Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ” ከአቅም በታች” ተብሎ ተመደበ፤ ስጋት የመሆን ደረጃው ተመናምኗል

በትግራይ ክልል ያለውን ታጣቂ ሃይል የሚመሩት የቀድሞ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ” ዝግጅታችንን ጨርሰናል። በየትኛውም ሰዓት ማድረግ የምንፈልገውን እናደርጋለን” በማለት በከፍተኛ ብቃት ላይ እንደሚገኝ የተናገሩለትን ሃይል መንግስት ከተራ የመንደር ተዋጊ ባነሰ መልኩ ” ከአቅም በታች” ሲል የስጋት ደረጃው መመናመኑን አመልከተ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በድንገት እንዲመታ ከተደረገና በትግራይ ያለው መሳሪያ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከተወሰደ በሁዋላ በውስን ሃይል በተደረገ የሞት ሽረት ውጊያ አብዛኛውን መሳሪያ ማስመለስ እንደተቻለ በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል።

በቀድሞ የመከላከያ ኤታማዦር ሹም ከነራል ሳድቃንና በህይወት በሌሉ የትህነግ ካድሬዎች በቅጽበታዊ ጥቃት በደቂቃዎች ውስጥ መድመሰሱ የተነገረለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከክህደት ካራ ተርፎ ትግራይን ዳግም ቢቆጣጠርም ሰፊ በደል በድጋሚ ደርሶበት ትግራይን ለቆ መውጣቱም በአመራሩና አባላቱ መገለጹ አይዘነጋም። ከዚያን በሁዋላ ትህነግ በለውጡ ማግስትና አስቀድሞ ሲያደራጅ የነበረውን ሃይል አሰማርቶ ሸዋ ሲዘልቅ የኢትዮጵያ መከላከያ እያፈገፈገ ራሱን በሰው ሃይልና በሎጅስቲክ ሲያደራጅ ቆይቶ በቀናት ውስጥ የትህነግን ሃይል ሽባ ማድረግ እንደቻለ የጦር መሪዎች ቢናገሩም ትህነግ ሃይሉ ሳይነካ ሆን ብሎ ወደ ትግራይ ማፈግፈጉን፣ ይህንንም ያደረገው ለሰላም ሲል እንደሆነ አስታውቆ ነበር።

ትህነግ ይህንን ቢልም የባይቶና መሪና የራሱ የትህነግ የወጣቶች ክንፍ ከስምንት መቶ ሺህ በላይ የትግራይ ወጣቶች የገቡበት እንደማይታወቅ በራሳቸው ሚዲያ ማስታወቃቸው፣ እናቶች ልጆቻቸውን መጠየቃቸውን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ አክቲቪስቶች በተደጋጋሚ ሲያታውቁ ቆይተዋል።

ይህ ከሆነ በሁዋላ በቂ ዝግጅት ማደረጉንና ለውጊያ ራሱን እንዳበቃ የትህነግ ሃይል መሪ ቢናገሩም አሁን ድረስ የተሞከር ነገር የለም። በመንግስት በኩል ቃል በቃል ወቅታዊ ምላሽ ባይሰጥም የየክፍሉና ክፍለጦር አመራሮች ” አታስቡ” ሲሉ መግለጫ ሲሰጡ ቆይተዋል።

ራሱን ” ተራራ ያንቀጠቀጠ” ሲል የሚጠራውና ” ውጊያ ባህላዊ ጨዋታዬ ነው” በሚል የሚያሞካሸው ትህነግ በቅርቡ በመሪው ዶክተር ደብረጽዮን አማካይነት መንግስት እየፈራ ሁሉንማይነት አቅርቦት ለማዘጋጀት መገደዱን ባስታወቁ በሳምንት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የአገሪቱ የብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት “ከአቅም በታች” ሲል የትህነግን ደረጃ ወደ መንደር በጥባጭ አውርዶታል።

በቅርቡ ለፓርላማ ሪፖርት ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ሰአርዊታችን አምስትና ስድስት እጥፍ ተገንብቷል” ሲሉ ተሰምተው ነበር። ዛሬ ኢትዮጵያ የክልል ልዩ ሃይል፣ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስና ሚሊሻዎችን ሳያካትት በሚሊዮን የሚቆጠር ሃይል እንዳላት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከቁጥሩም ባሻገር የአገሪቱ የጸጥታ ሃይል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ረቂቅ የሚባሉ መሳሪያዎችን የታጠቀና በነበረው የማገገሚያ ጊዜ ባለሙያዎችን፣ ከባድ መሳሪያ ተኳሾችንና የሽምቅ ተዋጊዎችን በሚገባ አስለጥኖ የነበረበትን ክፍተት መሙላቱን ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ሲያስረዱ ነበር።

ከዚህ ሁሉ በላይ የአየር ሃይል ሰፊ አቅምና ትጥቅ፣ እዲሁም የወቅቱን ቴክኖሎጂ የታጠቀ መሆኑ ለአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች መከታ የሆነበት ደረጃ መድረሱን የጎበኙ፣ በተለይዩ ሃላፊነት ላይ የተሰማሩ የሰራዊቱ አባለትና አመራሮች፣ እንዲሁም አዛዦች የአየር ሃይሉ ብቃት ኢትዮጵያን ከየተኛውም ሃይል የሚታደግ እንደሆነ በኩራት አርጋግጠዋል። ይህንኑ አቅማቸውን በሶማሌ በኩል በቅርቡ ለተነሳው የአልሸባብ ሃይል በተሰጠ ምላሽ አሳይቷል።

ይህ ሁሉ ከሆነ በሁዋላ ዛሬ ስብሰባ ያደረገው የብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በትግራይ ክልል አካባቢ ያለው የሥጋት ሁኔታ ገምግሞ የትህነግ ወቅታዊ ቁመናና አቅም ከጸጥታ አካላት አቅም በታች እንደሆነ ለህዝብ ይፋ አድርጓል።

በትግራይ ክልል ያለውን የሥጋት ሁኔታ ከጸጥታ አካላት ዐቅም በታች እንደሆነ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ያስታወቀው በአተቃላይ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መክሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።

“በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ በድርድር እንዲፈታ መንግሥት አቅጣጫ መያዙና የተግባር እንቅስቃሴ ማድረጉ የአደባባይ እውነታ ነው” ሲል ያመለከተው መግለጫ ፣ “ድርድሩ ውጤት እስኪያመጣ ድረስ ለመቀጠል መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን ወዳጅም ጠላትም ተረድቶታል” በማለት ለሰላም ያለውን የማያወላዳ አቋም አስታውሷል።

ለሰላም ያለው ቁርጠኛነት እንደማይታጠፍ ሁሉ፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍልና በዚያ አካባቢ ሊኖር ይችላል የሚባለውን ስጋት የአገሪቱ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ገምግሟል። ለግምገማ ከቀረበለት ሪፖርት በመነሣት የደኅንነት ምክር ቤቱ የትህነግን ወቅታዊ ቁመና ከጸጥታ አካላት ዐቅም በታች ሲል ደረጃ ሰጥቶታል። በተሰጠው ደረጃ መሰረት በተገቢው መንገድ የጸጥታ ሃይሉ ተገቢ የሚባል ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ በሪፖርቱ መረጋገጡን በመግለጫው አመልክቷል።

Exit mobile version