ETHIO12.COM

ለዓለም ዓቀፍ መልዕክተኞችን ኢትዮጵያ እንቅጩን አስታወቀች

ትግራይ ደርሰውና በፎቶ ተንበሽብሸው ለተመለሱት የዓለም ዓቀፍ መልዕክተኞች ኢትዮጵያ እንቅጩን ማስገንዘቧ ተሰማ። የወልቃይት ጉዳይ አሁን ላይ የታተመ “የደም ዋጋ” እንደሆነ በየአቅጣጫው በሚነገልጽበት ወቅት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ውጭ አደራዳሪ የሚባል ነገር እንደማትቀበል በድጋሚ አመልክታለች።

መልዕክተኞቹ ከመቀለ ቆይታቸው በሁዋላ ያልተገደበ የእርዳታ አቅርቦትና በረራ እንዲሁም የተቋረጡ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ በመግለቻቸው ቢያስታውቁም ኢትዮጵያ እርዳታ ያለገደ እየገባ እንደሆነ አመልክታ መልዕክተኞቹ የሰላም ንግግሩ ላይ እንዲያተኩሩ አሳስባበለች። በአቋም ከያዘችው ጉዳይ ንቅንቅ እንደማትልም አመልክታለች።

ትህነግ በክረምት ውጊያ እንደሚከፍት አስታውቆና ዝግጅቱንም አተናቆ እንደነበር አስታውቆ የነበረ ቢሆንም በለመነው መጠን ቀለብ ስለተሰፈረለት ውጊያውን አለማድረጉን ዶክተር ደብረጽዮን በኩራትና በድል ስሜት ማስታወቃቸው አይዘነጋም። መንግስት ፈርቶ ቀለብ እንዲገባ መፍቀዱን ሲያስታውቁ አገልግሎት እንዲከፈት፣ ማመልከታቸው ይታወሳል።

ይህንኑ ተከትሎ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ በቲውተር ገጻቸው ትህነግ እህል አከማችቶ ትንኮሳ ለመጀመር ዝግጅት ላይ መሆኑንና እያምታታ እንደሆነ አመልክተዋል። የትህነግ አፈ ቀላጤ አቶ ጌታቸው ረዳ ዛቻ መሰንዘራቸውን ተከትሎም ” የወልቃይት ጉዳይ ታትሟል” ሲሉ የተለያዩ ሃላፊዎች ተናግረዋል። “ከቻላችሁ ሞክሩ” የሚል ምላሽ የሰጡም አሉ።

አሁን ላይ የኢትዮጵያ ጦር ቁጥሩን በሚሊዮን ያሳደገና ቀደም ሲል የነበረበትን የባለሙያ እንዲሁም የመሳሪያ ቸግር ሙሉ በሙሉ የቀረፈ፣ ቲከኖሎጂን የታጠቀና እልህና ቁጣ የተሞላ ሰራዊት በመሆኑ ትህነግ ውጊያ ከሞከረ በአጭር ቀናት የሚጠናቀቅ ኦፕሬሽን እንደተዘጋጀለት የሚጠቁሙ አማራጩ ፈረንጃን መተማመን ሳይሆን ወደ ሰላም በቀናነት መመለስ ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል።

የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መልዕክተኞች እና አምባሳደሮች የመቐለ ቆይታን በተመለከተ ጉዳዩን የያዙበት መንገድ በመንግስት ላይ ቅሬታ መፈጠሩን ያመልከቱት ከዚሁ መነሻ እንደሆነ ተሰምቷል።

አምባሳደሩ፤ ልዩ መልዕክተኞቹ እና አምባሳደሮቹ ለሰላም ንግግር ጥረት ማድረግ ሲገባቸው በሌላ ወገን የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ላይ ተጠምደዋል ብለዋል።

” ተቋርጠው የሚገኙ መሠረታዊ አገልግሎቶች በተመለከተ የመንግሥት አቋም ግልጽ ነው ፤ አገልግሎት ማስጀመር የሚቻልባቸው ሁኔታ መፍጠር እና የሰላም ንግግር መጀመር ቀዳሚ መሆን አለበት ” ሲሉ ገልፀዋል።

” ልዩ መልዕክተኞቹ እና አምባሳደሮቹ ከመቐለ ጉዟቸው በኋላ ባወጡት መግለጫ አሁንም ‘ ያልተገደብ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ‘ የሚል ትርክት እንደቀጠለ ነው ” ያሉት አምባሳደሩ ” አሁን ላይ ወደ ክልሉ ያልተገደብ በረራ እና የጭነት መኪኖች ጉዞ እየተደረገ ነው ” ሲሉ ገልፀዋል።

የነዳጅ ጉዳይም መፍትሄ እንደተሰጠውና በሁሉም አድናቆት የተቸረው ጉዳይ ነው ብለዋል።የሰላም ንግግሩን በተመለከተም ፤ ” የሚመራው የአፍሪካ ኅብረት ብቻ ነው ” ሲሉ አስረግጠው ፅፈዋል።

ከዚህ ቀደም የፌደራል መንግሥት ከህወሓት ጋር የሚደረገውን ንግግር መምራት ያለበት የአፍሪካ ኅብረት እንዲሆን ፍላጎት እንዳለው ገልጾ ነበር።

ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ” ህወሓት ” ደግሞ ድርድሩ በበላይነት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እንዲመሩ ጠይቆ ነበር።

ማክሰኞ ትግራይ ክልል መቐለ የተጓዙት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መልዕክተኞች ደግሞ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደውን ንግግር ለመደገፍ ዝግጁ ነን ማለታቸውን ጠቅሶ ተዘግቧል።

Exit mobile version