Site icon ETHIO12.COM

እርዳታ ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ውስጥ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ተያዘ

ባለፈዉ ሳምንትም በጣቢያዉ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ መያዙን አስታውሰው፤ ዛሬ ጠዋት 3 ሰአት ላይ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-A10298 የተሳቢ ሰሌዳ ቁጥር 23634 በሆነ ከባድ ተሽከርካሪ ውስጥ 2 ሚሊዮን 280 ሺህ 640 ብር ሊያዝ መቻሉን ተናግረዋል።

በአፋር ክልል እርዳታ ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ተያዘ

እርዳታ ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ መያዙን በአፋር ክልል የጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ቅርጫፍ ሰርዶ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስታወቀ።

የጣቢያዉ አስተባባሪ ኮማንደር አህመድ ሳልህ እንደገለጹት፤ በፍተሻ ጣቢያዉ በህገወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ ነዳጅና ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶች እየተያዙ ነው።

ባለፈዉ ሳምንትም በጣቢያዉ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ መያዙን አስታውሰው፤ ዛሬ ጠዋት 3 ሰአት ላይ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-A10298 የተሳቢ ሰሌዳ ቁጥር 23634 በሆነ ከባድ ተሽከርካሪ ውስጥ 2 ሚሊዮን 280 ሺህ 640 ብር ሊያዝ መቻሉን ተናግረዋል።

ተሽከርካሪው የእርዳት እህል ጭኖ ሲጓዝ እንደነበረም አመልክተዋል።

ከገንዘቡ በተጨማሪ የወርቅ ሚዛንና ሌሎች ቁሳቁሶችም በተሽከርካሪው ውስጥ በጣቢያው የፍተሻ ሰራተኞች መያዙን ገልጸዋል።

መኪናዉና አሽከርካሪዉ በህግ ቁጥጥር ስር ዉለዉ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸዉ እንደሚገኘ የጣቢያ አስተባባሪዉ ኮማንደር አህመድ ገልጸዋል።

(ኢዜአ)

Exit mobile version