Site icon ETHIO12.COM

ኢንሳ የኮንዶሚኒየም ዝርፊያን ትስስር በምርመራ አጋለጠ፣ እጣው ውድቅ ሆነ

ለውድድር ብቁ ናቸው ተብሎ የተገለፀው 79 ሺህ ያህል ሰዎች የነበሩ ሲሆን ሲስተሙ ግን በድብቅ ያጋጃቸው ሰዎች 172ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ፡፡. ሁሉም በአንድ ሰው የተሰራ ነበር፡፡ በአንድ ላፕቶፕ ከስራው ጀምሮ እስከ እጣ ማውጣቱ ድረስ ተከናውኖበታል፡፡ አጠቃላይ ሲስተሙ ከብልጸጋ እስከ ትግበራ ድረስ ሙሉ ለሙሉ ችግር ያለበት ስለሆነ በዚህ አይነት መንገድ የወጣ እጣ ኦፊሽያል አድርጎ መቀበል አዳጋች

የቤት እጣ አወጣጡ ሂደት ላይ በተፈጠረው ኢፍትሀዊነት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጡ።

በአዲስ አበባ የቤት እጣ አወጣጡ ሂደት ላይ የተፈጠረውን ፍትሀዊ ያልኾነ አካሄድ አስመልክቶ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሐምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ የማጥራት ሂደቱን ሲያከናውን የነበረው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) እንዳብራሩት፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብን ሃብት ለመጠበቅ ያደረገውን እንደ ተቋምም እንደ ግለሰብም ላደረገው ጥረት ላመሰግን እፈልጋለሁ ብለዋል።

ዶ/ር ሹመቴ ያነሷቸው ዋና ዋና ሃሳቦች፦

👉 ኢንሳ እንዲህ አይነት ስራዎችን እንዲመራ የህግ ሃላፊነትም ስላለበት ስራውን መርቶ እዚህ ደረጃ አድርሷል ብለዋል፡፡

👉 ሲስተሙ ከኑሮው ቀንሶ ተቸግሮ ሲቆጥብ የኖረውን ማህበረሰብ መብት እንዲያጣ የሚያደርግ በመሆኑ ሲስተሙ ተአማኒነት የሌለው ነው፡፡

👉 ሰው ነው ቴክኖሎጂን የሚገነባው ፤ ነገር ግን ፍትህን ያጓደለ ሲስተም ሆኖ ነው ያገኘነው፡፡

👉 ሲስተሙ የመልማት አለም አቀፍ ስታንዳርዱን ያልጠበቀና ሶስቱን አካላት ፤አልሚውን፤ ተጠቃሚውን እና አረጋጋጩን አካላት የቀላቀለ እንዲሁም ለምዝበራ ያጋለጠ ነው ብለዋል፡፡

👉 የዳታው አጠቃቀም ከእጅ ንክኪ ነፃ እንዲሆን የሚፈለግ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን እጅ በዝቶበት የነበረ መሆኑ ታይቷል፡፡

👉 ከዚህ የምንማረው ነገር ቢኖር በደረስንበት ደረጃ ተዓማኒ ያልሆኑ ነገር ሲገኝ አቁመን እንዲጣራና እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ እንደሚገባና ሁልጊዜም ይህንን ማድረጋችንን መቀጠል እንዳለብን

👉 በተጨማሪም የአመራር ስነምግባርን ሟሟላት እንደሚያስፈልግ እንዲሁም ሰዎች የተሰጣቸውን የማገልገል እድል በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸውም ገልፀዋል፡፡

አቶ በሃይሉ አዱኛ ከኢንፎርሜሽንና ደህንነት ኤጀንሲ አጠቃላይ የአጣሪ ቡድኑን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን

👉 አጠቃላይ ሲስተሙ ፕሪፌሽናል በሆነ መንገድ የተሰራ አይደለም፡፡

👉 የሲተም አዘረጋግ አለም አቀፍ ስታንዳርዱን የጠበቀ አለመሆኑና የሚና ክፍፍል የሌለበት አሰራር መተግበሩ በማጥራቱ ታይቷል፡፡

👉 ሁሉም በአንድ ሰው የተሰራ ነበር፡፡ በአንድ ላፕቶፕ ከስራው ጀምሮ እስከ እጣ ማውጣቱ ድረስ ተከናውኖበታል፡፡

👉 እጣው የወጣበት እለት ጭምር ኢንተርኔት አክሰስ ሲደረግ ነበር፡፡

👉 የጥራት ፍተሻ እንዲደረግ የተጠየቀው አካል ራሱ ማንዴቱ የሌለው መሆኑም ታይቷል፡፡

👉 የተተገበረው እጣ አወጣጥ ሶፍትዌር የተሻለ አማራጭ የነበሩትን ጭምር ያልተጠቀመና መረጣው መንገድ ችግር ያለበት ነው፡፡

👉 የማበልጸግ ሂደቱ በሚከናወንበት ወቅት ከኢንተርኔት ጋር አክሰስ የተደረገ ሲሆን ይህም ፈፅሞ ተአማኒነቱን የሚያሳጣው መሆኑ

👉 የተወዳዳሪዎች ዳታ እና ከባንክና ከቤቶች ተገኘው የአያያዝ ችግር ያለበትና ለቅየራ የተጋለጠ ነበር፡፡

👉 የዳታ ዝርዝሩም ለ5 ቀናት በሰው እጅ ስር ነበር፡፡

👉 ሲስተሙን ያለማው ሰው ለሌሎች የፈጠረው ዩዘር መጠቀሚያ በሚገባ ሲስተሙን እንዳያውቁ የሚከለክል ነበር፡፡

👉 ይህ ግለሰብ በኮምፒውተሩ ስህተቱን ሪፖርት እንዳይደረግ ሚያደርግ ድብቅ ሶፍትዌር ጭኖ ነበር፡፡ በኋላ ግን አጥፍቶታል፡፡

👉 የኮምፒውተሩ የድርጊት ሂደት ዝርዝር በሚታይበት ወቅት ያለፉት 8 ቀናት ኖርማል የነበረ ሲሆን በመጨረሻዎቹ ቀናት ግን ዳታ ማጥፋ የመጨመርና ማዛወር ስራ መሰራቱን ተረጋግጧል፡፡

👉 ይህ ግለሰብ የኮምፒውተሩንም የሰዓት አቆጣጠር ሆነ ብሎ አንድ ቀን እንዲዘገይ በማድረግ ሁሉም ነገር ቀደም ብሎ እንደተፈፀመ እንዲደረግ በጥንቃቄ አከናውኗል፡፡

👉 በአጠቃላይ ለውድድር ብቁ ናቸው ተብሎ የተገለፀው 79 ሺህ ያህል ሰዎች የነበሩ ሲሆን ሲስተሙ ግን በድብቅ ያጋጃቸው ሰዎች 172ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ፡፡

👉 ከዚህ ውስጥ ደግሞ ገንዘብ ቀድመው አውጥተው የተዘጉ ፤የአመዘጋገብ ችግር ያባቸውና ብቁ ያልሆኑ ጭምር ተካተውበታል፡፡

👉 ሲስተሙ የሚፈልገውን አካል እጣ እንዲያወጣ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

👉 ከባንክ የወጣው ዳታ ውስጥ የሌሉ አሸናፊዎች ተገኝተዋል፡፡

👉 አጠቃላይ ሲስተሙ ከብልጸጋ እስከ ትግበራ ድረስ ሙሉ ለሙሉ ችግር ያለበት ስለሆነ በዚህ አይነት መንገድ የወጣ እጣ ኦፊሽያል አድርጎ መቀበል አዳጋች መሆኑን በምክረሃሳብ ደረጃ ቀርቧል።

(አሚኮ)

Exit mobile version