከራ አይቆምም” ከሚል ድምዳሜ የደረሱ ራሳቸውን በኢትዮጵያ ባንዲራ እየጠቀለሉ የሚያነቡ፣ በአማራ ስም የሚምሉ፣ ነገር ግን በተቀነባበረ መልኩ በአንድ ሰው የተሰጣቸውን አጀንዳ በማራገብ የትህነግ ሴራ ተቀባይና አከፋፋይ የሆኑት ትህነግን ሊያድኑት እንደማይችሉ አመልክተዋል። ኦሮሞና አማራን ” እሳትና ጭድ እንዴት ተስማማ? ይህ የእኛ ጥፋት ነው” ሲሉ አስቀድመው በይፋ አቶ ጌታቸው ረዳ የተናገሩትን በማስታወስ “የሚታለል የለም” ሲሉም እነዚሁ ክፍሎች ይገልጻሉ።

ይህ የንጹሃን ጭፍጨፋ ላይ የቆመ፣ የምስኪኖችን ደም ነዳጅ አድርጎ የተነሳ የሚዲያ ዘመቻ በጋለበት ሰዓት ከኤርትራ የወጣውና የሶማሌ አዲሱ መሪ ጉብኝት በትህነግ ዘንዳ ለመተንበይ የሚያስቸግር መደናገጥ መፍጠሩ ተሰምቷል። አሜሪካ “ለምን ከኤርትራና ኢትዮጵያ ጋር ህብረት ፈጠሩ” ስትል የቀድሞውን የሶማሌ ፕሬዚዳንት እንዲባረሩ ማድረጓን ተከትሎ ትህነግ እንደ አገር ራሱን ለጥጦና ቆዳውን አሳስቦ ” እንኳን ደስ አለዎት አብረን እንሰራለን” ሲሉ የደስታ መግለጫ መላኩ ይታወሳል።

አዲሱ የሶማሌ ፕሬዚዳንት ሼክ ሁሴን ሙሃሙድ በአሜሪካ ውሳኔ መመረጣቸው፣ ፈርማጆ መባረራቸው ለትህነግ ዳግም ወደ ምስራቅ አፍሪቃ ፖለቲካ መመለስ ወርቃማ እድል እንደሆነ ሲገለጽ ቢሰነብትም፣ ትህነግም እንደ ቀድሞ በሶማሌ ምድር ሽር ብትን ለማለት በከበባ ውስጥ ሆኖ ለማኮብኮብ ቢከጅልም ይህ ሁሉ ህልም እንደ ጉም መበተኑን ነው ጉዳዩን የሚከታተሉ ያስታወቁት።

ይህ ብቻ አይደለም አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በተመረጡ ቅጽበት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተግባብተው ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኛነት ልዑክ በመላክ ማረጋገጣቸውን በማስታወስ የሚናገሩ፣ በሹመታቸው ድግስ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መገነታቸው ተዳምሮ ለትህነግ ወቅታዊ ጭንቀት የፈጠረ ቢሆንም የዛሬው ዜና ጭንቀቱን ወደ መርዶ የቀየረ እንደሆነ አመልክተዋል።

በሰሞኑ ናይሮቢ በተካሄደ የኢጋድ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስት አብይ ከሱዳን ምክር ቤት ሰብሳቢ አልቡርሃን ጋር ፊት ለፊት መክረው የደረሱበት ውጤትና፣ ቀደም ሲል ጀነራሉ ለኬንያ መንግስት ” አደራድሩኝ” ሲሉ ካቀረቡት ጥይቄ ጋር ተዳምሮ ዜናው የትህነግን ምኞት ያሟሸሸ፣ አጣብቂኝ ውስጥ የከተተና “ለጦርነት ተዘጋጅተናል” የሚለውን ፉከራ የበላ እንደሆነ እነዚሁ ወገኖች ያስረዳሉ።

በቅርቡ ጦርነቱን ወደ ኤርትራ በማዞር “ታላቋን ትግራይ እንመሰርታለን” በሚል በይፋ ያስታወቁት የቀድሞ ጀነራል፣ ዕቅዳቸው ኤርትራን በመያዝ የቀይባህር ሃያል መሆን ብቻ እንደሆነ አስታውቀዋል።ከኤርትራ የተሰጣቸው ምላሽ ” ከጀመራችሁ መጨረሻው ግብአተ መሬታችሁን እስከወዲያኛው…” የሚል እንደነበር ይታወሳል። የቀድሞ የኢንሳ መሪ የነበሩት ጀነራል ከምሽግ ከወጡ በሁዋላ በርካታ አነጋጋሪ አሳቦችን፣ እንዲሁም ሚስጢራቸውን ይፋ እያደረጉ መሆኑ ይታወሳል። ” መለስ አብይ አሕመድን አስወግደው” ብሎኝ ነበር ሲሉ ይፋ ያደረጉት ሚስጢር ለአብነት ይጠቀሳል።

የሶማሌ ፕሬዚዳንት በኤርትራ ግብዣ አስመራ መግባታቸውን የተገለጸው አስቀድሞ የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ቀደም ሲል ያደረጋቸውን ስምምነቶች አክብሮ እንደሚቀጥል ጠቅሶ ነበር። ይህ “በመካከላችን ችግር የለም” የሚል ዜና “በፕሬዚዳንት ኢሳያስና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መካከል ንፋስ ገብቷል” አሉባልታና ሆን ተብሎ ሲከፈት የነበረ ዘመቻ በዜሮ ካባዛው በሁዋላ ነው።

ለአራት ቀናት ሰፊ የስራ ጉብኝት አስመራ የገቡት አዲሱ የሶማሌ መሪ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረው ስምምነት እንደሚፈጽሙ ይጠበቃል። የሶማሌ መንግስ አንደበት የሆነው ሆርሰድ መዲያ ሁለቱ መሪዎች በጋራ ግንኙነታቸውና ቀጣናዊ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን፣ ከዚያም አልፎ ኤርትራ የሶማሌን ጦር በምታስለጥንበት አግባብ መወያየታቸውን አመልክቷል። “The two presidents will discuss bilateral relations and regional issues. The presidents will also focus on the training of Somali troops in Eritrea, which is the main purpose”

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ አሜሪካን ቅር ያሰኘ የሶስትዮሽ ስምምነት መስማማታቸው ይታወሳል። ኤርትራ ይህን ስምምነት አክብራ ከኢትዮጵያ ጋር እንደምታስቀጥል በይፋ ካስታወቅች በሁዋላ ነው የሶማሌ አዲሱ መሪ ኤርትራ ገብተው ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች እየመከሩ ነው። ይህን በጉብኝቱ መጨረሻ ይህንኑ የሶስትዮሽ ስምምነት የሶማሌ ፕሬዚዳንት አክብረው እንደሚቀጥሉ በይፋ ያስታውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዜናውን የሚከታተሉ እንደሚሉት የፈርሞጆን መሸኘት ተከትሎ በድል አድራጊነት ሲፈነጥዝ ለኖረው ትህነግ መርዶ ነው። ለዚህም ነው ትህነግ በንጹሃን እልቂት ከበሮ ሲመታ ቢከርምም ይህ ዜና ወገቡን የቆረጠው እንደሆነ የተመለከተው።

ሐሰን ሼክ መሐመድ ወደ መሪነት ሲመጡና ፎርማጆ ሲሰናበቱ የኢትዮጵያና የሶማሌ፣ የሶማሌና የኤርትራ ግንኙነት እንዳከተመለት በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ሚዲያዎችና ሃብቱን እያፈሰሰ በሚደግፋቸው በርካታ አውዶች ሲነገር ነበር። ከዜና አልፎ ደስታው “ታላቅ” ድል ሆኖ አበባ ሲበተንለት ነበር።

የሱዳን ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አል ቡርሃን ከኢትዮጵያ ጋር መጋጨቱ እንደማይጠቅማቸው አስልተው ኬንያን “ገላግሉን” ማለታቸውን ተከትሎ ከኤርትራ የተሰማው ዜና ሲገጣጠም ለትህነግ እጅግ ከባድ ሃዘን መሆኑ ተመልክቷል።

Exit mobile version