Site icon ETHIO12.COM

አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ ከፈጸመው ጥቃት ወዲህ በኢትዮጵያ ምን ምን ተከሰተ?

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ዓለም በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ትኩረቱን ባደረገበት ወቅት የህወሓት ታጣቂዎች በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ጥቃት ፈጸሙ። ይህ እለት የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ በግልጽ ጦርነት የከፈተበት እለት ነበር።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 4 ቀን 2020
የአሽባሪው ሕወሓት ቡድን በአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በፈጸመ ሃያ አራት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፤ “በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጸመ” የሚል የቲዊተር ዘመቻ ከፈተ። ዘመቻውንም በቅንጅት በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች አውታሮች አሰራጨ። በዚህ ፖሮፓጋንዳው የአለም ማህበረሰብን ሲያደናግር የቀደመው አልነበረም።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 5 ቀን 2020
ከአሸባሪው ሕወሓት ቃለ አቀባዮች መካከል አንዱ ሴኩቱሬ ጌታቸው በመከላከያ ሰራዊት ላይ “መብረቃዊ ጥቃት” ፈጽመናል ሲል በግልጽ በቴሌቪዥን ተናገረ።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 6 ቀን 2020
በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ተጠባባቂ ረዳት ፀሃፊ ሮበርት ኤፍ. ኮዴክ፣ ህወሓት የጦርነቱ መነሻ መሆኑን ጦርነቱንም ህወሓት መጀመሩን በግልጽ አስታወቁ።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 9 ቀን 2020
አሸባሪው ቡድን አሰልጥኖና አስታጥቆ ለእኩይ ተግባር ባሰማራው “ሳምሪ” በተሰባለው ቡድን በማይካድራ በአማራ አርሶ አደሮች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተፈጸመ።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 14 ቀን 2020
የህወሓት እኩይ ሴራ የሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመፈጸም ብቻ ያቆመ አልነበረም፣ በአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋትን ለመፍጠር የኤርትራ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው አስመራ ሮኬቶችን መተኮሱን የቡድኑን መሪ አረጋግጧል።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቨምበር 17 ቀን 2020
የአሜሪካው ምክር ቤት ፀሐፊ የሮኬት ጥቃቱን አወግዘዋል። የምክር ቤቱ ጸሐፊ ማኪ ፖምፒዮ አሸባሪው ህወሓት በኤርትራ ላይ የሮኬት ጥቃት ማድረሱን ኮንነዋል፤ ድርጊቱ ግጭቱን አለም አቀፍ መልክ ለማስያዝ በማሰብ የተፈጸም መሆኑን በመጥቀስ ሊወገዝ እንደሚገባው ገልጸዋል።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 27 ቀን 2020
ግጭቱን አለም አቀፍ መልክ ለማስያዝ አሸባሪው ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ ሮኬት ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ አስወነጨፈ፤ ያስወነጨፈው ሮኬትም በአስመራ የመኖሪያ መንደሮች አቅራቢያ ማረፉ ተነግሯል።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 28 ቀን 2020
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ሳምንታት ከወሰደ የህግ ማስከበር ዘመቻ በኋላ መከላከያ የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ገባ።

– እኤአ ኖቬምበር 30 ቀን 2020
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ አስመልክተው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ስጥተዋል።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 28 ቀን 2020
የቦስተን ከተማ ነዋሪ የሆነው የጁንታው ደጋፊ ራሱን “ቄስ ወልደማርያም” በሚል ስም ቄስ በመምሰል በተንቀሳቃሽ ምስል አማካኝነት በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን በፀሎትና በቅዳሴ ላይ የነበሩ ሰዎች በአማራ ልዩ ሃይልና በኤርትራ ወታደሮች ተገደሉ በማለት ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማደናገር የሀሰት መረጃ አሰራጨ።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 30 ቀን 2020
በአክሱምና በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተጨፍጭፈዋል ተብሎ ሐሰተኛ መረጃ ቢሰራጭም አመታዊው የአክሱም ጽዮን የንግስ ክብረበዓል በሽዎች የሚቆጠር ምዕመን ተሳትፈውበት ያለምንም ችግር ተከብሯል።

– እኤአ አቆጣጠር ዲሴምበር 14 ቀን 2020
የሕወሃት ሰዎች የኢትዮ ቴሌኮምን ኔትወርክ አገልግሎት እንዳይሰጥ ማድረጋቸውን ኢትዮ-ቴሌኮም በሲሲቲቪ ተንቀሳቃሽ ምስሎች አሰደግፎ ይፋ አደረገ። በትግራይ ክልል እአአ ኖቬምበር 3 ቀን 2020 በሀገሪቱ ሰሜናዊ እዝ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ ከሰአታት በፊት በመቀሌ የሚገኘውን የቴሌኮሙኒኬሽን ኔትዎርክ ማዕከልን የህወሓት ሰዎች አገልግሎቱን እንዳቋረጡት መረጃው ያሳያል።

– እኤአ አቆጣጠር ዲሴምበር 25 ቀን 2020
የመከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከተማን ጨምሮ ስትራቴጅካዊ የሆኑ ቦታዎችን ተቆጣጥሯል፣ የሰብዓዊ ድጋፎች ለዜጎች እንዲደርሱ የፌደራል መንግስት ማስተባበርና ምቹ ሁኔታዎችን ፈጠረ። ይሁን እንጂ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያደርሱ ቡድኖች በሚፈለገው ደረጃ ተሳትፎ ማድረግ አልቻሉም ነበር። ይህ ሁኔታ በሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ሰበብ ምዕራባውያንን እና ሚዲያዎቻቸው የአሸባሪውን ቡድን ከሽንፈቱ እንዲያንሰራራ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎታቸው የተንጸባረቀበት መሆኑ ተስተውሏል።

– እኤአ አቆጣጠር ኦክቶበር 4 ቀን 2021
ሾልኮ በወጣ የድምፅ ቅጂ መቀመጫውን ኢትዮጵያ ያደረገው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ ማውሪን አቺንግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚመራው ሰብአዊ ርዳታ ህወሓት ሰርጎ ለመግባት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጋልጠዋል። አላማው ከሰብአዊነት ይልቅ የህወሓትን የፖለቲካ አላማዎች ለማሳካ የሚደረግ ነበር ተብሏል፤

– እኤአ አቆጣጠር ኦክቶበር 23 ቀን 2021
ምዕራባውያን የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነቱን እንዲያቆም ግፊት ሲያደርጉ፤ ህወሓት በሰሜን አማራና አፋር ክልሎች ላይ ጥቃቱን ቀጥሏል። የሰብአዊ ዕርዳታ ስርጭትም መስተጓጎሉ ተገልጿል።

– እኤአ አቆጣጠር ኦክቶበር 30 ቀን 2021
የትግራይ ታጣቂዎች ከ3 ወራት ተከታታይ ውጊያ በኋላ ደሴ ከተማን ያዙ፤ በአዲስ አበባ በጦርነቱ ጉዳይ ላይ ፓርላማው አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ አድርጓል።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 1 ቀን 2021
የህወሓት ታጣቂ መሪ ፃድቃን በሰጠው ቃለ ምልልስ “ጦርነቱ አሁን ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፣ ምንም የምንደራደርበት ነገር የለም” በማለት ድል አውጇል።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 2 ቀን 2021
ፓርላማው ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 9 ቀን 2021
የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በተመለከተ ዳግም ተሰበሰበ። ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ዜጎቻቸው ኢትዮጵያን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አሳሰቡ። ሆኖም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እነዚህን ጥሪዎች የበለጠ አለመረጋጋትን ለመፍጠር ታስበው የተደረገ አድርጎ በመቁጠር ተቃውሞውን ገልጿል።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 12 ቀን 2021
የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ቀውስ እየሰፋ ሲሄድ “ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት የአሜሪካ ወታደሮች” በቅርበት መኖራቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ጄኔራል ዊሊያም ዛና ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሰተያያት ሰጪዎችም የአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ ውስጣዊ ግጭት ላይ ስጋት ይፈጥራል ሲሉ ተቃወሙ።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 22 ቀን 2021
የ#nomore ዘመቻ ተጀመረ፤ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን ዲያሰፖራዎች በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ በሚገኙ ትላልቅ ከተሞች የሐሰት መረጃዎችን በመቃወም ተከታታይ ህዝባዊ ሰልፎችን አካሄዱ። ህወሓት በቅርቡ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግስት ለመጣል እያደረገ ያለውን አረመኔያዊ ዘመቻ በመቃወም ተቃውሟቸውን ለጆ ባይደን አሰተዳደር አቅርበዋል።

– እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 24 ቀን 2021
የኢትዮጵያን መንግስት በሃይል ለማስወገድ ለሚፈልጉ አማፂ ቡድኖች ድጋፍ ሲሰጡ የተደረሰባቸውን አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ኢትዮጵያ አዘዘች። አየርላንድም የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት እንዲሰበሰብ አጀንዳ አይዛ ነበር።

-እኤአ አቆጣጠር ኖቬምበር 24 ቀን 2021
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የህወሓት ታጣቂዎችን ለመመከት በሚደረገው ውጊያ ሰራዊቱን ተቀላቀሉ።

– እኤአ አቆጣጠር ዲሴምበር 16 ቀን 2021
በፌዴራል መንግስት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ሰሜን ተመልሰው ሸሹ። ህወሓት ለወራት የቆየባት ወሳኟ ስትራቴጂካዊቷ ጋሸና ከተማ በኢትዮጵያ መንግስት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ዋለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የህወሓት ታጣቂዎች ተገደሉ።

-እኤአ አቆጣጠር ዲሴምበር 20 ቀን 2021
ተከታታይ ሽንፈትና ከባድ ኪሳራ የደረሰበት ህወሓት በወረራ ከያዛቸው አከባቢዎች መውጣቱን አስታወቀ። የህወሓቱ መሪም በሰብአዊነት ምክንያት ወጥቻለሁ ሲል አስታወቀ

– እኤአ አቆጣጠር ዲሴምበር 23 ቀን 2021
የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ ሰራዊቱ ወደ ትግራይ እንደማይዘልቅ አስታወቁ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አማፂ ኃይሎችም በወረራ ከያዟቸው ቦታዎች እንደተባረሩና ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጿል።

– እኤአ አቆጣጠር ጃንዋሪ 7 ቀን 2022
በሽብር እና በሽብርተኝነት ተከሰው ታስረው የነበሩ አቶ ስብሃት ነጋ፣ እስክንድር ነጋ እና ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው እስረኞች ተፈቱ። ይህ በመንግስት የተወሰደው ተግባር ብዙዎችን ያስደነገጠ ያልተጠበቀ እርምጃ ነበር።

– እኤአ አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 4 ቀን 2022
የኢትዮጵያ ጦር እና የአካባቢው ሚሊሻዎች በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት ወደ ጥንታዊቷ የላሊበላ ከተማ የገቡት የህወሓት ታጣቂዎች ከከተማዋ ተባረው ወጡ፤

– እኤአ አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 15 /2022
በሀገሪቱ እየታየ ካለው የፀጥታ ሁኔታ አንፃር ለስድስት ወራት ተጥሎ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ተደርጓል። በወቅቱም የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ “አሁን በመደበኛ የህግ ማስከበር ዘዴዎች ህግን ማስከበር ስለሚቻል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነስቷል” ብለዋል።

– እኤአ አቆጣጠር ኤፕሪል 5 /2022
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባካሄደው ጥናት በወልቃይትና ሁመራ አሸባሪው ሲያስተዳዳር በቆየባቸው ባለፉት 30 አመታት በርካታ የአማራ ተወላጆችን በግፍ የተገደሉበት የጅምላ መቃብሮችን ማግኘቱን ይፋ አደረገ። የጅምላ ግድያውና የተገኘው መቃብር በዓለም አቀፍ ዋና ዋና የዜና ማሰራጫዎች ብዙም ሽፋን አላገኘም።

– እኤአ አቆጣጠር ጁን 2 /2022
በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚደረገው የሰላም ውይይት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ግጭትን ለማስቆም ያለውን ብሩህ ተስፋ በማስመልከት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሌሴንጎ ኦባሳንጆ ይፋ አደረጉ፤

– እኤአ አቆጣጠር ጁላይ 31/2022
ተስፋ ሰጪ የሰላም ንግግሮች ተደመጡ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። ይሁን እንጂ ህወሓት ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ለሰላም ውይይቱ እንቅፋት መሆኑን ቀጠለ፤

– እኤአ አቆጣጠር ኦገስት13 /2022
የአባይ ግድብ ለሶስት ተከታታይ አመታት የውኃ ሙሌት ተከናውኖ ሁለተኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ጀምሯል።

የዚህ ዘገባ ምንጭ https://abren.org/history/ ነው
በመሀመድ ሁሴን ENA

Exit mobile version