Site icon ETHIO12.COM

ዓለም ባንክ ከ850 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የመንገድ ግንባታ የሚውል ከ850 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ። ይህ ድጋፍ በጦርነቱ ለተጎዱ ክልሎች ከተፈቀደው 300 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ ነው።

የኢትዮ 12 መረጃ ምንጮች እንዳሉት ከ850 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሰጠው ድጋፍ ለሁለት መንገዶች ግንባታ ነው። እንደ መረጃዎቹ ከሆነ ይህ ድጋፍ በቅርቡ ይፋ ይሆናል። የቀሩት መጠነኛ የአፈጻጸም ሂደት እንጂ ጠረጴዛ ላይ ያለ ያበቃለት ድጋፍ ነው።

በጦርነት ለተጎዱት የአማራ፣ አፋር፣ ትግራይና ቤኒሻንጉል ክልሎች የሚውል የ300 ሚሊዮን ዶላር በቅርቡ መፈቀዱን ተከትሎ ትህነግ ገንዘቡን ለማንቀሳቀስ ጠይቆ እንደነበር ይታወሳል። ስማቸውን ያልጠቀሱ የዓለም ባንክ ምንጮች ” ዓለም ባንክ ከክልልና ቀበሌ አመራሮች ጋር በዚህ ጉዳይ ውል አይገባም። አሰራሩም አይፈቅድለትም። ድጋፉ በቀጥታ አቶ አህመድ ሸዴ ለሚመሩት የገንዘብ ሚኒስቴር የሚተላለፍ ነው” ሲሉ ነግረውናል።

ኢትዮጵያ ላይ በጅምላ ተከፍቶ በነበረው ዘመቻ ዓለም ባንክ ያዘገያቸውን ብድሮች፣ ድጋፎችና የተለያዩ ስምምነቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ እያንቀሳቀሰና በቅርቡም ይህንኑ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ምንጮቹ ጨምረው ጠቁመዋል።

Exit mobile version